Thursday, January 24, 2019
የሀሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
ብዙ ክለቦች አይናቸውን የጣሉበት ወጣቱ ፍራንክ ዲዮንግ ትናንት በይፋ የባርሴሎና ተጨዋች ሆኗል በአያክሳምስተርዳም ሁለት አመት የቆየው የ21አመቱ ኮከብ በ75ሚዩ ባርሴሎናን መቀላቀሉ ይፋ ሆኗል በፒኤስጂ በጥብቅ ቢፈለግም ማረፍያው ስፔን ሆኗል 71ሚዩ መነሻ ሲሆን ብቃቱ እየታየ 11ሚዩ ለአያክሶች ይከፈላቸዋል
ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ፒኤስጂ ለማምራት ከፒኤስጂ ፕሬዝዳንት ከናስር አልኻላፊ ጋር ተነጋግሯል ተብሏል ከአሰልጣኝነት ከተነሳ ቡሀላ ወደ ኳታር አምርቶ ለቤይን ስፖርት በተንታኝነት እየሰሩ ባሉበት ጊዜ ከፒኤስጂ ፕሬዝዳንት ጋር ተነጋግረዋል ተብሏል
ቪክቶር ሞሰስ ወደ ፊነርባቼ ሊያመራ እንደሆነ መረጃዎች ወተዋል በአንቶኒዮ ኮንቴ ስር በቀኝ ተመላላሽነት በቋሚነት ሲሰለፍ የነበረው ሞሰስ ሳሪ ከመጣ ቡሀላ ግን ምንም እድል እየተሰጠው አደለም ይህን ተከትሎ ዛሬ ወይም ነገ በውሰት ወደ ቱርኩ ክለብ እንደሚያቀና ተነግሩዋል
ጁቬንቱስ በዚ የጥር የዝውውር መስኮት ራምሴን ለማስፈረም ለአርሰናል ኤሚል አውዱዮን የተባለ ግብ ጠባቂ አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ ሆኗል ልጁ አሁን ላይ ሳምፕዶርያ ነው የሚገኘው ከፒተር ቼክ ጋ ክረምት ላይ ሚለያዩት አርሰናሎች ሁለተኛ በረኛ ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ ይህን ተከትሎ ቀድሞውንም ሚፈልጉትን ተጨዋች በአማራጭ ሊያገኙት ይችላሉ
ከጥቂት ወራት በፊት ወደ ልጅነት ክለቡ ተመልሶ ማሰልጠን የጀመረው የቀድሞ ኮኮብ ሄነሪ ከቡድኑ ጋ ሊለያይ እንደሚችል ተሰምቷል ቡድኑን ከወራጅ ቀጠና ማሶጣት የከበደው ሄነሪ ሰሞኑ ከስራው በላይ የቡድኑ ህልውና እንደሚያሳስበው መናገሩ ይታወሳል እናም መረጃው እንዳወጣው የቀድሞ ኮከብ ከሶስት ወራት ቡሀላ ከክለቡ ጋር ሊለያይ ይችላል ብሏል ይህንን ተከትሎ ሄነሪ የተካው የቀድሞ አሰልጣኝ ሊዮናር ያርዲ በድጋሚ ወደ ሞናኮ ይመለሳሉ ተብሏል
አርሰናሎች ሞሮኮዋዊን የጁቬንቱስ ተከላካይ መህዲ ቤናቲያን ለመውሰድ ፍላጎት አላቸው ልጁን ከአርሰናል በተጨማሪ ፉልሀም እና ከተለያዩ የቻይና ክለቦች ጥያቄም ቀርቦለታል ከአርሰናል እና ፉልሀም ይልቅ የቻይና ክለቦች ለልጁም ሆነ ለጁቬንቱስ ከፍተኛ ገንዘብ ቀርቦላቸዋል
ሴድሪክ ሱዋሬዝ ወደ ኢንተር ሚላን ለማምራት እየተነጋገሩ ይገኛሉ ኢንተሮች በክረምቱ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ያስፈረሙት ሺሜቨር ሳልኮ በተጠበቀበት ደረጃ ባለመገኘቱ ወደ ገበያ ለመውጣት ተገደዋል ዋነኛ ኢላማቸውም ፖርቹጋላዊው ሴድሪክ ሱዋሬዝ ሆኗል
የአልቫሮ ሞራታ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ መግባቱ እርግጥ መሆኑን ተከትሎ ጊልሰን ማርቲኔዝ ወደ ሞናኮ ለመሄድ ተቃርቧል ዝውውሩም ለመጠናቀቅ ከጫፍ ደርሷል
ወደ ቼልሲ ያመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የዜኒቱ አማካይ ሊዮናርዶ ባራቴዝ ወደ ፒኤስጂ ለመሆድ ምርጫውን እንዳደረገ የተለያዩ ታማኝ ምንጮች አስነብበዋል በተጨማሪም ፖርቹጋላዊው የሙኒክ አማካይ ሬናቶ ሳንቼዝ ወደ ፒኤስጂ ሊያመራ እንደሚችል ተነግሩዋል
Wednesday, January 23, 2019
የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አርሰናል የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካዩን ኤሪክ ባይሊን በውሰት ለመውሰድ ለዩናይትድ ጥያቄ አቅርበው ነበር ኤምሪም ልጁን የማግኘት ተስፋ ነበራቸው ለማግኘት ነገር ግን ዩናይትዶች ጥያቄውን ውድቅ አድርገውባቸዋል ዩናይትዶችም ልጁን እንደሚፈልጉት እና እንደማይለቁትም ተናግረዋል
በፒኤስጂ እና በማንችስተር ሲቲ ሲፈለግ የነበረው ሆላንዳዊው የአያክስ አማካይ ፍራንክ ዲዮንግ በመጨረሻም ማረፊያው ባርሴሎና ሊሆን ነው ባርሳዎች ለልጁ እስከ 65ሚፓ ከፍለው ሊያመጡት ከጫፍ ደርሰዋል ባርሴሎና ዝውውሩን የሚያጠናቅቅ ቡድን ዛሬ ወደ ሆላንድ እንደሚልክ ነው የተሰማው ተጨዋቹም ወደ ስፔን መሄድ ይፈልጋል
ፒኤስጂ በፈረንሳይ ሊግ የስነምግባር ኮሚቴ ቅጣት ተላልፎበታል 100ሺዩ የተቀጣው ምክንያቱም ደሞ ወጣት ተጨዋቾችን ሲያስፈርም ዘርን መሰረት ያደረገ መረጃ መዝገቡ ላይ ያሰፍራሉ ሚል መረጃ ወቷል የፈረንሳዩ ዌብሳይት ሚዲያ ፓርት ይህን ዘገባ ይዞ ከወጣ ቡሀላ ምርመራ ሲደረግ ነበር በመጨረሻም ቅጣት ተላልፎበታል ፒኤስጂ ላይ
ኤሲ ሚላኖች የሂግዌንን ለመልቀቅ መቃረብን ተከትሎ የጄንዋውን አጥቂ ክሪትስቶስ ፒያቲክን ለማስፈረም ተቃርበዋል ለዝውውሩ 30ሚፓ ይከፍላሉ ዝውውሩም ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሏል ሜዲካሉንም ዛሬ እንደሚያደርግ ተነግሯል በሚላንም የአምስት አመት ኮንትራት ይፈርማል
ቶማስ ቱሄል ከማርኮ ቬራቲ መጎዳት እና ከራቢዮት አለመጫወት የተነሳ የመሀል ሜዳው ክፍል ሳስቷል ብለዋል ሌላ የመሀል ሜዳ ተጨዋች ያስፈልገዋልም ብለዋል የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት አማካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ ሊወጡ ነው በዝውውሩም የናፖሊውን አለንን እና የዋትፎርዱን ዶኮሬን ኢላማቸው ውስጥ አስገብተዋል
አርሰናልን እንደሚለቅ የተረጋገጠው አሮን ራምሴ አርሰናሎች ዴኒስ ስዋሬዝን ወይም ሀሜስ ሮድሪጌዝን ካገኙ በጥር የዝውውር መስኮት ሊለቁት እንደሚችሉ ተሰምቷል .
የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ሄሴ ሮድሪጌዝ ወደ ጣሊያኑ ቶሪኖ ለመዘዋወር ተቃርቧል
የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ በውሰት ለሬዲንግ ለመጫወት መፈረሙ ተረጋግጧል
Tuesday, January 22, 2019
የማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
ሰሞኑ በተደጋጋሚ ከኮሎምቢያዊው ሀሜስ ሮድሪጌዝ ጋ ስሙ እየተነሳ የሚገኘው አርሰናል ከባየርን ሙኒክ ይልቅ ሪያል ማድሪድን ለማነጋገር ወስነዋል ተብሏል ምክንያቱም ሙኒኮች ልጁን በቋሚነት እንደማያስፈርሙት ብዙ ማረጋገጫዎች እየወጡ ነው መሆናቸውን ተከትሎ ከማድሪድ ጋር እየተነጋገረ ነው ሚለው መረጃ በሰፊው እየወጣ ነው
.
ሰሞኑ በሰፊው ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ የተነሳው የዌስትሀሙ ማርኮ አርናቶቪችን በተመለከተ ዌስትሀሞች በልጁ ጉዳይ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን መረጃዎች እያሳዩ ይገኛሉ ልጁ በዚ የጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን እንዲለቅ አይፈቀድለትም በቀጣይ ክረምት ግን ወደየትኛውም ክለብ መሄድ ከፈለገ እንደሚፈቀድለት ውሳኔ ላይ ደርሱዋል
.
የ38 አመቱ የቀድሞ የአርሰናል እና የቸልሲ ተጨዋች አሽሊ ኮል የቀድሞ የክለቡ አጋር ሚያሰለጥነውን ደርቢ ካውንቲን እስከዚ አመት መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል ተቀላቅሉዋል በቻምፒየን ሺፑ ከሚጫወቱ አንጋፋ ተጨዋች የመጀመሪያው ይሆናል ማለት ነው
.
ትናንት ምሽት ወጣቱን ማክቶሚናይን ውል ያራዘሙት ዩናይትዶች በዚ ሳምንት የወጣቱን ባለተሰጦ ተጨዋች የማርሻልን ኮንትራት ለማስፈረም ከጫፍ ደርሱዋል ከማርሻል በተጨማሪም ዴህያ ማታ እና ሄሬራም የተሳካ ድርድር እያደረጉ እንደሆነ ታውቋል
.
የሶስት ተጨዋቾች ዝውውር በፒያቴክ ዝውውር መጓተት ተይዟል ሂጉዌይን አሁንም በጣሊያን ይገኛል ኤሲ ሚላኖች የጄኑዋውን ፒያቴክ ዝውውር እንዳጠናቀቁ አርጀንቲናዊው አጥቂ ወደ ለንደን ያመራል ከዛም ሞራታ ወደ ወደ አትሌቲኮ እንዲዛወር በቼልሲ ፍቃድ ያገኛል
.
ሪያል ማድሪዶች ተጨዋች የማስፈረም አማራጫቸውን በሀሜስ ሮድሪጌዝ ላይ ጥለዋል በሙኒክ በውሰት የሚገኘውን ሀሜስን በክረምቱ ኤሪክሰንን ከቶተንሀም ለማምጣት አንድ የዝውውሩ አካል ሊያደርጉት አስበዋል በተጨዋቹ ምክንያት ይሄ ማይሳካ ከሆነ ሌላኛው ሚፈልጉትን ሀዛርድን ከቸልሲ ለመውሰድ አንድ የዝውውር አካል ሊያደርጉት ይፈልጋሉ ማድሪዶች ግን ዋና ኢላማቸው ኤሪክሰን ነው
.
️ቢቢሲ ስፖርት በመረጃው እንዳስነበበው ከሆነ ሜሱት ኦዚል ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ሊሄድ እንደሚችል እና ከአሌክሲስ ሳንቼዝ ጋር ዳግም ሊገናኙ እንደሚችል ዘግቧል ዩናይትዶችም ልጁን በቅርበት እየተመለከቱት ነው
.
የቀድሞ የቸልሲ እና የኒውካስትል አጥቂ ዴምባባ ወደ ኢስታንቡል ባሳክስዬር አምርቷል ዝውውሩም ለ6 የሚቆይ የውሰት ውል ነው በቻይና ሻንሺንዋ እየተጫወተ የነበረው ዴምባባ በድጋሚ ወደ ቱርክ ተመልሱዋል
Monday, January 21, 2019
የማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች
አሰልቺው የጎንዛሎ ሂግዌን ዝውውር ወደ መጠናቀቁ ደርሧል ከክረምት ጀምሮ ስሙ በሰፊው ከቸልሲ ጋ የተያያዘው ሂግዌን ዝውውሩ ወደ መጠናቀቁ ደርሶለታል እንደምክንያት የተቀመጠው ዛሬ ምሽት ኤሲሚላን ከጄንዋ ከሚያደርጉት ጨዋታ ውጭ ሆኗል
ማቲዮ ዳርሚያን ከማንችስተር ዩናይትድ ወደ ጁቬንቱስ በውሰት ሊዘዋወር እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል ጁቬንቱስ ተጨዋቹን በውሰት ውል እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ወስዶ የውድድር አመቱ ሲጠናቀቅ በ7.1ሚፓ ለማስፈረም ከዩናይትድ ጋ ድርድር መጀመራቸው ተሰምቷል
አርሰናል የአትሌቲኮ ማድሪዱን ጊልሰን ማርቲንሰንን በውሰት ለማምጣት ተስማምቷል ሚል መረጃ ወቷል በተለይ የፖርቹጋሉ ኦዦጎ የተባለው ጋዜጣ ይዞት እንደወጣው ከሆነ በይፋ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ጥያቄ አቅርበዋል አትሌቲኮዎች ደግሞ ምናልባት ሞራታን የማግኘት እድላቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ማርቲንስን ለመስጠት ፍላጎት አሳይቷል የሚል መረጃ አውጥቷል
ሂግዌንን ወደ ቼልሲ ለመላክ እጅጉን የተቃረቡት ኤሲ ሚላኖች የሱን ምትክ ክሪትስቶስ ፒያቲክን በ31ሚ.ፓ ከጄንዋ ለማስፈረም እንደበስማማ እና ከተጨዋቹም ጋ በግል ከስምምነት እንደደረሰም ተነግሩዋል ልጁም ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ የጄንዋን ማልያ በመልበስ ቀጣይ ክለቡን ይገጥማል
ሜሱት ኦዚልን ሽጠው ሀሜስ ሮድሪጌዝን የማምጣት ፍላጎት ያላቸው አርሰናሎች ዝውውሩ ላይሳካ እንደሚችል መረጃዎች እያሳዩ ይገኛሉ ከትናንት ጀምሮ አርሰናሎች ኦዚልን ለባየርን ሙኒክ ሰተው ሀሜስን በውሰት መውሰድ ቢፈልጉም በዚህ የዝውውር መስኮት ልጁ ባየርን ሙኒክን መልቀቅ እንደማይፈልግ ተነግሩዋል
እንደ ስካይ ኢታሊያ ዘገባ ከሆነ ባርሴሎናዎች ኬቨን ፕሪንስ ቡአቴንግን ከሳሱሎ ለማዘዋወር ተስማምተዋል።ጋናዊው ተጨዋች በካምፕኑ የስድስት ወር ውል ፈርሟል።
አልቫሮ ሞራታ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ማድሪድ ከተማ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ወተዋል
ቼልሲ ከሂግዌይን በተጨማሪ ብራዚላዊውን ፊሊፔ ኮቲንሆን ለማስፈረም እንደሚፈልግ ተነግሩዋል ቼልሲዎችም ከባርሴሎና ሰዎች ጋር ንግግር መጀመራቸውም ታውቋል ቸልሲ ለልጁ እስከ 100ሚፓ መክፈል ፍላጎት አላቸው
የጉዳት ዜና በቅዳሜው ምሽት የለንደን ደርቢ ጨዋታ ጉዳት የደረሰበት ሄክቶር ቤላሪን በዚህ የውድድር አመት ወደ ሜዳ እንደማይመለስ ተነግሩዋል
ባርሴሎና ሌጋኜስን ሲገጥሙ ጉዳት የደረሰበት ኦስማን ዴምቤሌ ለሁለት ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ ይፋ አድርጉዋል ዴምቤሌ ባርሳ በኮፓ ዴላሬ ከሲቪያ ጋ በሚያደርጋቸው ደርሶ መልስ ጨዋታ እንዲሁም በላሊጋው ከቫሌንሲያ እና ከጄሮና ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ያመልጡታል
Sunday, January 20, 2019
የዕሁድ አመሻሽ ስፖርታዊ ዜናዎች
ከዩናይትድ ከተባረሩ ቡሀላ በዚህ ሳምንት ወደ ስራ ተመልሰው በቤይን ስፖርት ትንተና በመስጠት ላይ የሚገኙት ሞሪንሆ ከዩናይትድ ከተባረሩ ቡሀላ ሶስት ትላልቅ ስራዎች መተውልኝ ሶስቱንም ውድቅ አድርጌያለው ብለዋል
የጁቬንቱሱ አጥቂ ጎንዛሎ ሂጉዌን በሚቀጥለው ሳምንት ሙሉ ለሙሉ ዝውውሩን ያጠናቅቃል ሂግዌን ይህ የውድድር አመት እስኪጠናቀቅ ድረስ ቸልሲን በውሰት ይቀላቀላል በፕርሪሚየር ሊጉም ቶፕ 5 ተከፋዮች ከሚባሉት ውስጥ ይካተታል በሳምንት በሚያገኘው £270,000- ሳምንታዊ ደሞዝ ይከፈለዋል በቸልሲ
ዩናይዶች አሠልጣኝ ማፈላለጉን አሁንም ተያይዘውታል ምንም እንኳን ሶልሻየር አስደናቂ ስራ እየሠራ ቢገኝም በቋሚ አሠልጣኝነት ይቀጥላል ተብሎ አይታሰብም በመሆኑም የቶተንሃሙን ማውሪሲዎ ፖቼቲኖን ለማምጣት ዩናይትድ ሙከራ በማድረግ ላይ ይገኛል
ቨርጅል ቫንዳይክ ከቀድሞ የሊቨርፑል አሰልጣኝ ኬኒ ዳግሊሽ ጋር ቶሎ ቶሎ እንደሚደዋወል ተናገረ ስልካቸውን ሰተውኛል ያለችግር እደውላለው ብሏል ስለቡድኑ ሙሉ ነገር በየጊዜው አሳውቃቸዋለው እሳቸውን ማግኘት ባለብኝ ሰአትም አግኝቼ አወራቸዋለው ብሏል
በሪያል ማድሪድ የአንድ አመት ተኩል ኮንትራት የሚቀረው ሉካ ሞድሪች በማድሪድ ብዙ አመት መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሩዋል ሲቪያን ባሸነፉበት ምሽት ወሳኙዋን ጎል ያስቆጠረው ሞድሪች ከተለያዩ ክለቦች ጋር በተደጋጋሚ ስሙ ቢነሳም እሱ ግን ምርጫው ማድሪድ እንደሆነና መልቀቅም እንደማያስብ ተናግሩዋል
የኢንተር ሚላኑ CEO ማውሮ ኢካርዲ ከክለቡ ጋር እንደማይለያይ ተናግረዋል አሁን እስከ 2021 የሚያቆይ ኮንትራት አለው ከዚም ቡሀላ በሳንሴሮ ረጅም አመት እንደሚቆይ ለፈላጊ ክለቦቹ በይፋ አረጋግጠዋል
ወደ ሪያል ማድሪድ ሊሄድ ከጫፍ ደርሱዋል ቢባልም ዩናይትዶች አሁንም ብራዚላዊውን የፖርቶ ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው መረጃዎች አሳይተዋል
ኮሪዮ ዴሎ እስፖርት ባወጣው መረጃ ኤሲ ሚላን ኦዚልን በውሰት እንዲወስድ ቀርቦለት የነበረውን ጥያቄ ማልዲኒ ተቀብሎት ተጫዋቾች በመሸጥ ለኦዚል ቦታ ለማስለቀቅ ዝግጁ የነበረ ቢሆንም አሁን በሚላን የሚገኙትየቀድሞ የመድፈኞቹ አለቃ ጋዚዲስ ከ 25 አመት በላይ የሆነ ተጫዋች አንፈልግም ብለው ጥያቄውን ውድቅ አድርገውታል
በቢቲ ስፖርት በተንታኝነት እየሰራ የሚገኘው የቀድሞ የዩናይትድ ኮከብ ፖል ስኮልስ ወደ ልጅነት ክለቡ ኦልድሀም አሰልጣኝ ለመሆን ተቃርቧል
ባጅዮ በካሊፎርኒያ ሰማይ ስር
ፅሁፉ የጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ነው
Moments:
ባጅዮ በካሊፎርኒያ ሰማይ ስር
…በመልበሻ ቤት ውስጥ ከቡድን ጓደኞቹ ተነጥሎ ተቀመጠ። እንደፈረስ ጭራ
ወደ ኋላ የተዘረጋው ፀጉሩ ጀርባው ላይ እንደተጋደመ፣ ጭንቅላቱን በእጆቹ
መዳፎች ላይ አሳርፎ በዝምታ ቆየ። ጓደኞቹ ምን እያደረገ እንደሆነ
አልገባቸውም። ጭንቀት ይሆን? ወይስ ፀሎት እያደረሰ ነው? እርግጠኛ መልስ
ያለው አልነበረም።
ከ1994ቱ የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ በኋላ ነበር። ሮቤርቶ ባጅዮ ቡልጋሪያ
ላይ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ ሃገሩን ለፍፃሜ ቢያደርሳትም እንደ ድል ነሺ ሳተና
በኩራት አልተኮፈሰም። በውድድሩ ያስቆጠራቸው አምስት ጎሎች የአሪጎ ሳኪን
ቡድን ለዋንጫው ሽሚያ ያድርሰው እንጂ የባጅዮ ደስታ ሞልቶ አልፈሰሰም።
ጎዶሎ ነው። ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲቃረብ የደረሰበት ጉዳት በፍፃሜው ፍልሚያ
ላይ ተሳታፊ ይሁን ወይም አይሁን እርግጠኛ እንዳይሆን ሳንካ ፈጠረበት።
ያለመሰለፍ ዕድሉ ሰፊ ሆነ።
በካቶሊካዊት ክርስትና እምነት ተከታዮች የተሞላው መልበሻ ቤት 10 ቁጥራቸው
ፀሎት እያደረገ ስለመሆኑ ማወቅ አይችልም። ገና ከአፍላነት ዕድሜው ጀምሮ
የቡድሂዝም ተከታይ ሆኗልና የፀሎት ስርዓቱ ከክርስትናው ጋር ለየቅል ነው።
ማቀርቀሩ ፀሎት ይሁን ብስጭት ጓደኞቹ ያላወቁት ለዚህ ነበር።
የባጅዮ ድርጊት ፀሎትም ይሁን ጭንቀት የሃሳቡ ማዕከል የፍፃሜው ጨዋታ
ነው። ጉዳትና የተጫዋቾች ቅጣት ያሳሰባት የባጅዮ ጣልያን ከብራዚል ጋር
ትጫወታለች። በካሳዴና፣ ካሊፎርኒያ፣ ሮዝ ቦውል ስታዲየም፣ ጁላይ 17 ቀን
1994።
… ቡልጋሪያን ያሸነፉት በኒውዮርክ ነበር። ፍፃሜው በሩቁ ካሊፎርኒያ ግዛት
መሆኑ ጣልያናዊያኑን አላስደሰተም። የስድስት ሰዓት የአውሮፕን ጉዞ ማድረግ
ግዴታቸው ሆነ። የብራዚል ቡድን ደግሞ ግማሽ ፍፃሜውን ያከናወነው እዚያው
ነው። የጉዞ ድካም የለበትም። ባጅዮ ደግሞ ከጉዞ ድካምም ባለፈ የጭን ጅማት
መሳሳብ አሳስቦታል።
በአንድ የባንግላዴሽ የቡድሂዝም ቤተመቅደስ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቡድሃ
መነኮሳት ባጅዮ ብቁ ሆኖ ሜዳ እንዲገባ የህብረት ፀሎት አደረጉለት። ከዓለም
ዋንጫው በፊት መነኮሳቱ ጣልያን ድረስ ተጉዘው ባጅዮን በጎበኙበት ጊዜ ፀሎቱ
የተደረገበት ቤተመቅደስ የሚታደስበትን ወጪ ሸፍኖላቸው ነበር።
ሁለት የማገገሚያ ቀናትን ብቻ ቢያሳልፍም የባጅዮ ጭን በወፍራም ፋሻ
ተጠቅልሎ ብራዚልን ሊፋለም ገባ።
መደበኛውም ሆነ ጭማሪው ሰዓት አሸናፊውን መለየት አላስቻለም። መለያ ምት
ግድ ሆነ።
ብራዚላዊያን የዓለም ሻምፒዮን መባል ናፍቋቸዋል። ክብሩን ካገኙ 24 ዓመታት
ተቆጥረዋል። አዲሱ ትውልድ በአባቶቹ ሲነገረው የኖረውን የድል ታሪክ ሊኖረው
ቋምጧል። ጣልያን ደግሞ በዚህ ትውልድ ህልም መንገድ ላይ ቆማለች።
ወቅቱ ለጣልያን እግር ኳስ የኃያልነት ዘመን ነበር። የዓለማችን ሶስቱ ውድ
ተጫዋቾች የሚጫወቱት በሴሪ አ ነው። ጂያንሉዊጂ ሌንቲኒ፣ ዣን ፒየር ፓፐ እና
ጂያንሉካ ቪያሊ። በ1994 ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ የፋቢዮ ካፔሎ ኤሲ ሚላን
የዮሃን ክራይፍን ባርሴሎና 4-0 ረምርሞ አውሮፓዊ ዘውዱን ደፍቷል። እናም
ጣልያን ለብራዚል ከባድ ተጋጣሚ ነበረች።
…ባጅዮ ወሳኟን መለያ ምት ሊመታ መጣ። ኳሷን በነጥቧ ላይ አስቀመጠ።
የባጅዮ ኳስ ካልተቆጠረች ከእነፔሌ ዘመን ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚል
የወርቁን ዋንጫ ይዛ ሃገሯ ትገባለች።
ሲንደረደር ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥኑ ወጣ። በእርጋታ ሊመታት ተዘጋጀ።
የብራዚል በረኛ ክላውዲዮ ታፋሬል በፍፁም ቅጣት ምት መሳሳትን ከማያውቅ
ኮከብ ጋር ተጋፈጠ። 94ሺህ ተመልካች በሮዝ ቦውል የመጨረሻዋን ቅፅበት
ሊመለከት አይኑን ባጅዮ ላይ ተከለ።
ሮጥ ብሎ ኳሷን መታት። ታፋሬል ወደ ግራው ለመውደቅ ቢሞክርም የባጅዮ ኳስ
ከግቡ አግዳሚ ርቃ ወደ ላይ በረረች። ብራዚላዊያን በድል መንፈስ ሲዋጡ
የጣልያናዊያን ተስፋ የማይገፈፍ ድቅድቅ ጨለማ ወረሰው። በስታዲየሙ
ብራዚላዊያን የድል ብስራቱን በጭፈራ አደመቁት። የሳኪ ልጆች ግን መንፈሳቸው
ተሰበረ። ባጅዮ ሁለት እጆቹን በሽንጡ ላይ እንዳሳረፈ ቆሞ አቀረቀረ።
ሮቢ መወደድን፣ መጠላትን፣ መደነቅን፣ መተቸትን፣ ልይህ ልይህ፣ አይንህን ላፈር
መባልን ያውቀዋል። ከፊዮሬንቲና ወደ ጁቬንትስ በዓለም ሪከርድ ዋጋ ሲዛወር
በፍሎረንስ ከተማ የጎዳና ላይ አመፅ ተቀስቅሶ ነበር። በወቅቱ የ1990 የዓለም
ዋንጫ ተቃርቦ ስለነበር አዙሪ በፍሎረንስ አቅራቢያ በሚገኘው ኮቬርቺያኖ
ማዕከል መዘጋጀት እንኳን አልቻለም። በአመፁ ምክንያት የዝግጅት ቦታውን
ለመቀየር ተገደደ። በ"ወይንጠጆቹ" ደጋፊዎች የተወደደውን ያህል ተጠላ።
በአሜሪካኑ የዓለም ዋንጫ ዘግይቶ ስኬቱን ቢጀምርም በአምስቱ ጎሎች መሬት
አይንካህ ተብሎ ሳለ፣ በፍፃሜው መለያ ምቱን ባለማስቆጠሩ ብቻ ገሸሽ
ተደረገ።
ባጅዮ የዓለም ዋንጫን አሳይቶ ከነሳት በኋላ ጣልያን ሃዘን ገባት። ከሽንፈቱ በኋላ
ምሽቱን ተጫዋቾች በጋራ ሊመገቡ ከየሆቴል ክፍላቸው ሲወጡ ሮቤርቶ ባጅዮ
አልተቀላቀላቸውም። በራሱ ክፍል ላይ ቆልፎ ብቻውን ተቀመጠ። ረጅሙን
የቁዘማ ጉዞም አጥብቆ ተያያዘው።
በቻርተር በረራ ሮም ሲደርሱ ባጅዮ በደበዘዘ ስሜት ከአውሮፕላኑ ወጣ።
"አየሩን ስስብ የጣልያንን ህዝብ ሃዘን በአፍንጫዬ ያስገባሁ ያህል ተሰማኝ"
በማለት ከአሜሪካ ይዞት የመጣው ጫና የሃገሩን ምድር ሲረግጥ
እንደተባባሰበት ተናገረ።
ከአንድ ወር በላይ ድብርቱ ተጫነው። እንቅልፉ ተዛባ። የውስጥ ሰላሙ ታወከ።
የጥፋተኛነቱ ስሜት ጎዳው። ከዚያም በኋላ ባጅዮ የቀድሞው ባጅዮን አልሆነም።
ከአንድ ዓመት በኋላ ማርቼሎ ሊፒ ለሚላን ሸጡት። በሚላን ብቃቱ አላመረቃም።
ቦሎኛ፣ ኢንተር፣ ብሬሺያ ተዟዙሮ ተጫወተ። ከኃያላኑ ይልቅ አነስ ባሉት ክለቦች
ውስጥ የተሻለ ተጫወተ።
በ2004 ከተጫዋችነት ዓለም ከተለየ በኋላ ባሎን ዶር የተሸለመበት ብቃቱ
ሳይሆን በጁላይ 17ቷ መለያ ምት ስህተቱ ይበልጥ ይታወስ ያዘ። እስከዚያች
ዕድለ ቢስ ዕለት ድረስ ፍፁም ቅጣት ምት ከባጅዮ ብዙ ጠንካራ ጎኖች አንዱ
ነበር። እጅግ በጣም አስፈላጊ በሆነበት ሰዓት ግን ጥንካሬው ከዳው። ቀን
ሲጥል ደግሞ ሰው ብቻ አይደለም፣ የገዛ ህሊናም አፅናኝ አይሆን!
ሮም ከደረሱ በኋላ ሳኪ ባጅዮን ተመለከቱት። አዩት፣ አያቸው። ከፍፃሜው ጨዋታ
በፊት ባሉት ቀናት ተጫዋቾቻቸውን ደጋግመው የጠየቁትን ጥያቄ ደገሙለት።
"ሮቢ እስቲ ወደ ላይ ተመልከት"
ባጅዮ ወደ ሰማዩ አየ።
"ከሰሞኑ የተለየ ነገር ይታይሃል?"
የ24 ዓመቱ ኮከብ ምንም የተለየ ነገር አላገኘም።
"በቃ! ይኸው ነው!" አሉት።
እውነት ነው! የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ላይ ወሳኟን መለያ ብትስትም፣ ሃገርህ
የዓለም ሻምፒዮን እንዳትሆን ያደረግከው አንተ ብትሆንም፣ የሃገርህን ዜጎች
ሃዘን ላይ ብትጥልም፣ ጀግንነትህ በአንዲት ምት ብቻ በጥፋተኝነት ቢቀየርም፣
የዓለም ፍፃሜ አይደለም። ህይወት ትቀጥላለች።

Saturday, January 19, 2019
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ከ"ቀይ ሰይጣንነት" ወደ "ነጭነት" የተቀየረባት ዕለት
ፅሁፉ የጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ነው
Moments:
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ
ከ"ቀይ ሰይጣንነት" ወደ "ነጭነት" የተቀየረባት ዕለት
…ረፋድ ላይ። በሊዝበን ከተማ አንድ የግል አውሮፕን ወደ ስፔን ለመብረር
ሞተሩን አስነሳ። በጉዞው መዳረሻ ማድሪድ ልዩ ዝግጅት ስላለ በታላቅ ጉጉት
ይጠበቃል።
በረራው በ20 ደቂቃ ቢዘገይም ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፣ 12 ወዳጆቹና የቤተሰቡ
አባላት በረራቸውን ወደ ሰሜን አቅጣጫ በማድረግ ጀመሩ።
በትሬሆን ደ አርዶዝ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ የወጣትነት ውበት የተደፋበት
ዘለግ ያለው ሮናልዶ ከአውሮፕላኗ ወጣ። የዳይመንድ ሎቲው ጆሮው ላይ
ያበራል። በጂንስ ሱሪና ቀይ ጃኬት ደምቋል። ከውስጥ የለበሰው የስፖንሰሩ
ናይኪ ምልክት ያረፈበት ነጭ ቲሸርቱ ይታያል። ፀጉሩ ባነሰ መጠን ተቆርጧል።
የአውሮፕላኑን ደረጃ እንደወረደ በስፔን ምድር ላይ የመጀመሪያውን አውቶግራፍ
ፈረመ፣ ፎቶዎች ተነሳ።
ዛሬ ሰርጉ ባይሆንም "ዓለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ!" ቢዘመርለት አያንሰውም። ወደ
ትልቁ ባለታሪክ ሪያል ማድሪድ የሚያደርገው ዝውውር ይፋ የሚሆንበት የደስታው
ቀን ነው። ሳንቲያጎ ቤርናቢዩም ሙሽራዋን በጉጉት ትጠባበቃለች።
በቤርናቢዩው የስነስርዓቱ "ካህን" ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ናቸው። የሪያል ማድሪዱ
አለቃ በዓለም የተጫዋቾች ክብረ ወሰን የማዴይራውን ልጅ በመጨረሻ
ከማንቸስተር ዩናይትድ እጅ ፈልቅቀው ወስደዋል። ይህን ጀብዳቸውን "እወቁልኝ"
የሚሉት ደግሞ በዚሁ ስነስርዓት ነው። ለባለትዳሩና ጎልማሳው ፔሬዝም ዕለቱ
ከሰርጋቸው ዕለት ደስታቸው ጋር የሚወዳደር ነበር።
…ጠባቂው አጅቦት ወደ ተዘጋጀለት መኪና መራው። መስታወቷ በጥቁር ልባድ
የተለበጠ ነጭ ኦዲ መኪና ተዘጋጅታለታለች። በኋለኛው ወንበር በማናጀሩ ዦርጌ
ሜንዴዝና በእህቱ ባል ዜ ታጅቦ ጉዞ ተጀመረ።
ሶስቱ ሰዎች በዦርጌ ስፓኒሽ ችሎታ እየቀለዱ፣ ሮናልዶም ረጋ፣ ዘና ብሎ ዋናውን
ጎዳና ሲያያዙ ጥቂት ሸለብ አደረገ።
ከፊርማው በፊት በተዘጋጀ ልዩ ክሊኒክ ለህክምና ምርመራ ቆሙ። ከ10 ቀናት
በፊት ሮናልዶ በፖርቱጋል ሙሉ ምርመራ ተደርጎለት ለዝውውሩ ብቁ መሆኑ
ተመስክሮለት ነበር። ሆኖም በማድሪድም እንደገናም ታየ። ክሊኒኩ ዘንድ ሲደርስ
በካሜራዎችና በመቅረፀ ድምፆች ተከቧል። ደጋፊዎችም በብዛት መጥተዋል።
አንዲት የ18 ዓመት ኮረዳ "ሮናልዶ እወድሃለሁ!" የሚል ጽሁፍ ይዛ ቆማለች።
ደም፣ ሽንት፣ ኢሲጂ፣ ኤኮካርዲዮግራም፣ ኤምአርአይ፣ የደረት ራጅ፣ የእግር፣
የእጅ ምርመራዎች ተደረጉለት። 30 ደቂቃ የፈጀው ምርመራ ሲያበቃ ጉዞ ወደ
ቤርናቢዩ ሆነ።
በመንገድ ላይ የትራፊክ መብራት ሲያቆማቸው ሁለት ወጣት ሴቶች ከየት መጡ
ሳይባል መኪናቸው አጠገብ እየጮሁ ቀረቡ።
"ክሪስቲያኖ! ክሪስቲያኖ!" ይላሉ።
ሮናልዶ የመኪናውን መስተዋት አውረዶ "አንሺ! አንሺ! ፎቶውን አንሺ!" ሲል
ከሁለቱ አንደኛዋን አበረታታት።
ፎቶ ተነሱ። ከዚያም እጁን አውጥቶ ጨበጣቸው።
"ትውውቁ ላይ እናይሃለን!" እያሉ ደስታቸውን እያጣጣሙ ተሰናበቱትና ጉዞ ወደ
ቤርናቢዩ ሆነ።
ነጯ ኦዲ ወደ ቤርናቢዩ መግቢያ ተጠጋች። ክሪስቲያኖ አሳንሰሩን ይዞ ወደ
ክለቡ ጽህፈት ቤት አመራ። ረጅሙ ስራ ገና አሁን ተጀመረ። በቅድሚያ የስፔን
ጋዜጦችን አሳዩት። በሁሉም የፊት ገፆች ላይ ምስሉ ወጥቷል። ከዚያ በስሙ
የታተመውን የመጀመሪያው ማሊያ ላይ ፊርማውን አኖረ። አንድ ሰዓት ባልሞላ
ጊዜ ውስጥ ይህን የመሰሉ ሺሆች የሮናልዶ ማሊያዎች በክለቡ ሱቅ
ተቸብችበዋል።
የሪያል ማድሪድ የወቅቱ ጄኔራል ማናጀር ሆርጌ ቫልዳኖ የዕለቱን ፕሮግራሞች
ይዘት በቅደም ተከተል አብራራለት። በቢሮው ሰፊ መስኮት በኩል ሜዳው
ይታያል። ንግግር የሚያያደርግበት ስቴጅ እየተዘጋጀ ነው። የዝግጅቱ ሽር ጉድ
ቀጥሏል።
ከስነስርዓቱ በፊት ሮናልዶ ከሪያል ማድሪድ ቲቪ ጋር ቃለምልልስ አለበት።
በግራጫ ሙሉ ልብስ ሩብ ሰዓት በስፓኒሽ፣ ሩብ ሰዓት በእንግሊዝኛ
ቃለምልልሱን ከፈፀመ በኋላ ወደ ፕሬዚዳንቱ አመራ።
ፔሬዝ ወደ ስታዲየሙ ንጉሳዊ ትሪቡን ወሰዱት።
"ክቡር ፕሬዚዳንት፣ ዛሬ ጨዋታ አለ አንዴ?" ሮናልዶ ቀለደ። ፔሬዝ በፈገግታ
ብቻ መልስ ሰጡት። ሰውየው የዓለማችንን ኮከብ በማግኘታቸው ጮቤ
ረግጠዋል። በቦርዱ ጽህፈት ቤት በሞላላው ጠረጴዛ ጎን ከፔሬዝ ጎን ተቀምጦ፣
በአራት ዶሴዎች ላይ የኮንትራት ፊርማውን አኖረ። ፔሬዝም ተመሳሳዩን አደረጉ።
በክፍሉ ውስጥ የቀድሞ ዝነኞች አልፍሬዶ ዲ ስቴፋኖ፣ ዩዜቢዮ እና ሌሎች
ዳይሬክተሮች "ቀዩ ሰይጣን" ሮናልዶ በይፋ "ነጭ" ሲሆን ተመለከቱት።
ሁሉም አጨበጨበ። የፎቶ ካሜራዎች ታሪካዊ ምስሎችን ለማስቀረት
ተንቀጫቀጩ። ፔሬዝ የተፈረመበትን ብዕር፣ የቤርናቢዩን ሞዴል እና አዲስ ሰዓት
በስጦታ መልክ አበረከቱለት።
በመልበሻ ቤት በ8 ቁጥሩ ካካ እና በ10 ቁጥሩ ሽናይደር ማሊያዎች መካከል
የሮናልዶ 9 ቁጥር ተንጠልጥሎ ባለቤቱን ይጠብቀዋል። ክሪስቲያኖ ሙሉ
ልብሱን አውልቆ ነጩን ማሊያ አጠለቀው።
"ነጭ ያምርብሃል ባክህ?!" ፔሬዝ በተራቸው ቀለዱ።
ሮናልዶም ትጥቁን አሳምሮ ወደ መስተዋቱ ቀረበ። ሁሉ ነገር ያምራል። ፎቶዎችን
ተነሳ። በቻይንኛ፣ በጃፓንኛ፣ በዓረብኛ ስሙ በተፃፈባቸው ማሊያዎች ፎቶዎችን
መነሳቱን ቀጠለበት።
የቢሮው ስነስርዓት ሁሉ ካበቃ በኋላ በሜዳው ዝግጅት ላይ ፔሬዝ ስሙን
እስኪያስተዋውቁ ድረስ እንዲታገስና፣ ስሙም ሲጠራ እንዲወጣ ተነገረው።
ትዕዛዙም ተቀብሎ ስሙን መጠባበቅ ጀመረ።
የተጠበቀችው አጓጊ ሰዓት ደረሰች።
"ክሪስቲያኖ ሮናልዶ!" ሲባል ፖርቱጋላዊው ኮከብ ከቤርናቢዩ ጉያ ወደ ሜዳው
ወጣ። ያን ጊዜ ስታዲየሙ በጩኸት ተደበላለቀ።
"Si, Si, si ...Cristiano ya este aqui," ተዘመረ።
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ዶሳንቶስ አቪዬሮ ገና ሳይጫወት ክብረ ወሰን ሰበረ።
በ1984 ኔፕልስ ዲዬጎ ማራዶናን ስትቀበል ሳን ፓውሎ በ65ሺ ተመልካች
ተሞልቶ ነበር። ያቺ ቀን በእግር ኳሱ ዓለም በአዲስ ፈራሚ ትውውቅ ላይ ከፍተኛ
የተመልካች ቁጥር የተመዘገበባት ነበረች። ሮናልዲንሆ በኤሲ ሚላን ሲተዋወቅ
40ሺህ፣ ለካካ በቤርናቢዩ 50ሺህ ተመልካች ተገኝቷል። ሮናልዶ ግን የሁሉንም
አስከነዳ። በአንድ ወገን በእድሳት ላይ የነበረው ቤርናቢዩ ያለጨዋታ፣ ለእንኳን
ደህና መጣህ ስነስርዓት ብቻ 80ሺህ ተመልካች አስተናገደ። በዚያ ውብ የበጋ
ዕለት 5ሺህ የሚጠጉ ማድሪዳዊያን ቲኬት አለቀ ተብለው በአቀባበሉ ላይ
ባለመገኘታቸው አዘኑ። ጁላይ 9 ቀን 2009…።

የዕሁድ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች
የጁቬንትሱ አጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን በቀጣዩ ሳምንት ቼልሲን የሚቀላቀል ይሆናል።የ31 አመቱ አጥቂ ሰማያዊዎቹን የሚቀላቀላው በውሰት ሲሆን እስከ ሲዝኑ መጨረሻም በስታንፎርድ ብሪጅ የሚቆይ ይሆናል።አንድ ስታር ዘገባ ያሳለፍነውን ሲዝን በኤሲ ሚላን ያሳለፈው ሂጎይን በቼልሲ በሳምንት £270,000 የሚከፈለው ሲሆን ይህም ከፕሪምየር ሊጉ አምስት ከፍተኛ ተከፋዮች ዝርዝር ውስጥ ያስገባዋል።
(Star on Sunday)
ቼልሲ £100M የሚገመተውን የቀድሞው የሊቨርፑል አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ለማዘዋወር ለባርሴሎና ጥያቄ አቅርቧል።የ26 አመቱ ብራዚላዊ ሊቨርፑልም በድጋሚ ማስፈረም ይፈልጋል።
(Express)
ሪያል ማድሪድ የቼልሲውን ቤልጄሚያዊ አጥቂ ኤድን ሃዛርድ ከ£100ሚ ባነሰ ዋጋ የማስፈረም ተስፋ እንዳላቸው አስበዋል።ሃዛርድ በቼልሲ ያለው ኮንትራት በፈረንጆቹ ጁን 2020 ነው የሚጠናቀቀው።
(Marca)
ኤቨርተን በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ የሚገኘውን የቼልሲውን ቤልጄሚያዊ አጥቂ ሚቺ ባትሹዋይ ለማዘዋወር ለሰማያዊዎቹ £40ሚ አቅርቧል።
(Sun)
የፓሪሰን ዤርመኑ አጥቂ ኪልያን ምባፔ ከአንድ የፈረንሳይ ሚድያ ጋር በነበረው ቆይታ ለወደፊት ሪያል ማድሪድ እጫወታለው ብሎ እንደሚያስብ ተናገረ።ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ የተጨዋቹ ቀንድኛ አድናቂ እንደሆኑ ይታወቃል።
(AS, via Mirror)
የቶተንሃሙ አጥቂ ማውሪስዮ ፖቼቲንሆ ወሳኝ ተጨዋቻቸውን ሃሪ ኬን በጉዳት ማጣታቸውን ተከትሎ የሱን ቦታ ለመተካት ተጨዋች ከማስፈረም ይልቅ ከአካዳሚ ወጣት ተጨዋች ሊያመጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
(London Evening Standard)
የባርሴሎናው አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ወደ አርሰናል የሚያረገውን ዝውውር በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚጨርስ ይጠበቃል።
(Star)
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከዩናይትድ ከመባረራቸው በፊት ገና ሲዝኑ ከመጀመሩ በፊት የሊጉ ሻምፒዮን እንደማይሆኑ አስበው እንደነበር ተናግረዋል።ሞሪንሆ ከዩናይትድ ከወጡ በኋላ ከሶስት ክለቦች ጥያቄ እንደቀረበላቸውም ተናግረዋል፡፡
(Manchester Evening News)

ዲንሆ የማይረሳት ምሽት
ጽሁፉ የጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ነው
ዲንሆ የማይረሳት ምሽት
!
....ሳንቲያጎ ቤርናቢዩ ለኤልክላሲኮ በሮቹን ከፈተ። በላ ሊጋው ሰንጠረዥ ላይ
ሪያል ማድሪድ ከባርሴሎና በአንድ ነጥብ ይብለጥ እንጂ በዚያ ሰሞን ነጮቹ
በጉዳትና በብቃት መውረድ ወዛቸው ተሟጦ ተቸግረዋል። ጋላክቲኮስ
እንደስማቸው መሆን አቅቷቸዋል።
ከጨዋታው ቀድሞ ሮናልዲንሆ ውጥረቱን ለማቀዝቀዝ "ሪያል ማድሪድን ማሸነፍ
ሊጉን ማሸነፍ አይደለም። ያው እንደማንኛውም ጨዋታ ሶስት ነጥብ
የምታገኝበት ጨዋታ ነው" በማለት ቀለል ያለ መግለጫ ሰጠ።
ጨዋታው ግን ዲንሆ እንዳቀለለው አልቀለለም። ከጨዋታም በላይ ነበር። ሶስቱ
አጥቂዎች ሳሙኤል ኤቶ፣ ሊዮኔል ሜሲና ሮናልዲንሆ ለባርሴሎና በኃያሉ
ተፎካካሪው ፊት አይበገሬ ግርማ ቸሩት። ኤቶ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጠረ።
ሮናልዲሆ ከጥልቅ ቦታዎች እየተነሳ ጉልበትና የቴክኒክ ልህቀትን አዋህዶ
በሚያስደንቅ አጨራረስ ሁለት ጎሎችን በስሙ አስመዘገበ። ሪያል 0፣ ባርሳ 3።
በዚያች ምሽት ዲንሆ እንደ እንዝርት ሾሮ የባርሴሎናን የብቃት መዘውር
በቴክኒካዊ ብቃቱ አዳወረው። ማድሪዳዊያን በገዛ ጓሯቸው ለማይወዱት
ተፎካካሪያቸው ብርቱ ክንድ እጅ ሰጡ። ሮናልዲንሆና ጓደኞቹ መራራውን የሽንፈት
ፅዋ አስጨለጧቸው። የባርሳ ልጆች ለስህተት ቦታ አልነበራቸውም። ብቃታቸው
ወዳጅን ቀርቶ ባላንጣን የሚያሳምንና ለተሸናፊው ሰበብ የማይመች ነበር። የኑ
ካምፑ ንጉሥ በኃያሉ ፍልሚያ ሜዳ ትልቅነቱን አሳይቶ በቤርናቢዩም ነገሰበት።
ይህ ለሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች ከአእምሮ በላይ ሆነባቸው። ከተቀመጡበት
ተነስተው ለመራሩ ባላጋራቸው ተጫዋች አጨበጨቡ።
ጭብጨባው የፍፁማዊ አድናቆት አንጂ የምፀት አልነበረም። ባትወደውም
ከውስጥ የመነጨ የእግር ኳስ መንፈስ የሚያስገድድህ የእውነተኛ ስፖርት
ቤተሰብነት ስሜት ነበር። ከዚያ በፊት ማድሪዲስታስ ለሁለት የባርሳ ተጫዋቾች
ብቻ በአድናቆት አጨብጭበዋል። በፌብርዋሪ 1974 ባርሳ 5-0 ሲረታቸው
ለዮሃን ክራይፍ አድርገውታል። በጁን 1983 የዲዬጎ ማራዶና ብቃት አስገርሞ
ከመቀመጫቸው አስነስቶ አስጨብጭቧቸዋል። በዚያች ምሽት ደግሞ
ሮናልዲንሆ የክራይፍ/ማራዶና የክብር መዝገብ ውስጥ ተካተተ።
"መቼም አልረሳውም። በአንድ ተጫዋች ህይወት ውስጥ እንዲህ አይነቱ ነገር
ከዘመናት አንድ ጊዜ ብቻ የሚያጋጥም ነው" በማለት ሮናልዲንሆ በሪያል
ደጋፊዎች አፀፋ የተሰማውን ደስታ ገለፀ።
ለሪያል ማድሪድ ጋላክቲኮስ የራሳቸው ደጋፊዎች አድናቆታቸውን ነፍገዋቸው፣
ክብራቸውን ለተጋጣሚዎቻቸው ሲሰጡ መመልከት የሚያሳፍር ነበር። ለደካማው
ጥረታቸው ማድሪዳዊያኑ እንዲህ አድርገው ተጫዋቾቻቸውን ቀጧቸው።
በገፅታው አስቀያሚነት ምክንያት ሮናልዲንሆን ማስፈረም "ለሪያል ማድሪድ
ብራንድ ውድቀትን ያስከትላል" ያሉት የቤርናቢዩ ባለስልጣናት በሞኛሞኙ
አስተሳሰባቸው ተጸጸቱበት። ምልመላ በደም ግባት ሳይሆን በጨዋታ ብቃት ብቻ
መሆን እንዳለበት ታሪክ ከክፉ ምክር ጋር አስተማራቸው።
ሽንፈቱ ለቫንደርሌይ ሉክሰምቡርጎ ዘርሮ ከውድድር ውጭ የሚያደርግ ብርቱ
ቡጢ ያህል ነበር። ከዚያ በኋላ የብራዚላዊው አሰልጣኝ የብቃት ቆሌ ተገፎ ቀረ።
አላገገሙም። የሮናልዲንሆ ምትሃት ሪያልን አንገት አስደፍቶ ብቻ አልቀረም።
ብዙም ሳይቆይ ሉክሰምቡርጎ የስንብት ደብዳቤ ደረሳቸው። ጥቂት ወራት ብቻ
እንደተቆጠሩ በፌብርዋሪ 2006 ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ የጋላክቲኮስ ፖሊሲያቸውን
ጥለው በፈቃዳቸው ከፕሬዚዳንትነታቸው ተነሱ።
በዚያ ቤት ለቅሶ ሲሆን በሮናልዲንሆ ዘንድ ደስታው በዛ። 2005 ፍፁም ያማረ
ዘመን ሆኖ ተገባደደለት። ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የፊፋን ኮከብነት ክብር
ተጎናፀፈ። ለመጀመሪያ ጊዜም ባሎን ዶርን አሸነፈ። የወርልድ ሶከር እና የኦንዝ
መፅሔቶችም "አንተ የዓለም ኮከብ ተጫዋች ነህ" ብለው ሸለሙት። ዘመኑም
የሮናልዲንሆ ወርቃማው ዘመን ሆኖ በታሪክ ማህደር ላይ ተፃፈ። እኛ፣ የእግር
ኳስ አፍቃሪዎችም… ማንም ሳይነግረን፣ ከዓለም እግር ኳስ ኃያላን ነገሥታት
ተርታ አሰለፍነው። አልተሳሳትንም ነበር።

የቅዳሜ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
ሪያል ማድሪድ አሁንም ኤሪክሰንን እና ሀዛርድን ለማስፈረም ማሰቡን ማርካ አስነብቧል በተለይ ሀዛርድ ከቸልሲ የቀረበለትን የውል ማራዘሚያ አልፈርምም ማለቱ በክረምቱ ማድሪድን ለመቀላቀል ፍላጎት ስላለው ነው ተብሏል እንዲሁም 18 ኮንትራት የቀረውንም ኤሪክሰንን ማስፈረም ይፈልጋሉ
አርሰናሎች ፍራንቺስኮ ቲርካቲርናኮኦ የሚባል የፖርቱጋል ወጣት ተጨዋችን ከብራጋ ለማምጣት መልማዮቻቸውን ልከዋል ልጁ የአርሰናል የረጅም ጊዜ እቅድ እንደሆነም ተነግሯል ልጁ ከአርሰናል ውጭ በጁቬንቱስም እየተፈለገ ይገኛል
ቼልሲዎች ሊዮናርዶ ፓራቴስ የተባለውን የዜኒቱን አማካይ ለማስፈረም ቼልሲዎች ተቃርበዋል ፋብሪጋስ ክለቡን ከለቀቀ ቡሀላ የሱን ተተኪ በመፈለግ ላይ የሚገኙት ቸልሲዎች ከብዙ ድርድር ቡሀላ ዝውውሩ ለመሳካት ከጫፍ ደርሱዋል
ሜሱት ኦዚል ክለቡን ብትለቅ ይሻላል ብለውት እንደነበር ኡናይ ኤምሪ ለክለቡ ቅርብ የሆነው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ዴቪድ ኦርነስቴን ተናገረ
ሊቨርፑል እና ቼልሲ የላዚዮውን አጥቂ ቺሮ ኢሞቢሌን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው ተብሏል የርገን ክሎፕ እንደውም እሁድ ከናፖሊ ላዚዮ የሚያደርጉትን ጨዋታ መልማዮችን እንደሚልኩ እየተነገረ ይገኛል
አንቶኒዮ ሳናብሪያን በቶተንሀም እየተኘለገ ይገኛል ፖቸቲንሆ በጉዳት ለብዙ ሳምንታት ከሜዳ የሚርቀውን ሀሪ ኬንን ለመተካት ፍላጎታቸው እሱ ነው ተብሏል
ሊቨርፑል ለቤነፊካው የ 19 አመት ታዳጊ ጆአኦ ፌሊክስ ሚዩ61 አቅርቦ ውድቅ እንደተደረገበት ዘገባዎች እያመላከቱ ነው ሊቨርፑል ወደ ሀያልነቱ እየተመለሰ መሆኑን ተከትሎ የበለጠ ለመጠንከር ዝውውሮች ላይ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል
በማድሪድና ጁቬንቱስ እየተፈለገ ሚገኘው የዩናይትድ ወጣት አጥቂ
ራሽፎርድ በክለቡ መቆየት እንደሚፈልግ እየተዘገበ ይገኛል ዩናይትድም ደሞዙን እጥፍ በማረግ አዲስ የረጅም አመት ኮንትራት ለማስፈረም ፍላጎት አለው
ሪያል ማድሪድ የፖርቶውን የመሀል ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል ከልጁ ወኪል ዊሊያኖ ቤርቶሎጂ ጋር ተነጋግረዋል ማድሪዶች ለተከላካዩ እስከ 50ሚ.ዩ ለመክፈል ፍቃደኛነታቸውን አሳይተዋል
Friday, January 18, 2019
የቅዳሜ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች
ሊቨርፑል ፖርቱጋላዊውን የ19 አመት የአጥቂ አማካይ ጃኦ ፌሊክስ ለማዘዋወር £61M ቢያቀርብም ቤኔፊካ ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።
(Correio da Manha - in Portuguese)
የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ዤርደን ክሎፕ ከ12 ወራት በፊት ለባርሴሎና በ£142M የሸጡትን ብራዚላዊውን አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ከተቻለ በድጋሚ ወደ አንፊልድ መመለስ ይፈልጋሉ።ኩቲንሆ ህይወት በካታላኑ ክለብ እምብዛም ምቹ እንዳልሆነችለት ይነገራል።
(Liverpool Echo)
ቡድኑን በማጠናከር ላይ የሚገኘው የሞናኮው አሰልጣኝ ቴሪ ሄንሪ የማንቸስተር ዩናይትዱን የ31 አመት አማካይ ማርዋን ፌላኒ በውሰት መውሰድ ይፈልጋል።
(RMC - in French)
ንብረተነቱ የጁቬንትስ የሆነው አርጀንቲናዊ አጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን ቼልሲን ለመቀላቀል ወደ ለንደን እንደሚያመራ ተነግሯል ፥ ሰን እንደዘገበው ከሆን በቀጣይ ሳምንት ሃሙስ በካራባኦ ካፕ ሰማያዊዎቹ ከ ቶተንሃም ላለባቸው ጭዋታ ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል።
(Sun)
ባየርን ሙኒክ ለቼልሲው የ18 አመት እንግሊዛዊ ዊንገር ካሉም ሂውደሰን-ኦዱው ሳምንታዊ 85,000k አቅርቧል።
(Sun)
ፈረንሳዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ አንቶኒ ማርሻል በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ለተጨማሪ አምስት አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ሊፈርም እንደሆነ ተነግሯል።የ23 አመቱ አጥቂ በአዲሱ አሰልጣኝ ኦሊጉናር ሶልሻየር ደስተኛ መሆኑም ነው የተነገረው።
(Sky Sports)
ኤቨርተን ቤልጄሚያዊውን የቼልሲ አጥቂ ሚቺ ባትሹዋይ የማዘዋወር ፍላጎት ያለው ሲሆን ለዝውውሩም £40M አሰናድቷል።የ25 አመቱ አጥቂ በውሰት በስፔኑ ክለብ ቫሌንሲያ ከቆየ በኋላ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ መመለሱ ይታወቃል።
(Sun)
በተደጋጋሚ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ እየተያያዘ የሚገኘው ማርኮ አርናቶቪች
ከዌስትሀም መውጫ በር ላይ ቆሟል ከቸልሲ እንዲሁም ከቻይና ክለቦች ለክለቡ
ጥያቄ ቢቀርብም ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል አሁን ላይ የልጁ ወኪል ክለቡ
ላይ ጫና በማሳደራቸው ለመልቀቅ ተዘጋጅተዋል አሰልጣኙ ፔሌግሪኒም
በዝውውሩ ጉዳይ አስተያየት ሰተዋል ትክክለኛ ገንዘብ የሚመጣ ከሆነ
እንሸጠዋለን ብለዋል ዌስትሀም ለዝውውሩ ከ40ሚፓ ይፈልጋሉ።
(Goal)

የዕለተ አርብ ስፖርታዊ ዜናዎች
አርሰናል እና ዴኒስ ሱዋሬዝ ለመገናኘት ከጫፍ ደርሰዋል እንደ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘገባ አርሰናል ይህን የ25 አመት እስከ ዚህ የውድድር አመት መጨረሻ በውሰት ይወስደዋል ለዝውውሩም 2ሚዩ ይከፍላል ለውሰት ውሉ ባርሴሎና ይሄ ተጨዋች በቋሚነት እንዲፈርም ስለሚፈልጉ በቀጣይ አርሰናል 20ሚዩ ከፍሎ መውሰድ ይችላል
.
በተደጋጋሚ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ እየተያያዘ የሚገኘው ማርኮ አርናቶቪች ከዌስትሀም መውጫ በር ላይ ቆሟል ከቸልሲ እንዲሁም ከቻይና ክለቦች ለክለቡ ጥያቄ ቢቀርብም ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል አሁን ላይ የልጁ ወኪል ክለቡ ላይ ጫና በማሳደራቸው ለመልቀቅ ተዘጋጅተዋል አሰልጣኙ ፔሌግሪኒም በዝውውሩ ጉዳይ አስተያየት ሰተዋል ትክክለኛ ገንዘብ የሚመጣ ከሆነ እንሸጠዋለን ብለዋል ዌስትሀም ለዝውውሩ ከ40ሚፓ ይፈልጋሉ
.
ከሎሳንጀለስ ጋላክሲ ጋር ከተለያየ ቡሀላ ክለብ አልባ የነበረው የቀድሞ የአርሰናል እና የቸልሲ ተጨዋች አሽሊ ኮል ወደ ቀድሞ አጋሩ ክለብ ደርቢ ካውንቲ ሊያመራ እንደሚችል መረጃዎች አሳይተዋል
.
የዩናይትድ ተጨዋቾች ሶልሻየር በክለቡ ቋሚ እንዲሆን ፍላጎት አላቸው ተብሏል እንደ ዴይሊ ሜይሊ ዘገባ ከሆነ እስከዚ አመት መጨረሻ ኮንትራቱ ቢቆይም ሁሉም ተጨዋቾች ድጋፋቸውን ለሶልሻየር አሳይተዋል አሁን ላይ ዩናይትድ ተቀዳሚ ምርጫው አሁንም ፖቸቲንሆ ነው ነገር ግን የሱ ማይሳካ ከሆነ ሶልሻየርን ለመቅጠር ፍላጎት አላቸው
.
ቸልሲ ካሉም ሁድሰንን ላለማጣት እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ እስከ 70ሺፓ ሳምንታዊ ደሞዝ ሊያሳድጉለት ቃል እንደገቡለት ሚያሳይ የተለያዩ መረጃዎች ወተዋል ልጁ ግን አሁንም በቸልሲ ውሉን ማደስ እንደማይፈልግ ተነግሯል ለ18 አመቱ ሁድሰን ባየርን ሙኒክ 35ሚፓ አቅርቧል
.
የሂግዌን ዝውውር ሙሉ ለሙሉ ወደ መጠናቀቁ ደርሷል ታማኝ የሚባሉ የእንግሊዝ ሚዲያዎች እንደተቀባበሉት ከሆነ ሂግዌን ዝውውሩን በ24 ሰአት ያጠናቅቃል ብለዋል ዛሬ ማምሻውን ወደ ለንደን መቶ ሜዲካሉን በማድረግ ዝውውሩን ያጠናቅቃል ለሀሙሱም የሊግ ካፕ የመልስ ጨዋታ እንደሚሰለፍ ተነግሯል
.
ባርሴሎና በጥር አልያም በክረምት ሁለት ወሳኝ የሚባሉ ተጨዋቾችን ማስፈረም ይፈልጋሉ በባርሳ የሚፈለጉት ተጨዋቾች ፍራንክ ዲዮንግ እና ክርስቲያን እስቱዋኒን ከአያክስ እና ከጄሮና ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል የባርሴሎናውም አሰልጣኝ ቫልቬርዴ አዳዲስ ተጨዋቾችን ማስፈረም እንፈልጋለን ግን ስለልጆች መናገር አልፈልግም ብለዋል
.
በጉዳት ምክንያት ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን ያጡት ቶተንሀሞች በውሰት ተጨዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል ከተለያዩ ተጨዋቾች ጋር ስማቸው እየተያያዘ ይገኛል አሁን ደሞ ከእንግሊዝ ሳይወጡ የሊቨርፑሉን ዲቮክ ኦሪጊን የአጭር ጊዜ መፍትሄ አድርገው ለማስፈረም ጥረት ጀምረዋል ተብሏል
Thursday, January 17, 2019
የዕለተ ሀሙስ ስፖርታዊ ዜናዎች
የሱዋሬዝ እድሜ መገፋት ተከትሎ ባርሴሎናዎች የተለያዩ አጥቂዎችን እየተመለከቱ ይገኛሉ ከሰሞኑ በተደጋጋሚ ከሰርቢያዊው አጥቂ ሉካ ዮቪች ጋር ስሙ እየተሳ ይገኛል አጥቂው በዘንድሮ የቡንደስሊጋ ውድድር 12 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል ባርሴሎናዎች የአያንትፍራንክፈርቱን አጥቂ የግላቸው ለማድረግ እንቅስቃሴም መጀመራቸውንም ዘገባው አስነብቧል
በክረምቱ ባርሴሎናን የተቀላቀለው ማልኮም ከባርሳ ለመልቀቅ ከጫፍ መድረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል በላሊጋው አንድ ጨዋታ ላይ ብቻ የተሰለፈውን ማልኮምን ለማስፈረም የተለያዩ የእንግሊዝ የጣሊያን እና የቻይና ክለቦች የልጁ ፈላጊ ሆነዋል
ቼልሲ እና ጁቬንቱስ በጎንዛሎ ሂግዌን የዝውውር ጉዳይ ላይ መስማማታቸው ታውቋል ተጨዋቹን እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ ለመውሰድ ነው የተስማሙት ውድድር አመቱ ሲጠናቀቅ ደሞ ለ12 ወራት የውሰት ውል የማራዘም መብት ይኖረዋል
የሀሜስ ሮድሪጌዝ ወደ አርሰናል መዘዋወር ዜና በሰፊው እየተነገረ ይገኛል ባየርኖች ይሄ አመት ሲጠናቀቅ በ37ሚፓ ማዘዋወር ይችላሉ ይሄንንም ተከትሎ የባይርን ሙኒኩ ስፖርት ዳይሬክተር ሀሰን ሰሊሀሚዚች አስተያየት ሰተዋል በሁለተኛው የውድድር አመት አጋማሽ ተጨዋቹ የሚያሳየውን አቅሙን ተመልክተን በአመቱ መጨረሻ እኖስናለን ሚል አስተያየት ሰተዋል
የቶተንሀሙ አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከ18 ወራት ቡሀላ ኮንትራቱ ይጠናቀቃል ይሄ የውድድር አመት ሲጠናቀቅ ኮንትራት የማይፈርም ከሆነ ቶተንሀም ሊሸጠው ይፈልጋል AS የተባለው የስፔን ጋዜጣ እንደዘገበው ይህንን ድንቅ ዴንማርካዊ ለማስፈረም ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ተፋጠዋል ተጨዋቹ ግን ወደ ሪያል ማድሪድ ማምራት ነው ፍላጎቱ ተብሏል
ወደ ጁቬንቱስ ማምራቱ እርግጥ ነው እየተባለ የተወራለት አሮን ራምሴ ዝውውሩን በትንሹም ቢሆን ቀዝቀዝ ሚያረገው ዜና ትናንት ተሰምቷል በጣሊያን ሱፐር ካፕ ሻምፒዮን የሆኑት የጁቬንቱስ አሰልጣኝ አሌግሪ ስለራምሴ ተጠይቀው ነበር ጋዜጠኛውም ራምሴን በጥር የዝውውር መስኮት የማስፈረም ፍላጎት አላቹ ተብለው ሲጠየቁ የአርሰናል ተጨዋች ነው አሁን ላይ ለማስፈረምም ጥረት እያደረግንም አደለም አሁን ባለን ስኳድ ደስተኛ ነኝ ብሏል
የቀድሞ የቸልሲ ግብ ጠባቂ ፒተር ቼክ ከትናንት በስቲያ በዚህ አመት ጓንቱን እንደሚሰቅል አሳውቆ ነበር እናም ቸልሲዎች የቀድሞ ልጃቸውን በዚህ አመት መጨረሻ ወደ ቸልሲ ለመመለስ አስበዋል ቸልሲዎችም ከተጨዋቹ ጋ ንግግር ጀምረዋል ቸልሲም ቼክን የክለቡን አካዳሚዎችን ወይም ወጣቶችን እንዲያሰለጥንላቸው ካሎነም የክለቡ አምባሳደር አርጎ መሾም እንደሚፈልጉ ተነግሯል
Wednesday, January 16, 2019
የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
ፓውሊንሆ ወደ ቻይናው ጉዋንግዙ ኤቨርግራንዴ በቋሚነት ተዘዋውሯል ይህ ብራዚላዊ ኮከብ በ2017 ነበር ወደ ባርሴሎና በ40ሚፓ የተዘዋወረው ባለፈው ሲዝን ለባርሴሎና ትልቅ ግልጋሎት ሲሰጥ ነበር በላሊጋውም 9ግቦችን ማስቆጠር ችሎ ነበር በዘንድሮ ሲዝን ግን ለኤቨርግራንዴ በውሰት ተሰቶ ነበር ነገር ግን ይሄን ተጨዋች በቋሚነት የማስፈረም ስምምነት ነበራቸው ትናንት የ30 አመቱን ፓውሊንሆን ከ42 እስከ 50 ዩሮ በሚጠጋ ቋሚ ማረጋቸው ታውቋል
ፉልሀም የቀድሞውን የሊቨርፑል አጥቂ ሆላንዳዊውን ሪያን ባብልን እስከዚ አመት መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል ከቤኪሽታሽ አስፈርመውታል
የፋብሪጋስን ቦታ ለመተካት ወደ ገበያ የወጡት ቸልሲዎች ለዜኒቱ ሊያንድሮ ፓርዴዝ የተሻሻለ ሂሳብ አቅርበውለታል ከዚህ በፊት 26ሚፓ አቅርበው ነበር ዜኒት 36ሚፓ ነው የምፈልገው ብሎ አሁን ደሞ ቸልሲዎች የተሻሻለ 31ሚፓ አቅርበዋል ከተጨዋቹ ጋር በግል ተስማምተዋል ተብሏል አራት አመት ተኩል በሳምንት 80ሺ ፓዎንድ እየከፈሉት ለማስፈረም ተስማምተዋል ነገር ግን አሁንም ከዜኒት ጋር አልተስማሙም
ካሊዱ ኩሊባሊ በጣሊያን እየደረሰበት ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት ከጣሊያን መልቀቅ እንደሚፈልግ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ ማረፊያው ደግሞ ዩናይትድ ሊሆን እንደሚችል እየተገረ የሚገኘው
የአትሌቲኮ ማድሪዱ ተከላካይ ዲያጎ ጎዲን ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል ተስማማ ኡራጋዊው ተከላካይ በመጪው ክረምት ኢንተርን በነፃ ይቀላቀላል ጎዲን ኢንተርን በሁለት አመት ውል ሚቀላቀል ሲሆን በአመት 6ሚዩ ክፍያ ያገኛል
ያያ ቱሬ ከግሪክ መልስ ወደ ስኮትላንድ አምርቶ ሴልቲክን ለመቀላቀል ተቃርቧል
ባርሴሎናዎች ሉዊስ ሱዋሬዝን ለመተካት የፍራንክፈርቱን አጥቂ ሉካ ዮቪችን ለማዘዋወር ጥረት እያደርጉ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው
ብዙዎቻችን ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ምናቃቸው ማርቲን ኦኔል አዲሱ የኖቲንግሀም ፎረስት አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል ሰሞኑ በተደጋጋሚ ከክለቡ ጋር ሲያያዙ የነበሩት የ66አመቱ አሰልጣኝ በይፋ መግባቱን ክለቡ ይፋ አድርጓል
የስፔን ላሊጋ ፕሬዝዳንት ሀቭዬር ቴባስ ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ስፔን ላሊጋ ቢመለሱ ደስ ይለኛል ብለዋል ከካታላን ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስተያየቱን የሰጡት ማድሪዶች ፍላጎት አላቸው እየተባለ ነው ሳንቲያጎ ሶላሬን እስከ 2021 በክለቡ የሚያቆየው ውል ቢኖረውም ፊዮሬንቲኖ ፔሬዝ ግን ጆዜ ሞሪንሆን ካገኙ አይጠሉም እየበባለ ነው
የአውሮፓ የእግር ኳስ ማህበር ቼልሲዎች ላይ ደጋፊዎች ላይ ከፀረ ሴማዊነት እና ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ጩኸት አሰምተዋል ሞልዲቪ ከተባለው የሀንጋሪ ክለብ ጋር ሲጫወቱ በሚል ክስ መስርቶባቸዋል የቼልሲው ሊቀመምበርም ብሩስ ባክ ክለቡ እንደማይደግፈው እና ደጋፊዎች መቀጣት እንዳለባቸው ሲናገሩ ነበር አሁን ይህ ነገር ተግባራዊ ከሆነ የተወሰኑ ጨዋታዎችን በግማሽ ሜዳ እንደሚያደርግ ተነግሯል
Tuesday, January 15, 2019
የረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች
ማንቸስተር ዩናይትድ ቤልጄምውያዊውን አማካይ ማርዋን ፌላኒ ለመውሰድ የሚፈልግ ክለብ ካለ ለመሸጥ ፈቃደኛ ሲሆን ከዝውውሩ የሚፈልገውም £15ሚ. ብቻ ነው።ኤሲ ሚላን፥ፖርቶ እና የቻይናው ክለብ ጉዋንግዙ ኤቨርግራንዴ የተጨዋቹ ዋነኛ ፈላጊዎች ናቸው።
(Mirror)
ቼልሲ የ31 አመቱን አርጀንቲናዊ የጁቬንትስ ንብረት ሆኖ በ ኤሲ ሚላን የሚገኘውን ጎንዛሎ ሂጎኢን ዝውውር በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንደሚጨረስ ይጠበቃል።
የኤሲ ሚላኑ አሰልጣኝ ጄናሮ ጋቱሶ ግን ሂጎይን ከክለቡ እለቃለው ብሎ አለነገረኝም ብሏል።
(Telegraph)
ሪያል ማድሪድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዴንማርካዊው የቶተናሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ላይ ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ሆኗል።ሎስብላንኮዎቹ ይህንን ዝውውር የመጨረስ ጥረታቸውን አጠናክረው አየቀጠሉ ሲሆን ፍሎረንቲኖ ፔሬዝም ወደ 'ጋላክቲኮስ' አስተሳሰብ የመመለስ ሀሳብ አላቸው።
(AS)
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ኦዚል ከክለቡ ቢለቅ እንደማይከፉ ከተናገሩ ወዲህ የጀርመናዊው አማካይ ስም ከተለያዩ ክለቦች ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።ዛሬ የወጡ ዜናዎች ደግሞ እንደሚጠቁሙት ኢንተር ሚላን ተጨዋቹን በውሰት መውሰድ ይፈልጋል።
(Mirror)
አርሰናል ቤልጄሚያዊውን ዊንገር ያኒክ ካራስኮ ከቻይናው ክለብ ዳሊያን ዪፋንግ የማስፈረም ፍላጎት ቢኖረውም ኦዚልን ካልሸጠ ግን ኤምሬ የተመደበላቸው በጀት ተጨዋቹን ለመግዛት አያስችላቸውም።
(Fox Sports Asia)
የቼልሲው አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ቸልሲን የመልቀቁ ነገር እርግጥ እየሆነ ነው ቅዳሜ እና እሁድን ያሳለፈው በማድሪድ ነበር እናም በማድሪድ ማሳለፉን ተከትሎ ስሙ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋ ተያይዟል ባሳለፍነው ሳምንት ስሙ በሰፊው ከሲቪያ ጋ መነሳቱ የሚታወስ ነው ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች ይፋዊ ጥያቄ እንዳላቀረቡ ነው መረጃዎች ሚያሳዩት።
(Goal)
ቤልጄማዊው የቶተንሀም አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ ወደ ቻይና መሄዱ ተረጋግጧል ትናንት ከሰአት ወደ ቤጂንግ ጉዋን ነበር ሊያመራ ነው የተባለው ነገር ግን ከ4 ሠአታት ቡሀላ ከዚ ከቤጂንግ ጉዋን ጋ የነበረው ድርድር ባለመሳካቱ ሌላው የቻይና ክለብ ዴምቤሌን የማግኘት እድሉ ሰፍቷል ተብሏል።
(Goal)
ቼልሲ ቤልጄሚያዊውን የጨዋታ ቀማሪ ኤድን ሃዛርድ የሚፈልግ ማንኛውም ክለብ £100M እንዲያቀርበለት ይፈልጋል።የሀዛርድ ስም በተደጋጋሚ ከሪያል ማድሪድ ጋር እንደሚያያዝ ይታወቃል።በተለይ ከሳምንታት በፊት ሃዛርድ ስለጉዳዩ ተጠይቆ "ሪያል ማድሪድ ለመሄድ አልፈልግም ብዬ አልዋሽም" ካለ ወዲህ የዚህ ዝውውር ጉዳይ ብዙ አያስባለ ነው።
(Telegraph)
ቶተንሃም በማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው 1-0 በተሸነፈበት ጨዋታ የቁርጭምጭሚት ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ሃሪ ኬን ለስድስት ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ተነግሯል።

ኡራጋዊው የፓሪሴንት ጄርሜን አጥቂ ኤዲሰን ካቫኒ በፒኤስጂ ጫማውን መስቀል እንደሚፈልግ ተናግሩዋል በክለቡ እስከ 2020 የሚያቆይ ኮንትራት ያለው በ2013 ከናፖሊ የተቀላቀለው አጥቂ በ117 ጎል የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪም መሆኑ ይታወቃል እስከ 2020 በዚ ክለብ ነው መቆየት የምፈልገው ከ2020 ቡሀላ ግን የመጫወት አቅም ይኖረኛል ብዬ አላስብም እድሜዬም እየሄደ ስለሆነ ስለዚ እግር ኳስ የመጫወት ጊዜን ማጠናቀቅ የምፈልገው ወይም ጫማዬን መስቀል ምፈልገው በዚ ክለብ ነው
የቼልሲው አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ቸልሲን የመልቀቁ ነገር እርግጥ እየሆነ ነው ቅዳሜ እና እሁድን ያሳለፈው በማድሪድ ነበር እናም በማድሪድ ማሳለፉን ተከትሎ ስሙ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋ ተያይዟል ባሳለፍነው ሳምንት ስሙ በሰፊው ከሲቪያ ጋ መነሳቱ የሚታወስ ነው ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች ይፋዊ ጥያቄ እንዳላቀረቡ ነው መረጃዎች ሚያሳዩት
ቤልጄማዊው የቶተንሀም አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ ወደ ቻይና መሄዱ ተረጋግጧል ትናንት ከሰአት ወደ ቤጂንግ ጉዋን ነበር ሊያመራ ነው የተባለው ነገር ግን ከ4 ሠአታት ቡሀላ ከዚ ከቤጂንግ ጉዋን ጋ የነበረው ድርድር ባለመሳካቱ ሌላው የቻይና ክለብ ዴምቤሌን የማግኘት እድሉ ሰፍቷል ተብሏል
አሮን ራምሴን በነፃ ከአርሰናል ያገኙት ጁቬዎች አርሰናልን ለመካስ ሞሮካዊውን ተከላካይ መህዲ ቤናቲያን ለአርሰናል ለመሸጥ መስማማታቸውን የተለያዩ መረጃዎች ወተዋል
ቼልሲ የፋብሪጋዝን መውጣት ተከትሎ ተጨዋች ለማስፈረም እያሰሱ ይገኛሉ ሳሪ እናም የሱን ቦታ ለመተካት ሁለት ተጨዋቾች የቸልሲ ራዳር ውስጥ ገብተዋል የመጀመሪያው የካግሊያሪው ኒኮሎ ባሬላ ነው ሁለተኛው ደግሞ የዜኒትስበርጉ ሊያንድሮ ፓራዴዝ ነው በተለይ ደግሞ ለፓራዴዝ ይፋዊ የሆነ ጥያቄ አቅርበዋል ተብሏል ለዜኒቶች 26.8ሚፓ ለመክፈል ጠይቀዋል ተብሏል
ኤቨርተኖች የኢድሪስ አጋናጉዬን ዋጋ ለፓሪሰንት ጄርሜን አሳውቀዋል ተብሏል እንደሚታወቀው ፒኤስጂ የአድሪያን ራቢዮት በክለቡ መቆየት አጠራጣሪ መሆኑን ተከትሎ የሱን ቦታ ሚሸፍን አማካይ እየፈለጉ ይገኛሉ ስለዚ በፒኤስጂ ይፈለጉ የነበሩት አማካዮች አለን የናፖሊው አንዱ ነበር 89ሚፓ በመጠየቃቸው አንፈልግም ብለው ነበር እንዲሁም ዊሊያን ቬግልም ከዶርትመንድ እንዲሁም በፒኤስጂ የሚፈለግ ተጨዋች ነው ዶርትመንድ ደሞ አማካዩን መልቀቅ አይፈልግም ስለዚ ያላቸው አማራጭ የኤቨርተኑ አጉዬ ነበር 28 ሚፓ መክፈል ከቻላቹ መውሰድ ትችላላቹ ብለዋቸዋል
ኡናይ ኤምሬ ሜሱት ኦዚልን ለመልቀቅ ፍቃደኛ መሆናቸው ተነግሯል በዚ የዝውውር መስኮት በውሰት እንጂ በቋሚነት ማስፈረም ስለማይችሉ ኦዚልን በመልቀቅ ሌላ አዲስ ተጨዋች ማምጣት ይፈልጋሉ አሁን በወጣ መረጃ ለጁቬንቱስ እና ለኢንተር ሚላን ይሄንን ተጨዋች እንዳቀረበ መረጃዎች ይጠቁማሉ በሳምንት 350ሺፓ የሚከፈለውን ኦዚልን ሽጠው ሁለት አዳዲስ ተጨዋቾችን በቋሚነት ማስፈረም ይፈልጋሉ ኦዚል እና አርሰናል መለያየታቸው እየተቃረበ ይመስላል
ማንችስተር ዩናይትድ ቶተንሀም እና አርሰናል የሊሊያም ቱራምን ልጅ ማርከስ ቱራምን ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብተዋል የ21 አመቱ አጥቂ ለጋንጎ ነው እየተጫወተ የሚገኘው በ17ጨዋታዎች 10ጎሎችን አስቆጥሯል እንዲሁም ቅዳሜ እለት ጋንጎ ከሴንቲቲያን ያደረጉትን ጨዋታ ሶስቱም ክለቦች መልማዮቻቸውን ልከው ማርከስ ቱራምን እንደተከታተሉት ታውቋል
የማክሰኞ ምሳ ሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ጀርመናዊው ኢንተርናሽናል ሜሱት ኦዚል በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከክለቡ እንዲሰናበት ይፈልጋሉ።ኤምሬ ከዝውውሩ በሚገኘው ገንዘብ ሁለት ተጨዋቾችን ለማዘዋወር አቅደዋል።ኦዚል በሳምንት £350,000k የሚከፈለው ሲሆን የክለቡ ከፍተኛ ተከፋይም ነው።
(Mail)
ቼልሲ ቤልጄሚያዊውን የጨዋታ ቀማሪ ኤድን ሃዛርድ የሚፈልግ ማንኛውም ክለብ £100M እንዲያቀርበለት ይፈልጋል።የሀዛርድ ስም በተደጋጋሚ ከሪያል ማድሪድ ጋር እንደሚያያዝ ይታወቃል።በተለይ ከሳምንታት በፊት ሃዛርድ ስለጉዳዩ ተጠይቆ "ሪያል ማድሪድ ለመሄድ አልፈልግም ብዬ አልዋሽም" ካለ ወዲህ የዚህ ዝውውር ጉዳይ ብዙ አያስባለ ነው።
(Telegraph)
ቶተንሃም በ ማንቸስተር ዩናይትድ በተሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው ሃሪ ኬን ለአንድ ወር ያክል ከሜዳ ላይ ሊርቅ እንደሚችል እየተነገረ ነው።በዚህም ምክንያት ስፐርስ የባርሴሎናውን አጥቂ ማልኮም በውሰት ለማዘዋወር ጥረት ጀምራለች።
(Guardian)
የዌስት ሀሙ አጥቂ ማርኮ አርናውቶቪች በዚህ ሳምንት ውስጥ የህክምና ምርመራውን አጠናቆ በ £35M ወደ ቻይናው ክለብ ቻይኒዝ SIPG ይዘዋወራል ተብሎ ይጠበቃል።
(Sun)
አልቫሮ ሞራታን ለማዘዋወር £40M አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ሲቪያ ካቀረበው ገንዘብ በላይ የመክፈል አቅም ስለሌለው ስፔናዊው አጥቁ ወደ ዲዬጎ ሲሞኒው አትሌቲኮ ማድሪድ የመዘዋወር ዕድሉ እየሰፋ መጥቷል።
(Marca)
በኦሊጉናር ሶልሻየር ስር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ዴቪድ ዴሄያ በማንቸስተር ዩናይትድ ለመቆየት የሚፈልግ ሲሆን ደሞዙ ግን በሳምንት £300,000k እንዲሆንለት ይፈልጋል።
(Mail)
የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች በጊዜያዊነት ክለቡን የተረከበው ኖርዌያዊው አሰልጣኝ ኦሊጉናር ሶልሻየር በቋሚነት ዕድሉ ተሰቶት ቀያይ ሰይጣኖቹን ለረዥም ጊዜ እንዲያሰለጥን ይፈልጋሉ።
(Telegraph)
ቼልሲ የዜኒት ፒተርስበርጉን አርጀንቲናዊ አማካይ ሊዮናርዶ ፓራዴስ ለማዘዋወር ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን ለክለቡ £27M አቅርቧል።

Monday, January 14, 2019
የሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
የባርሴሎናው የግራ መስመር ተጨዋች ጆርዲ አልባ ከባርሴሎና ጋር ረጅም አመት መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሮ የወደፊት ቆይታው ላይ ግን እርግጠኛ እንዳልሆነ ተናግሯል በካምፕኑ እስከ 2022 የሚያቆየው ኮንትራት ቢኖረውም ባርሴሎናዎች ግን ከ2015 ቡሀላ በኮንትራት ጉዳይ አናግረውት አያውቁም ክለቡም ለልጁ ያን ያህል ፍላጎት እንደሌለው እና ልጁ ግን በክለቡ ቢቆይ ደስተኛ መሆኑ ተናግሯል
በባርሴሎና በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ብራዚላዊው የቸልሲ ተጨዋች ዊሊያን ክለቡን እንደማይለቅ ተናገረ በቼልሲ ደስተኛ ነኝ በቸልሲም ቆያለው 1አመት ከ6 ወራት ኮንትራት ይቀረኛል ይሄንን ውል አጠናቅቃለው በቀጣይነትም የ30 አመቱ ዊሊያን ከቸልሲ ሰዎች ጋር ድርድር እንደሚጀምርም ተነግሩዋል
አብዱላሂ ዱኮሬ ከዋትፎርድ መልቀቅ እንደሚፈልግ ተናገረ ይህንንም ለክለቡ መናገሩ ተናግሩዋል የ26 አመቱ ተጨዋች ከ3 አመት በፊት ነበር ክለቡን የተቀላቀለው በ78 ጨዋታ ዘጠኝ ግቦችን አስቆጥሯል አማካዩ ባሳለፍነው አመት የክለቡ ኮከብ ተጨዋች መባሉ ይታወሳል በቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፍ ክለብ መቀላቅል እንደሚፈልግም ተናግሯል
ማሪዮ ባላቶሊ አሁንም በኒስ ከአሰልጣኙ ጋ አሁንም አልተስማም አሁን ላይ ከኒስ መውጣቱ እርግጥ እየሆነነ ነው ፍራንስ ፉትቦል እንዳወጣው መረጃ አሁንም ማርሴ ተጨዋቹን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረገ ነው በሌላ መረጃ ደግሞ ልጁ ከማርሴ ይልቅ ወደ ጣሊያን መመለስ እንደሚፈልግም እየተነገረ ነው ነገር ግን የቀድሞ ክለቦቹ ተጨዋቹን የማስፈረም ፍላጎታቸው ስለቀነሰ እዛው ፈረንሳይ ውስጥም እንደሚቆይ እርግጥ ሆኗል
ጁቬንቱስን ለመቀላቀል ጫፍ ላይ የደረሰው አሮን ራምሴ ዛሬ ጠዋት በለንደን የጤና ምርመራውን አድርጉዋል አሁን ወደ ጁቬንቱስ መግባቱ እርግጥ ሆኗል የአምስት አመት ውል ይፈርማል በጁቬንቱስ በአመት 7ሚዩ ይከፈለዋል በሌላ ዜና የራምሴ መምጣት ሳሚ ከዲራን ከጁቬ እንዲወጣ ሊያደርገው ይችላል
የአትሌቲኮ ማድሪድ የመስመር ተከላካይ ሁዋን ፍራን በአትሌቲኮ መቆየት እንደሚፍልግ ተናግሯል ስፔናዊው የ34 አመት ተከላካይ በ2011 ነበር ከኦሳሱና አትሌቲኮን የተቀላቀለው በዚህ አመት መጨረሻ ነው ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ትናንትም ከጨዋታው ቡሀላ በሰጠው አስተያየት አዲስ ኮንትራት መፈረም ፈልጋለው ቀጣይ አመታትንም በክለቡ መቆየት እፈልጋለው ብሏል
የቀድሞ የፒኤስጂ የኒውካስትል ፓላስ ተጨዋች ፈረንሳዊው ሁዋን ካባይ ከአልናስር ክለብ ጋ መለያየቱ መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ የ33 አመቱ ተጨዋች ወደ እንግሊዝ ተመልሶ ወደ ቀድሞ ክለቡ የሚመለስበት እድል አለ ተብሉዋል የኒውካስትሉ አሰልጣኙ ቤኒቴዝ ተጨዋች እንደሚፈልጉ በግልፅ መናገራቸው ይታወሳል እናም ይሄንንም ተከትሎ የቀድሞ ልጃቸውን በነፃ ማግኘት የሚችሉበት እድል አለ ሚል ዘገባ ወቱዋል
የኢንተር ሚላኑ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ጁሴፔ ማሮታ ስለ ኢካርዲ አስተያየት ሰተዋል ደጋፊዎች በማውሮ ኢካርዲ ዙሪያ ደጋፊዎች ምንም አይነት ስጋት ሊገባቸው አይገባም ብለዋል በክለቡ ያለው የውል ማፍረሻ 110 ሚዩ ነው ከጁን 1-15 ባለው ጊዜ ነው ክለቦች ከፍለው መውሰድ የሚችሉት ማለት ከጣሊያን ውጭ ያሉ ክለቦች ከነዚህም ውስጥ ባርሴሎና ፒኤስጂ ማድሪድ እየተፈለገ ይገኛል በኢንተር ግን እንደሚቆይ ተስፋ አደርጋለው ብለዋል
Sunday, January 13, 2019
"ሶልሻየር ደስታችንን መልሶልናል" ዴሄያ
"ሶልሻየር ደስታችንን መልሶልናል ፥ ይሄ ትክክለኛው ማንቸስተር ዩናይትድ ነው" ዴሄያ
ዴቪድ ዴሄያ በጊዜያዊነት ማንቸስተር ዩናይትድን እያሰለጠነ የሚገኘው ኦሊጉናር ሶልሻየርን እውነተኛውን ዩናይትድ መልሶታል በማለት ከትናንቱ የስፐርስ ድል በኋላ ተናግሯል።
ዩናይትድ ከሶልሻየር መምጣት በኋላ በእጅጉ መሻሻሉ እየተነገረ ሲሆን በጆዜ ሞሪንሆ ስር ከነበረው የቡድን መንፈስም አሁን ያለው መነቃቃት ከፍተኛ ነው።
በስኳዱ ውስጥ ወደ በቃታቸው ከተመለሱ ተጨዋቾች አንዱ የሆነው እና በትናንቱ ፍልሚያ 11 ያለቀላቸው ኳሶችን ያዳነው ስፓኒያርዱ ግብ ጥባቂም አሁን ቡድኑ ላለበት ጠንካራ አቋም ኖርዊያዊው አሰልጣኝ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግሯል።

የዕሁድ ከሰዐት ስፖርታዊ ዜናዎች
ወደ ጁቬንቱስ መግባቱ እርግጥ የሆነው አሮን ራምሴ አሁን ደግሞ አርሰናሎች ለጁቬንቱስ አዲስ ጥያቄ አቅርበዋል ጁቬንቱስ የጥር የዝውውር መስኮት ከሆነ ራምሴን የሚፈልገው ከሆነ መክፈል ያለባቸውን ገንዘብ ገልፀውላቸዋል አርሰናልም ለራምሴ 18ሚ.ፓ መክፈል ከቻላቹ አሁኑኑ እንለቅላቹሀለን ብለዋቸዋል
.
ሪያል ማድሪዶች መልማዮቻቸውን ወደ ጣሊያን ልከዋል በክረምቱ በ4.5ሚ.ዩ ወደ ጄንዋ የተዘዋወረውን ክሪስቶፎ ፒያቲክን ለማዘዋወር ፍላጎት አሳይተዋል በሴሪያው ምርጥ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘውን አጥቂ ለማስፈረም ፉክክር ከናፖሊ ይገጥማቸዋል ናፖሊዎች ለልጁ እስከ 60ሚ.ፓ ከፍለው የማስፈረም ፍላጎት አላቸው
.
ኢንተር ሚላኖች የዩናይትዱን ቀኝ መስመር ተመላላሽ አንቶኒዮ ቫሌንሲያን ለመውሰድ ተቃርበዋል በዩናይትድ 10አመት የተጫወተውን ቫሌንሲያን በክረምቱ በነፃ ለማስፈረም ተቃርቧል
.
የፒኤስጂው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል አንድ አስተያየት ሰተዋል ከዝውውር ጋር በተያያዘ ተጠይቀው ከዚ ቡሀላ እንቅልፍ የምተኛው ቡድኔ ተጨዋች ሲያስፈርምልኝ ብቻ ነው የሚል አስተያየት ሰተዋል ፔዤ አንድ የተከላካይ አማካይ ለማስፈረም ይፈልጋሉ ከነዚህ ውስጥ ኢድሪስ አጉዬ ዶኮሬ እንዲሁም ፋቢንሆን እየፈለጉ ይገኛሉ
.
ትናንት የፋብሪጋዝን ዝውውር ያጠናቀቀው የሄነሪው ሞናኮ ቤልጄማዊውን ሚኪ ባትሽዋይን በውሰት ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል ህክምናውን ዛሬ እንደሚያጠናቅቅ እና ነገ ዝውውሩን ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል ከሄነሪ ጋ በቤልጄም ብ/ቡድን አብረው መስራታቸው ይታወሳል በተጨማሪም ዝውውሩ ከተጠናቀቀ በድጋሚ ወደ ፈረንሳይ ተመልሶ ይጫወታል ባትሹዋይ በአንድ አመት ለሶስተኛ ጊዜ ነው በውሰት ሲሰጥ አምና በቦሩሲያ ዶርትመንድ እንዲሁም ዘንድሮ በቫሌንሲያ ያልተሳካ ጊዜ አሳልፉዋል ሞናኮም በጥሩ የዝውውር መስኮት ባትሽዋይ አምስተኛ ፈራሚው ሆኗል
.
ሪያል ማድሪድ የቶተንሀሙን ሀሪ ኬንን ለማስፈርም ፍላጎት አለው AS እንዳለው ግን ቶተንሀሞች ማድሪድ ሀሪ ኬንን ማስፈረም ከፈለጋቹ 350ሚፓ መክፈል አለባቹ ብለዋቸዋል ተጨዋቹ ላይም ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ እንደለጠፉበት ዘግቧል
.
በወጣቶች ላይ ቡድናቸውን በመስራት የሚታወቁት ቦሩሲያ ዶርትመንዶች ከአርጀንቲናው ቦካ ጁንየርስ አንድ ተጨዋች ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል የቦካው ፕሬዝዳንትም ዝውውሩን ይፋ አርገውታል ለ19አመቱ ሊያናርዶ ባሌርቢ ዶርትመንዶች 15ሚ.ፓ ለመክፈል ተስማምተዋል በዚህ ሳምንት መጨረሻ የህክምና ምርመራውን እንደሚያጠናቅቅ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል
.
የቶተንሀም ሆትስፐር የአዲሱ ስታድየም ግንባታ እስከዚ ሲዝን መጨረሻ ላይጠናቀቅ እንደሚችል ተነግሯል ስታድየሙ 1ቢ.ፓ ወጪ ተደርጎበታል ቢያንስ ማርች ወር ላይ ከክሪስታል ፓላስ ጋ በሚኖረው ጨዋታ ለመክፈት ፍላጎት ነበረው ክለቡ ነገር ግን ለዚ ላይደርስ ይችላል ተብሏል ይህ ዜና በርካታ የቶተንሀም ደጋፊዎችን አስቆጥቷል

Saturday, January 12, 2019
የቅዳሜ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
የፊት መስመር ተጨዋች ችግር ውስጥ የገባው ሪያል ማድሪድ ፊታቸውን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ኮከቡቹ ኤሪክሰን እና ሀዛርድ ላይ አይናቸውን ጥለዋል የሀዛርድ የረጅም ጊዜ ፈላጊ የሆኑት ማድሪዶች አሁን ደግሞ ከሱ በተጨማሪ ኤሪክሰንን ፈልገዋል ማድሪዶች ለሁለቱ ኮከቦች ከ200 ሚ.ፓ በላይ ለማውጣት ፍላጎት አሳይተዋል
ቼልሲዎች ከባርሴሎና የቀረበላቸውን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል በቼልሲ ቤት የ18ወራት ኮንትራት ያለውን የ30 አመቱን ዊሊያንን ለማስፈረም በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ውድቅ ተደርጎባቸዋል ባርሳም በመጨረሻ 50ሚ.ፓ+ማልኮምን ለቸልሲ አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበታል
ጁቬንቱስ የአሮን ራምሴን ዝውውር ወደ ማጠናቀቁ እየተቃረበ ነው ታዋቂው ጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ጂያን ሉካ ዲማርዚዮ ከሱፐር ኮፓ ጨዋታ ቡሀላ ጁቬንቱስ ይህንን ዝውውር ይፋ ያደርጋል የሚል መረጃ ሰቱዋል አሁን ደግሞ ኢስኮንም ከማድሪድ ለመውሰድ ዝግጅቱን እንደጨረሰ መረጃዎች እየወጡ ነው በክረምቱም ልጁን እንደሚያስፈርሙት ተማምነዋል የሚል መረጃ ወተዋል
የአጥቂ ችግር ያለበት ቼልሲ አሁንም ሂግዌንን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል ተጨዋቹም ዝውውሩ እንዲጠናቀቅ ክለቡ ላይ ግፊት እያደረገ እንደሆነ ተነግሯል በተያያዘ ዜና አልቫሮ ሞራታ በውሰት ወደ ባርሴሎና ሊያመራ ይችላል የሚል በርካታ መረጃ እየወጣ ነው
አድራን ራቢዮት በፒኤስጂ ደጋፊዎች መጠላቱን ሌዲስ ስፖርት አስነብቧል በዘገባውም ከፒኤስጂ ደጋፊዎች በተሰበሰበ ድምፅ 88% የፒኤስጂ ደጋፊዎች ዳግመኛ ይሄንን ማልያ እንዳይለብስ ብለዋል በዚህ አመት ውሉ የሚጠናቀቀው ራቢዮት ኮንትራት ቀርቦለት አልፈርምም ማለቱ ይታወሳል ምናልባትም ወደ ባርሴሎና ወይ ባየርን ሙኒክ ሊያመራ ይችላል
በውሰት ብቻ ተጨዋች ማስፈረም እንደሚፈልጉ የተናገሩት ኡናይ ኤምሪ በውሰት ሊያስፈርሙዋቸው የሚችሉዋቸው ተጨዋቾች ዴኒስ ሱዋሬዝ እና ኤቨር ባኔጋ ናቸው የሱዋሬዝ ዝውውር በቅርብ ሊጠናቀቅ ይችላል ተብሏል ሁለቱም ተጨዋቾች ከኤምሪ ጋር አብረው ሰርተዋል በክረምቱ ደግሞ እስማኤል አሳር የሚባለውን የሬን ተጨዋች የማምጣት ፍላጎት አላቸው
ፉልሀሞች አሌክሳንደር ሚትሮቪችን ለማስፈረም ከአንድ የቻይና ክለብ ጥያቄ መቶላቸው ውድቅ አድርገውባቸውል የቻይናውም ክለብ ለፋልሀም ጠንካራ የዝውውር ጥያቄ አቅርበው ነበር ለሚትሮቪች ዝውውር ከ50ሚ.ፓ በላይ ቢያቀርቡም ጥያቄው ውድቅ ሆኗል
በኒውካስትሉ ጨዋታ ጉዳት የደረሰበት ፖል ፖግባ ለእሁዱ የዌምብሌ ጨዋታ 100% ዝግጁ እንደሆነ አሰልጣኝ ኦሊጎነር ሶልሻየር ተናግረዋል
ዳቪድ ሉዊዝ ኮንትራቱ ማይታደስለት ከሆነ ወደ ቀድሞ ክለቡ ቤኔፊካ መሄድ ይፈልጋል ተብሏል ከዛ ውጪ በስኮላሬ የሚሰለጥነው የብራዚሉ ፓልሜራስም ዳቪድ ሉዊዝን የመውሰድ ፍላጎት አለው ተብሏል
Friday, January 11, 2019
የቅዳሜ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች
ባርሴሎና ፊሊፔ ኩቲንሆን ለማዘዋወር ለሚፈልጉ ክለቦች በሩን ክፍት ማድረጉ እየተነገረ ነው።ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ የቀድሞ ብራዚለዊ የሊቨርፑል ተጨዋች ዋነኛ ፈላጊ ነው።
(Calciomercato, via Star)
ባርሴሎና በይፋ ብራዚላዊውን የቼልሲውን ዊንገር ዊልያን ለማዘዋወር ማክሰኞ ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ከተደረገበት በኋላ በድጋሚ ገንዘብ ጨምሮ ጥያቄ ሊያቀርብ ነው።
(Standard)
ቼልሲ የካጊላሪውን ጣሊያናዊ አማካይ ኒኮላ ባሬላ ለማዘዋወር በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሷል።የዜኒቱን አርጀንቲናዊ አማካይ ሊዬንድሮ ፓራዴስም ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።
(Telegraph)
የኔይማር ወኪል የሆነው ወላጅ አባቱ ብራዚላዊው የ26 አመት የአለማችን ውዱ ተጨዋች ወደ ቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና መመለስ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
(Express)
ሊቨርፑል እና ፉልሀም እስራኤላዊውን የራቢ ሳልዝቡርግ የ26 አመት አጥቂ ሞያኔስ ዳቡር ለማዘዋውር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Estadio Deportivo - in Spanish)
ጁቬንትሶች በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት ፈረንሳዊውን የ25 አመት የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ፖል ፖግባ በድጋሚ ወደ ቱሪን ለመመለስ የሚፈልጉ ሲሆን ቀያይ ሰይጣኖቹ በዝውውሩ ላይ ዳግላስ ኮስታ ከታከለበት ሊያጤኑበት ይችላሉ።
(Tuttosport, via Calciomercato)
አርሰናል አሮን ራምሴን ለጁቬንትስ ሲሰጥ ሞሮኳዊው ተከላካይ መህዲ ቤናቲያ የዝውውሩ አካል ሆኖ ወደ ኤምሬትስ እንዲመጣ ይፈልጋል።
(Gazzetta dello Sport, via Metro)
ባርሴሎና ስፔናዊውን የቼልሲ አጥቂ አልቫሮ ሞራታ በውሰት ለመውሰድ ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሲቪያ እና አትሌቲኮ ማድሪድም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(Sport - in Spanish)
የአርሰናሉ አምበል ላውረንት ኮሼልኒ ከሞናኮ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
(Le10 Sport, via Mirror)

የአርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
በባይርን ሙኒክ በውሰት ውል እየተጫወተ የሚገኘውን ሀሜስ ሮድሪጌዝ ውል ለማደስ እያቅማማ የሚገኘው ሙኒክ ልጁን ሊያጣ ተቃርቧል ሀሜስ በተለያዩ ክለቦች በጥብቅ እየተፈለገ ነው የእንግሊዞቹ አርሰናል እና ሊቨርፑል እንዲሁም ጁቬንቱስ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል ነገር ግን ከሁሉም በላይ ሙኒክ ልጁን ቋሚ አርጎ የማስፈረም መብት አለው
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ በዝውውር ጉዳይ ለአርሰናል ደጋፊዎች አስደንጋጭ ነገር ተናግረዋል በዚህ የዝውውር መስኮት ተጨዋቾችን የመግዛት አቅም የለንም ነገር ግን በውሰት ተጨዋቾችን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል
ከዩናይትድ የተባረሩት ጆዜ በዚህ ሳምንት የቤኔፊካው ፕሬዝዳንት እሳቸውን ለማምጣት ፈልገው እንደነበር አስተያየት ሰተው ነበር ጆዜም ትናንት ለዚ ጥያቄ መልሳቸውን ሰተዋል ቤኔፊካን የማሰልጠን ፍላጎት እንደሌላቸው እና በቅርቡም ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል ከዛም ባለፈም በቤይን ስፖርት በተንታኝነት እንደሚሰሩ ተረጋግጧል
የሞልድ ማኔጂንግ ዳይሬክተር እስከዚ የውድድር አመት መጨረሻ ነው የተስማማነው አሰልጣኛችንን ለዩናይትድ ስንሰጥ ስለዚ በጊዜው ይመለሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን አሁን በእቅዳችን ውስጥ ያለው ፕላን A ፕላን B ሶልሻየር ወደኛ እንደሚመለስ ነው ሌላ ምንም አይነት እቅድ የለንም ሌላም አሰልጣኝ የማምጣት ፍላጎት የለንም ብሏል
የሳውዝሀምብተኑ ቻርሊ ኦስቲን ቅጣት ተላልፎበታል በ20ኛ ሳምንት ከሲቲ ጋ በነበራቸው ጨዋታ በጣቱ ምልክት በማሳየት ያልተገባ እና ደጋፊዎችን የሚያበሳጭ ደርጊት ፈፅሟል ኤፌውም ክስ መስርቶበት ነበር ተጨዋቹም ሁለት ጨዋታዎችን ተቀቷል ሳውዛንብተን ከሌስተር እና ከደርቢ የሚያደርጋቸው ጨዋታ ያመልጡታል
ባርሴሎና ዊሊያን ላይ ያለው ፍላጎት አሁንም ተነስቷል ባለፈው ክረምት ሶስት ጊዜ ጥያቄ ለቼልሲ አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸው ባርሴሎናዎች አሁንም ድጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል ክረምት ላይ ዊሊያንን ሲያጡ ከቦርዶ ማልኮምን ማስፈረማቸው ይታወሳል እና አሁን ላይ ይሄንን ተጨዋች በዝውውሩ ላይ ለማካተት አላቸው
እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ኤቨርተን ሚኪ ባትሽዋይን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ነገር ግን ኤቨርተኖች ዝውውሩን በቋሚነት ነው ማረግ ሚፈልጉት ቸልሲዎች ደሞ ጥሩ አጥቂ እስኪያገኙ ድረስ በቋሚ ዝውውር መሸጥ አይፈልጉም
የላስቬጋስ ፖሊስ የሮናልዶን የዲኤንኤ ሳምፕል እንዲመጣለት ጠይቋል ምክንያቱም ከአስገድዶ መድፈር ጋ በተያያዘ ክስ እንደሚጠብቀው እና ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል መረጃዎች እያሳዩ ይገኛሉ
Thursday, January 10, 2019
ሀሙስ ምሽት የወጡ ስፖርተዊ ዜናዎች
በዚ የዝውውር መስኮት ቤልጄማዊው ያኒክ ካራስኮ ወደ አርሰናል የመምጣት እድሉ ሰፊ ሆኗል ልጁም ወደ አርሰናል ለመምጣት ከክለቡ ጋር ተስማምቷል ተብሏል በአመት እስከ 10ሚ.ዩ ለመክፈል አርሰናሎች ተስማምተዋል ልጁ በኤሲሚላን በጥብቅ ቢፈለግም ምርጫውን ግን የለንደኑን ክለብ ምርጫው አድርጓል
አልቫሮ ሞራታ በአትሌቲኮ ማድሪድ እና በባርሴሎና እየተፈለገ ይገኛል ባርሴሎና የሱዋሬዝን እድሜ መግፋት ተከትሎ ተተኪ እያፈላለገ ይገኛል ከነዚህም ውስጥ አልቫሮ ሞራታ አንዱ ነው አትሌቲኮም ማድሪድ የኮስታ መጎዳት እና አቋም መውረድን ተከትሎ ግሪዝማንን የሚያጣምር ጥሩ ሚባል አጥቂ ይፈልጋሉ ምርጫቸውንም ሞራታን አርገውታል
ዌስትሀም ከአንድ የቻይና ክለብ ለማርኮ አርናቶቪች የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ለ29 አመቱ አጥቂ 35ሚፓ ቢያቀርቡም ክለቡ ዌስትሀም ውድቅ አድርገውታል ለልጁም ከ50ሚፓ በላይ ክፍያን ይፈልጋሉ
ቸልሲዎች ሂግዌንን የማስፈረም ፍላጎታቸውን ቀንሰውታል አሰልጣኙ ሳሪ በናፖሊ አብረውት የሰሩትን ተጨዋች ማስፈረም ይፈልጋሉ ዝውውሩም ቶሎ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋሉ ነገር ግን የቸልሲዋ ዳይሬክተር እድሜው 31 ለሞላው ተጨዋች ይሄን ያህል ገንዘብ ማውጣት አልፈለጉም ይሄን ተከትሎ በሳሪ እና በቸልሲ ባለስልጣናት መካከል ችግር ሳይፈጠር አይቀርም ተብሏል ከዚህ በፊት ኮንቴም በዝውውር ጉዳይ ከቼልሲ ባለስልጣናት በተለይ ከቴክኒክ ዳይሬክተሯ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቶ ሀላፊነቱን እንዳጣ ይታወቃል አሁን ደሞ በሳሪ እና በቸልሲ ቦርድ መካከል ችግር እየተፈጠረ ነው
አንደር ሄሬራ በዩናይትድ ኮንትራት የማደስ ጉዳይ ላይ ንግግር እያደረገ እንደሆነ ተነግሯል ተጨዋቹ ሶልሻየር ከመጣ ቡሀላ በተደጋጋሚ የመሰለፍ እድል እያገኘ ይገኛል በውድድር አመቱ መጨረሻ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ሄሬራ ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል
ፓሪሰንት ጄርሜን ሎሬንዞ ፔሌግሪኒን ከሮማ ማስፈረም ይፈልጋሉ ዝውውሩንም ለማሳካት እንቅስቃሴ ጀምረዋል በተጨማሪም ከዛው ከጣሊያን የናፖሊውን አለንን ለማምጣት 100ሚዩ ሊያወጣ እንደሚችል ተነግሯል
ፈርናንዶ ሊዮሬንቴ በአትሌቲኮ ቢልባኦ እየተፈለገ ይገኛል የቢልባኦ የስፖርቲንግ ዳይሬክተር ራፋ አልኮርታ ይባላሉ እኚ ሰው ሲናገሩም ሀቪ ማርቲኔዝ ኢባ ሆሜዝ አንደር ሄሬራን ሎሬንቴን የማስፈረም ፍላጎት አለን የሚል አስተያየት ሰተዋል
ዴኒስ ስዋሬዝ ከባርሴሎና ወደ አርሰናል እንዲዘዋወር የባርሴሎና ባለስልጣኖች ይፈልጋሉ ፕሬዝዳንቱ ባርቶሚዮም ልጁ ክለቡን መልቀቅ ከፈለገ እንለቀዋለን ብለዋል ልጁም ወደ አርሰናል እንዳይሄድ እያደረገ ያለው ችግር አርሰናል ተጨዋቹን አሁን በውሰት ወስዶ ክረምት ላይ ተጨዋቹን መግዛት ይፈልጋል ባርሴሎና ደሞ አሁን ላይ ከፍለው ተጨዋቹን እንዲያዘዋውሩ ይፈልጋሉ ይሄ ጉዳይ ነው ዝውውሩን ያጓተተው ተብሏል
ማንችስተር ዩናይትድ ግሪካዊውን ኮስታስ ማኖላስን የሮማውን ተከላካይ ሊያስፈርሙ ተቃርበዋል ሚሉ መረጃዎች ወተዋል 30.5ሚፓ ኮንትራት ማፍረሻ ነው ይህንንም ለመክፈል ፍላጎት አሳይተዋል
ኢካርዲ ወደ ሪያል ማድሪድ?
ሪያል ማድሪድ ኢካርዲን ለማዘወዋር ከጫፍ ደርሷል
የኢንተር ሚላኑ አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ ወደ ሪያል መድሪድ ለመዘዋወር በግሉ ከስምምነት ላይ መድረሱን Don Balon አስነብቧል።
ጋዜጣው እንዳተተው ከሆነ አርጀንቲናዊው አጥቂ በሳንቲያጎ በርናቢዮ የስድስት አመት ኮንትራት የተዘጋጀለት ሲሆን የክለቡ ከፍተኛ ተከፋዮች ዝርዝር ውስጥም የሚገባ ይሆናል።
ዚነዲን ዚዳንን እና ክርስቲያኖ ሮናልዶን ካሰነበተ በኋላ ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ሎስብላንኮዎቹ በአመቱ ከሌሎች ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የግብ ድርቅ መቷቸዋል።
ኢካርዲ በዘንድሮ ሲዝን በሁሉም የውድድር አይነቶች ለኢንተር 13 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሞውሪንሆ ያቺን ሰዓት
ፅሁፉ የጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ነው
Moments:
ሞውሪንሆ ያቺን ሰዓት
በሪያል ማድሪድ መልበሻ ቤት የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ አለ። ጆዜ ሞውሪንሆ
አድብቶ የሚያስጠቃቸውን የዚህን ፍልፈል ማንነት አላወቁም። ዕረፍት ነሳቸው።
የመልበሻ ክፍሉን ድብቅ መረጃዎች ለጋዜጦች የሚሰጠው ማነው? ጆዜ ቆረጡ።
"መጋለጥ አለበት" አሉ።
የጋዜጦችን ዕለታዊ ወሬ ሰብስበው በየማለዳው ጠረጴዛቸው ላይ
የሚያስቀምጡላቸውን ሰዎች በወኪላቸው ዦርጌ ሜንዴዝ ኩባንያ "ጄስቲፊዩት"
በኩል ቀጠሩ። ሰዎቹ ሚድያ የተነፈሰውን ሁሉ… እንደወረደም ይሁን ተብራርቶና
ተተንትኖ ለአለቃቸው ያቀርባሉ።
የጆዜ ቀን ዘወትር ከማለዳው 2:00 ሰዓት ላይ ይጀምራል። በልምምድ ማዕከሉ
በሚገኘው ቢሯቸው የጋዜጣ ላይ ዘገባዎችን፣ አስተያየቶችንና የቲቪ ፊልሞችን
በማየት አይናቸውን ይገልጣሉ። ሚድያው የቡድኑን ምስጢር ሁሉ ይዞ
መውጣቱን ቀጥሏል። ጆዜ አንጀታቸው እያረረ መልስ ያላገኙለትን ጥያቄ
ይጠይቃሉ። ፍልፈሉ ማነው?
የመረጃውን ጥራት ሲመለከቱት ደግሞ በቡድኑ አባላት መካከል ባሉ ሰዎች
በኩል የሚወጣ ምስጢር አልመስልህ አላቸው። የሆነ…፣ የተደበቀ ድምፅ
መቅጃ ሳይኖር እንደማይቀር ጠረጠሩ። በድብቅ ንግግሮቻቸውን የሚያደምጥ
ካልሆነ በስተቀር ያቦኩት ሳይጋገር ለአደባባይ ሊበቃ አይችልም።
ቡድኑ ከጨዋታ በፊት በሚያርፍበት ሆቴል ውስጥ የሚሰሩ ሁለት የፅዳት
ሰራተኞች ድብቅ መቅረፀ ድምፅ እንዲፈልጉ አዘዟቸው። ሼራተን ሚራሲዬራ
ተበረበረ፣ በየጥጋጥጉ ተፈተሸ። ምንም አልተገኘም።
ጆዜ ጦፉ። ቀጣዩ ጨዋታ ኤልክላሲኮ ስለሆነ ደም፣ ደም ሸቷቸዋል።
ሲብስባቸው ለክለቡ ከፍተኛ አለቆች የተጫዋቾቻቸውንና ሰራተኞቻቸውን የስልክ
ምልልስ እንዲጠልፉና የሚያወሩትን እንዲቆጣጠሩ ጠየቋቸው። አንዳንድ
ተጫዋቾች ነገሩ በማስጠንቀቂያ መልክ ተነገራቸው። በእጅ ስልኮቻቸው በኩል
የሚያወሩትን ነገር ይዘትና የሚያነጋግሩትን ሰው ማንነት እንዲመርጡ ተመከሩ።
አፕሪል 16 ቀን 2011፣ በቤርናቢዩ ከባርሳ ጋር ከመጫወታቸው ጥቂት ሰዓታት
ቀደም ብሎ ማርካ ጋዜጣ "ዛሬ ፔፔ ይሰለፋል፣ ኬዲራ እና አሎንሶ ያጣምሩታል"
ሲል ሜሱት ኦዚል ተጠባባቂ እንደሚሆን ዘገበ። እንደገና ምስጢር አፈተለከ።
ሰዓቱ ደርሶ ቡድኑ ሊሟሟቅ ሲወጣ ተጫዋቾች በሜዳው ላይ ያልተለመደ ነገር
አስተዋሉ። ሳሩ ከወትሮው ይልቅ ረዝሟል። በቅጡ አልታጨደም። ረጅምና ደረቅ
ነው። የባርሳን የኳስ ሂደት ለማወክና ለማዘግየት መሆኑ ግልፅ ሆነላቸው።
በጨዋታው ማድሪድ በትዕዛዝና በኃይል መከላከልን መረጦ አፈገፈገ። ባርሳዎች
ደግሞ ኳሱን አብዝተው በእግራቸው ስር አቆዩ። ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶች
ተሰጡና ሁለቱም ተቆጠሩ። አንድ በሮናልዶ፣ አንድ በሜሲ። የመጨረሻ
ውጤት? ... 1- 1።
ከዚህ ጨዋታ በፊት ከጋርዲዮላ ባርሳ ጋር በተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች
0-2 እና 2-6 ተሸንፈዋልና አሁን ባያሸንፉም የቤርናቢዩ ደጋፊዎች እፎይታን
አገኙ። አቻው ውጤት ግን የሪያልን የዋንጫ እድል የሚያጠብ ነበር።
ጆዜ ተጫዋቾች በመልበሻ ቤት እስኪሰባሰቡ ጠብቀው ማንባረቅ ጀመሩ። ስድብ
አዘል የስፓኒሽ ቃላት እንደ በረዶ ውሽንፍር በተጫዋቾቹ ላይ ዘነቡ።
"ከሃዲዎች ናችሁ! ከዳተኞች! የማትታመኑ ናችሁ! ስለቡድኑ አሰላለፍ ለማንም
እንዳትናገሩ ነግሬያችሁ ነበር። እናንተ ግን ከእኔ ወገን እንዳልሆናችሁ አሳያችሁ።
የውሻ ልጅ ሁሉ! ብቸኛው ጓደኛዬ ግራኔሮ ብቻ ነበር። አሁን ግን እርሱንም ማመን
እየቸገረኝ ነው። ብቻዬን ተዋችሁኝ። ከገጠሙኝ ቡድኖች ሁሉ እንደዚህ
ከዳተኞች የበዙበት ስብስብ አይቼ አላውቅም…።"
የአሰልጣኙ ቁጣ ማለቁን ሳይጠብቅ ኢኬር ካሲያስ ጥሏቸው ወደ መታጠቢያ
ክፍሉ ገባ። አንዳንዶቹም ተከተሉት። ንዴት እንደ ጉሽ ጠላ አናታቸው ላይ
የወጣባቸው አሰልጣኝ በአፍታ እብደት አጠገባቸው ያገኙትን ሬድ ቡል በካልቾ
ጠለዙት። ቆርቆሮው በኃይል በሮ ከግድግዳው ጋር ሲላተም እግረ መንገዱን
በውስጡ የያዘውን ፈሳሽ በአቅራቢያው በሚገኙ ተጫዋቾች ፊት ላይ ረጨው።
ያኔ ጆዜ በንዴት በግነውና ተጨማሪ ስድቦችን አስከትለው፣ እየተቆጡ በመልበሻ
ቤቱ ወለል ላይ በጉልበቶቻቸው ተንበረከኩ። ሲነሱም በዓይናቸው ስር
እምባቸውን ይጠራርጉ ነበር። ዛቻ አስከትለው ለቁጣቸው ማሳረጊያ አበጁለት።
"ግዴለም! ለ[ፍሎሬንቲኖ] ፔሬዝ እነግረዋለሁ። ራሱ ወሬ አቀባዩን ፈልጎ
ያጋልጠው። በቪዬትናም ብሆን ኖሮ፣ በጓደኛችሁ ላይ እንዲህ ስትቀልዱ
ብመለከት ሽጉጤን መዝዤ በደፋኋችሁ ነበር…።"

Wednesday, January 9, 2019
የሀሙስ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች
ዌልሳዊው የአርሰናል አማካይ አሮን ራምሴ በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ጁቬንቱስ ለመጓዝ ከስምምነት ላይ መድረሱን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል ።ጋዜጣው እንዳተተው ከሆነ ራምሴ የአምስት አመት ውል ይፈርማል።
(Guardian)
አትሌቲኮ ማድሪድ የ26 አመቱን ስፔናዊ የቼልሲ አጥቂ አልቫሮ ሞራታ በውሰት ወደ ዋንዳ ሜትራፖሊታኖ ለማዘዋወር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፤ ሲቪያም የተጨዋቹ ፈላጊ ነው።
(Goal)
ሪያል ማድሪድ በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ የሚፈለገውን ሴኔጋላዊውን የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ለማዘዋወር €90M አቅርቦ በመስራት ላይ ይገኛል።
(Il Mattino, via Talksport)
ዩናይትድ ሰርቢያዊውን የፊዮረንቲና ተከላካይ ኒኮላ ሚሊንኮቪች ለማዘዋወር ያለው ፍላጎት ከፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ስንብት በኋላ ቀዝቅዟል።
(ESPN)
ቶተንሀም የሳምፕዶሪያውን ተከላካይ ጆአኪም አንደርሰን ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ስፐርስ ይህንን የምታደርገው የቶቢ ኤልደርዊልድ በክለቡ መቆየት ጥያቄ ምልክት ውስጥ በመግባቱ ነው።
(Independent)
የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ማሪያ ባርቶሚዮ የ25 አመቱ ስፔናዊ አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ፍላጎቱ ከሆነ ከክለቡ መልቀቅ እንደሚችል ነግረውታል።ሱዋሬዝ ስሙ በስፋት ከአርሰናል ጋር በመያያዝ ላይ እንደሆነ ይታወቃል።
(Marca)
አርሰናል የፖርቶውን አማካይ ሄክቶር ሄሬራ ለማዘዋወር እየሰራ ይገኛል።መድፈኞቹ ሜክሲኳዊውን አማካይ የአሮን ራምሴ ቦታ እንዲሸፍንላቸው ይፈልጋሉ።
(Tutto Mercato Web)
ማንቸስትር ሲቲ የዌስት ሀሙን አይርላንዳዊ የ19 አመት አማካይ ዴክላን ሬስ በማዘዋወር የረዥም ጊዜ የፈርናንዲንሆ ተተኪ ማድረግ ይፈልጋል።

ከትላንት ማምሻ ጀምሮ ቸልሲ እና ጎንዛሎ ሂግዌን ተስማምተዋል ሚሉ መረጃዎች ሲዎጡ ነበር ዛሬ ረፋዱንም ተጠናክረው ወተዋል ምናልባትም ዝውውሩ በሰአታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል ቸልሲዎች ለሂግዌን በሳምንት እስከ 140ሺ.ፓ ለመክፈል ተስማምተዋል በክረምቱ ደግሞ በ36ሚ.ፓ የመግዛት ግዴታ ውስጥ መግባታቸው እና መስማማታቸው እየተነገረ ነው
ጆዜ ሞሪንሆ ቤኔፊካን እንዲያሰለጥኑ ፍላጎት እንዳላቸው የክለቡ ፕሬዛዳንት ሉይስ ፊሊፔ ቬራ ተናግረዋል በቅርቡ ሩይ ቪክቶሪያን ከሀላፊነት እንደተነሱ ይታወቃል ቬራ ሲናገሩም በቀጣዩ ሳምንት አዲስ ነገር ጠብቁ ጆዜን እስካሁን አላናገርኩትም ግን ቡድኑን መያዝ ሚፈልግ ከሆነ ነገ ቡድኑን መያዝ እንደሚችል እናገራለው ሞሪንሆ አሰልጣኙ እንዲሆን የማይፈልግ የለም ብለዋል
ዴኒስ ሱዋሬዝ አርሰናልን ሚቀላቀል ከሆነ ሄነሪክ ሚኪታሪያን አርሰናልን ሊለቅበት የሚችልበት እድል አለ ኡናይ ኤምሪ ዝውውሩ አሁን ቋሚ እንዲሆን ይፈልጋሉ ባርሴሎና ግን አሁን በውሰት ሰተው በክረምቱ በ20ሚ.ፓ ከፍሎ የማስፈረም አማራጭ ስምምነት ውስጥ ሚያስገባ ከሆነ ስፔናዊውን አማካይ ማግኘት ይችላሉ የሚል እምነት አላቸው ዝውውሩም ወደ መጠናቀቁ ደርሷል
ሪያል ማድሪድ ፒቴክን በውሰት ውል ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል በጣሊያን ሴሪአ 12ጎሎችን ያሥቆጠረውን ፒቴክን አምጥተው የጎል ማግባት ችግራቸውን ለመፍታት ይሄንን ፖላንዳዊውን ግብ አዳኝ ፈልገውታል
ባርሴሎናዎች የ19 አመቱን ፈረንሳዊ ተከላካይ ዦን ክላይቭቶዲቦን ከቱሉዝ በነፃ ለማስፈረም ተስማምተዋል በክረምቱ ወደ ካታሎንያ የሚያመራ ይሆናል
ማንችስተር ዩናይትድ የፊዮሬንቲናውን ሰርቢያዊ ተከላካይ ኒኮላ ሜሪንኮቪች ለማዘዋወር እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተሰምቷል አማካዩን አንድሬስ ፔሬራን የዝውውሩ አካል አድርገው ስለማቅረባቸው ተነግሯል ከዚህ ውጪ በቼልሲ እና አርሰናል የሚፈለገውን የካግላሪውን አማካይ ኒኮሎ ባሬላን ለማስፈረም ዩናይትዶች 30ሚ.ፓ አቅርበዋል
ባይርን ሙኒክ በአለም ዋንጫ ድንቅ ብቃቱን ያሳየውን የስቱትጋርቱን ቤንጃሚን ፓቫንን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል ባየርኖች ለልጁ ውል ማፍረሻ 35ሚ.ዩ ከፍለዋል ልጁም በአመቱ መጨረሻ ባየርንን ይቀላቀላል
አንድሬስ ኢኔስታ ስለ ኔይማር ወደ ባርሴሎና መመለስ ተጠይቆ ሲመልስ በእግር ኳስ ማይመስሉ ግን የሆኑ 100ሺ ነገሮችን አውቃለው ነገር ግን ኔማር ወደ ባርሴሎና ይመለሳል ብዬ አላስብም ብሏል ከአለማችን ምርጥ ተጨዋች አንደኛው ነውም የሚል አስተያየት ሰቷል

ኢኒዬሽታ፣ ያርኬና የዓለም ዋንጫ
ጸሀፊው ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ነው
Moments:
ኢኒዬሽታ፣ ያርኬና የዓለም ዋንጫ
ጎሉ ሊቆጠር እንደሆነ ልቦናዋ አውቋል። አይኗን በሁለት እጆቿ ሸፍና በጨለማ
ውስጥ ተደበቀች። ሆድ ባሳት። እያመነታች እጆቿን ገለጥ አድርጋ ወደ ቴሌቪዥኑ
ተመለከተች። እንደገና ወደ ጨለማው ገባች። ደግማ የእጆቿን መጋረጃ ገለጥ
አድርጋ አየች። አንድሬስ ኢኒዬሽታ ጎሉን አስቆጥሮ ይሮጣል። …ከዚያ በኋላ
ያልጠበቀችው ሆነ። አይኖቿን ማመን አቃታት። መላዋ ስፔን በደስታ ስካር
ስታብድ፣ እርሷ ተንሰቅስቃ አለቀሰች።
ጄሲካ ያርኬ እግር ኳስ ጨዋታን በቴሌቪዥን ከተመለከተች አንድ ዓመት
ደፍናለች። የህይወቷ ግማሽ አካል ሴት ልጁን ብቻ ለስም መጠሪያ ጥሎላት
ላይመለስ ሄዷል። ዳኒ ምን አይነት ሰው መሰላችሁ? የመልካም ሰው ልክ፣
አሳቢ፣ አፍቃሪና ተንከባካቢ ፍቅሯ ነበር።
ጄሲ ፉትቦልን ለፍቅረኛዋ ብላ ትመልከት እንጂ ጥሩና መጥፎ ጨዋታን እንኳን
መለየት አትችልም። ዳኒ ደግሞ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ነው። ከከተማ ውጭ
ጨዋታ ካለበት የባለቤቷን ጨዋታ፣ ለእርሱ ብላ በቴሌቪዥን መመልከቷ
የማይቀር ነበር። ከጨዋታ መልስ ማታ ቤት ሲገባ በግጥሚያው ላይ ስላሳየው
ብቃት ይጠይቃታል።
"ውዴ! ዛሬ ጨዋታዬን እንዴት አየሽው?"
ጥቂት አሰብ እያደረገች… "ዛሬ ብቃትህ ልዩ ነበር" ትለዋለች። ዳኒ ተሰጥኦውን
ባላሳየበት ጨዋታ ላይ የጄሲካ መልስ እንዲህ ነበር። ተቃራኒውን የተጠየቀች
ይመስል ድፍን ስታዲየም ካደነቀው በኋላ "ጥሩ አልተጫወትክም" ማለቷን
ለምዶታል።
እርሱም አይፈርድባትም፣ ይ'ረዳታል። እርሱን ማፍቀሯ ይበቃዋል። የዕለቱ
ውሎውና የባለቤቱ መልስ አራምባና ቆቦ መሆኑን ለምዶታል።
…በዚያ እርጉም ነሐሴ ዳኒ ከኤስፓንዮል ጋር ለቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት
ወደ ጣልያን አመራ። በወሩ በስምንተኛ ቀን ጠዋቱን በልምምድ አሳለፈ።
አመሻሹ ላይ በኮቬርቺያኖ በመኝታ ክፍሉ ገብቶ ከነፍሰ ጡሯ ፍቅረኛው ጋር
ስልክ እያወራ ሳለ ተዝለፍልፎ ወደቀ። የጤና ባለሙያዎች ከሞት ሊታደጉት
ተረባረቡለት። ለአንድ ሰዓት ልቡን ወደ መደበኛ ስራ ለማስገባት የተደረገው
ጥረት ሁሉ ያለ ፍሬ አብቅቶ ዳኒ በ26 ዓመቱ ይህን ዓለም ተሰናበተ።
ኤስፓንዮል ወደ ሃገሩ ሲመለስ፣ ጄሲካ እንደ ወትሮው ምሽቱን ስለማታውቀው
እግር ኳስ የሚጠይቃትን የህይወቷን ፍቅር በኤርፖርት አልተቀበለችውም።
ድምፁ በድንገት ተቋርጦ፣ ትንፋሽ አጥሮትና የሚናገርበትን አቅም አጥቶ
አልተሰናበታትም።
መጥፎውን ዜና ከሰማችባት ከዚያች ዕለት ወዲህ እግር ኳስን ማየት እርም
አለች። በቲቪ መስኮት ፊት ሳትቀመጥ አንድ ዓመት አለፈ። የአባትን ጣዕም
የማታውቀው የአንድ ዓመት ህጻን ልጇ እንኳን በቴሌቪዥን ጨዋታ
እንድትመለከት የእናት ፍላጎት አይደለም። እግር ኳስ የውስጥ እግር እሣት
ሆኖባት ቀረ።
አባቷን ለአንድ ቀን እንኳን ለማየት ያልታደለችው ማርቲና በዚያ ጨቅላ ዕድሜዋ
ለይታ የምታውቀው አንድ እግር ኳስ ተጫዋች አለ። የኢኒዬሽታን የማስታወቂያ
ምስል በባርሴሎና ከተማ ቢልቦርዶች ላይ ያየች እንደሆነ በብሩህ ፈገግታ
"እማዬ እዪው" እያለች ጣቷን ወደ ፖስተሩ መጠቆሟን ጄሲካ ለምዳዋለች።
ኢኒዬሽታና ያርኬ የልጅነት ጓደኛሞች ናቸው። አንድሬስ ለዳኒ ጓዳ ቤተኛ ነው።
ለጄሲካም ቅርብ ነው። በኋላም ማርቲናም ተላምዳዋለች። ባርሳ ከኤስፓንዮል
ጋር ከተጫወተ ማሊያ ይቀያየራሉ። የኢኒዬሽታን ማሊያ የሚፈልጉ ዳኒ ቤት
መጥተው ሳያገኙ አይሄዱም። ለጋሱ ዳኒም ይሰጣቸዋል።
ሁለቱ የልጅነት ጓደኞች በአንድ ከተማ ኖረዋል። ለስፔን ወጣት ብሔራዊ ቡድን
አብረው ተጫውተዋል። ከውጭ ሃገር ጉዞ ሲመለሱ፣ አንድሬስ መኪና
ስላልነበረው ዳኒ ከኤርፖርት ወደ ቤት ያደርሰዋል። ኢንዬሽታም ሌላ መኪና
አይፈልግም። "ታክሲ ሹፌር ሆኖልኝ ነበር" እያለ ይቀልድበት ነበር። ዳኒ የአንድ
ዓመት ታላቁ ነው። ፉትቦል ይበልጥ አቀራርቦ አንድ አካል አድርጓቸዋል።
የዳኒ ድንገተኛ ህልፈት ለኢኒዬሽታም ሞት ሆነ። ለጄሲ ደግሞ የሞት፣ ሞት።
ሁለቱም አንድ ጎናቸው ተገንጥሎ የወደቀ ያህል መንፈሳቸው ታወከ። ከአንጀት
በማይወጣ ሃዘን አረሩ።
ኢኒዬሽታ ባርሳን ተሰናብቶ ወደ ጃፓን ባመራ ጊዜ "…ከያርኬ ሞት በኋላ ውስጤ
ሞተ። ለሁሉ ነገር የነበረኝ ፍላጎት ቀዘቀዘ። ጉጉቴ ሁሉ ከውስጤ ተነነ…" በማለት
የልቡን ቁስል ለጋዜጠኞች ገልጦ አሳይቷል።
ሁሉ ከንቱ የሆነባት ጄሲካም ከእግር ኳስ ተመልካችነት ሸሸች። በቴሌቪዥም
ቢሆን እንኳን ላታየው ቆረጠች።
ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ስፔን ለ2010 የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ስትደርስ ግን
አላስቻላትም። ጄሲ በቴሌቪዥኑ ፊት ስትቀመጥ ያለፉትን 12 ወራት እንዴት
እንዳሳለፈች የሚያውቁት እናቷ ማመን አቅቷቸው በአንክሮ ተመለከቷት።
"እርግጠኛ ነሽ? እውን ጨዋታውን ትመለከቻለሽ?"
"አዎ እማዬ፣ ዛሬስ አያለሁ።"
ሆድ እንደሚብሳት ያውቃሉና እናት ማረጋገጫ መፈለጋቸው አያስገርምም።
ባለቤቷ በህይወት እያለ ይወድ እንደነበረው በሰዎች ተከባም ቢሆን ጨዋታውን
ለመመልከት መወሰኗ ከልብ ነበር።
ጨዋታው በ0-0 ውጤት ቀጥሎ፣ በጭማሪው ሰዓት አራተኛ ደቂቃ ላይ፣
ኢኒዬሽታ ወደ ጎሉ ተጠጋ።
"አንድ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ውስጤ ይነግረኝ ነበር…" ጄሲካ ያቺን ሰዓት
ታስታውሳለች።
"እንግዳ ስሜት ተሰማኝ።… እንዴት እንደሆነ ባላውቅም…፣ ዳኒ በዚያ ጨዋታ
ላይ እንደሚገኝ አምኜ ነበር። በዚያች ቅፅበት ጎሉ እንደሚቆጠርም ተረዳሁ።
"እናቴ 'ኧረ እዪው! እዪው! እዪው!…' ብላ ጮኸች።
"ማየት አይበለው!… አይኖቼን በእጆቼ እየሸፈንኩና እየገለጥኩ አየሁት።
በመጨረሻ ጨከን ብዬ ሳተኩር ኢኒዬሽታ ጎል አስቆጥሮ ሲሮጥ ተመለከትኩት።
ዕይታዬን ሳጠራ የለበሰው የስፔን ማሊያ በላዩ ላይ የለም።"
አንድ ዓረፍተ ነገር እንኳን ሳታቋርጥ ትዝታዋን መናገር አልቻለችም። ሳግ
በቆራረጠው ድምፅ ቀጠለች።
"ስፔንን ለዓለም ሻምፒዮንነት ያበቃችውን ብቸኛ ጎል ለባለቤቱ፣ ለልጆቹ ወይም
ለሌላ ማስታወሻነት ማበርከት ይችል ነበር። ኢኒዬሽታ ግን እንዲህ ነው…።"
አንድሬስ ኢንዬሽታ ማሊያውን አውልቆ ከውስጥ በለበሰው ነጭ ካኒቴራ ላይ
በማርከር የተፃፈውን መልዕክት ለዓለም አሳየ።
"Dani Jarque, siempre con nosotros" ይላል።
"ዳኒ ያርኬ፣ ምንጊዜም ከእኛ ጋር ነህ!"

Tuesday, January 8, 2019
የረቡዕ ማለዳ የዝውውር ዜናዎች
በጨራስ አጥቂ ችግር ውስጥ የሚገኘው ቼልሲ በውሰት ኤሲ ሚላን የሚገኘውን የ31 አመቱን አርጀንቲናዊ ጎንዛሎ ሂጎይን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሱዋል።
(Marca)
የቶተንሃሙ ሀላፊ ዳኒ ሌቪ ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ማስፈረም የሚፈልግ ክለብ £225M ማቅረብ አለበት ብለዋል፡፡ሪያል ማድሪድ የ26 አመቱን አማካይ በጥብቅ
አንደሚፈልገው ይታወቃል።
(AS - in Spanish)
የቶተንሃሙ አጥቂ ፈርናንዶ ሊዮሬንቲ ወደ ቀድሞ ክለቡ አትሌቲኮ ቢልባኦ በዚሁ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
(Mirror)
የአትሌቲኮ ቢልባኦው ሃላፊ ራፋኤል አልኮርታ የማንቸስተር ዩናይትዱን አማካይ አንደር ሄሬራ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ አንደሚፈልጉ ተናግረዋል።አዲሱ የቀያይ ሰይጣኖችሁ አለቃ ኦሊጉነር ሶልሻየር ግን ስፔናዊው አማካይ በክለቡ እንዲቆይ ይፈልጋል።
(Cadena Ser, via Mail)
ናፖሊዎች ለማንቸስተር ዩናይትድ ሴኔጋላዊውን ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ማስፈረም የሚችሉት በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት እንደሆነ ነግረዋቸዋል።
(ESPN)
የቀድሞ የአርሰናል አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር የካታር ብሄራዊ ቡድንን ለማሰልጠን በመነጋገር ላይ ናቸው።
(France Football)
ኢንተር ሚላን ኢቫን ፔሪሲችን ለማንችስተር ዩናይትድ በመሸጥ በምትኩ ሉካ ሞድሪችን ከሪያል ማድሪድ ለማዘዋወር ወጥኖ እየሰራ ነው።
(Tuttosport,via Calciomercato)
አርጀንቲናዊውን የኢንተር ሚላን የ25 አመት አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር የቼልሲው ባለቤት ሮማን አብረሃሞቪች ፍላጎቱ አላቸው።

የእለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አርሰናል ዴኒስ ስዋሬዝን ከባርሴሎና ለማስፈረም ተቃርበዋል የአርሰናል የጥር የመጀመሪያ ፈራሚ እንደሚሆን ተነግሯል የ24አመቱ ሱዋሬዝ በባርሳ የመሰለፍ እድል እያገኘ አደለም በዚ የውድድር አመት ሁለት ጨዋታዎችን ነው በላሊጋው ተሰልፎ መጫወት የቻለው ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ በግልፅ ተናግሯል ከአርሰናል ውጭ ዌስትሀም እንዲሁም የጣሊያኖቹ ሮማ ና ኤሲ ሚላን ናቸው አርሰናል ከሌሎች ክለቦች ልጁን የማግኘት እድላቸው የሰፋ ነው
ማንችስተር ዩናይትድ የጆዜን ስንብት ተከትሎ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሶልሻየርን መሾሙ ይታወሳል በውድድር አመቱ መጨረሻ ቋሚ አሰልጣኛቸውን እንደሚያሳውቁ ይጠበቃል ብዙ አሰልጣኞቹ ከዩናይትድ ጋር ስማቸው እየተያያዘ ይገኛል ነገር ግን እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ በመልበሻ ክፍል ውስጥ ተጨዋቾቹ ቋሚ አሰልጣኛቸው እንዲሆን ሶልሻየርን እንደሚመርጡ ተሰምቷል
የቼልሲውን አጥቂ አልቫሮ ሞራታን ለመውሰድ ፍላጎት እንዳለው ሲቪያ ታውቋል የተጨዋቹ ወኪል ሁዋን ማሎፔዝ ትላንት ወደ ሲቪያ አምርቶ ከክለቡ ሀላፊዎች ጋር ተነጋግሯል ተብሏል የሲቪያው አሰልጣኝ ማብሎ ማቼን የተጨዋቹ ፈላጊ ናቸው በተለይ ደግሞ ያለባቸውን የግብ ማስቆጠር ክፍተት ስላለባቸው እንደሱ ልምድ ያለው ተጨዋች ያስፈልገናል በሚል የክለቡን ሰዎች ማሳመናቸውን መረጃዎች ይዘው ወተዋል
አርሰን ቬንገር የኳታር ብ/ቡድንን እንዲያሰለጥኑ ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበር የፈረንሳዩ ፍራንስ ፉትቦል ይፋ አድርጓል ለ2022 ኳታር ለምታስተናግደው የአለም ዋንጫ ቬንገር አሰልጣኝ እንዲሆን ፈልገው ነበር ነገር ግን ቬንገር ጥያቄውን ሳይቀበሉ ቀርተዋል የቀድሞ የባርሴሎና ተጨዋች ፊሊክስ ሳንቼዝ ነው ቡድኑን እያሰለጠነ የሚገኘው አለም ዋንጫው መቃረቢያ ላይ ቡድኑ እያሳየው ባለው አቋም ፌዴሬሽኑ ደስተኛ አደሉም ለ2022 ጥሩ ቡድን ይገነባል የሚል እምነታቸው ተሟጡዋል በዛም ምክንያት ቬንገርን ለማናገር ጥረት አድርገዋል ጥያቄውን ውድቅ ቢያረጉባቸው
ቤልጄማዊው የ31 አመት አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ ወደ ቻይና ለማምራት መቃረቡን ዘገባዎች እያሳዩ ነው ቤጂንግ ዋን የተባለው ክለብ ለልጁ 11ሚ.ፓ አቅርቧል በተደጋጋሚ ጉዳት ለቶተንሀም የሚጠበቀውን ነገር ያላደረገው ዴምቤሌ በጥሩ መልቀቁ እንደማይቀር ተነግሯል
አርሰናል ቤልጄማዊውን ካራስኮን ከቻይና ለማምጣት የተሻለ እድል አለው የሚል መረጃ እየወጣ ነው ምናልባት ማንችስተር ዩናይትድ የተሻለ ክፍያ መክፈል ሚችል ከሆነ ብቻ ካራስኮን እና አርሰናልን ሊለያቸው የሚችለው
ወደሞናኮ እንደሚሄድ እርግጥ የሆነውን ሴስክ ፋብሪጋዝን ለመተካት ቼልሲ ሁለት ተጨዋቾች ላይ አይኑን አሳርፏል የካግላሪውን ኒኮሎ ባሬላን ወይም የዜኒትፒስበርጉን ሊዮናርዶ ፓራዴዝን ከሁለት አንዳቸውን በዚ ሳምንት ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል ለክለቡ ሰዎቾም ተተኪ እንደሚፈልጉ አሳውቋቸዋል ተብሏል
አቅራቢ ኢብራሂም ሙሀመድ
Monday, January 7, 2019
የፈርዲናንድ የህይወት ትራጀዲ
ጽሁፉ የጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ነው
Moments:
የፈርዲናንድ የህይወት ትራጀዲ
"ክቡራትና ክቡራን የዚህ ሽልማት አሸናፊ… ሪዮ ፈርዲናንድ!" የሚለው
የምስራች ከመድረክ ላይ ሲሰማ አዳራሹ በጭብጨባ ቀለጠ። ሪዮ ቄንጠኛ ሱፍ
ኮቱን ቆልፎ አጠገቡ ተቀመጠችውን ሴት ጉንጭ ስሞ ወደ መድረኩ አመራ።
ሜይ 14 ቀን 2018…።
የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል በቴሌቪዥን ዘጋቢ ፊልሞች ዘርፍ
"Being Mum and Dad" በሚለው በቢቢሲ ቴሌቪዥን በተላለፈው ፊልሙ
የባፍታ ሽልማት ማግኘቱ ነበር።
ባማረው የለንደን ሮያል ፌስቲቫል አዳራሽ ለሽልማቱ ምስጋናውን ሲያቀርብ ሪዮ
እምባ ይተናነቀው ነበር።
በሜይ 2015፣ ከጥቂት ወራት የካንሰር ህመም በኋላ ሬቤካ ፈርዲናንድ ከሪዮና
ከሶስት ህፃናት ልጆቿ በሞት ተለየች። ህመሙ ፈጥኖ በመላው ስውነቷ
በመዛመቱ ለ34 ዓመቷ ሬቤካ አጣዳፊ ነበር። ባለቤቱ ባላሰበው ፍጥነት ከጎኑ
የተለየችበት ሪዮ በድንገት ሰማይ ተደፋበት፣ ምድሩ ሁሉ ጨለመበት። ህፃናቱን
ያለእናት ስለማሳደግ ማሰቡ በራሱ ዳገት ሆነበት። ልጆቹን አይውጣቸው ነገር፣
ምን እንደሚያደርጋቸው ጨነቀው።
"ህይወቴ ሁሉ ጨለማ ውስጥ ገባ። ጓዳዬ ገብቼ ለብቻዬ ተንሰቅስቄ ማልቀስ
የዘወትር ልማዴ ሆነ። አልወጣልህ አለኝ። የሚሰማኝ የተለየ ስሜት ነበር። እንደ
እግር ኳስ ተጫዋችነቴ የመልበሻ ቤት መንፈስ የተጠናወተኝ ነኝና ስሜታዊ
ጉዳቴን ለማንም ማማከር አልፈለግኩም። ለራሴው ይዤው ተብከነከንኩ።
"ልጆቼ 'እናት የሌለን ለምንድነው?' ብለው ቢጠይቁኝስ? ምን መልስ ይኖረኛል?
…በሐዘንና ጭንቀት ተጎዳሁ። ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ከመጠን በላይ አልኮል
ማዘውተር ጀመርኩ።"
ምሽት ወደ ልጆቹ መኝታ ቤት ይገባል። አልጋቸው ጎን ሆኖ ከገጠመው ሃዘን ሌላ
ነገር ማሰብ አይችልም።
"የሬቤካ ከጎናችን መለየት ያብሰለስለኛል። ከዚያ ወደታችኛው ፎቅ እወርድና
በሃዘንና ተስፋ መቁረጥ ከአልኮል መጠጥ ጋር ግብግብ እይዛለሁ። አለቅሳለሁ፣
እጠጣለሁ፣ እጠጣለሁ፣ እጠጣለሁ…።"
ሎሬንዝ (11 ዓመት) እና ታቴ (9 ዓመት) ወንዶች ናቸው። ሶስተኛዋ ቲያ 6 ዓመቷ
ነበር። እናታቸውን ቢያጡም በአያታቸው ተፅናኑ። የሪዮ እናት መኖሪያ ቤት ልጆቹ
ለሚኖሩበት ሰፈር ቅርብ ስለነበር ህፃናቱ የአያታቸውን ፍቅር በማግኘታቸው
ደስተኞች ነበሩ። ከትምህርት ቤት በፊት፣ በኋላና በሌላም ጊዜ ህጻናቱ
የአያታቸውን ዳበሳና ምክር ለመዱ። ግን ይህም ብዙ አልቆየም። በጁላይ
2017፣ ሪዮ ባለቤቱን በሞት ከተነጠቀ ሁለት ዓመት ሳይደፍን የሚወዳት እናቱን
በተመሳሳይ በሽታ አጣ።
ካንሰር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሪዮ ፈርዲናንድን ያለ እናትና ሚስት፣ ልጆቹን
ደግሞ ያለ እናትና አያት አስቀራቸው። ልጆቹም በፈተና ውስጥ አለፉ።
"በህይወቴ ሁሉ ምሳ አዘጋጅቼ፣ ምሳ ዕቃ ቋጥሬላቸው አላውቅም። ሬቤካ
በህይወት ሳለች ማልደው ተነስተው፣ ቁርስ ተመግበውና ተዘገጃጅተው ወደ
ትምህርት ቤት ሊወጡ 10 ደቂቃ ሲቀራቸው እኔ ከአልጋዬ መነሳትን የለመድኩ
ሰው ነኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ምሳ የቋጠርኩላቸው ቀን ግን በጣም ረፈደባቸው።"
ሃዘኑ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ቤት ሰርቶበት ራሱን ስለማጥፋት ማሰብ
ጀመረ። አልኮል ማዘውተሩ ደግሞ ራስህን ግደል የሚለውን ርኩስ ሃሳብ
አበረተባት። ያን ጊዜ በርካታ ሰዎች ሊረዱት መጡ። የምክር አገልግሎትም
አላጣም። በመከራ የተልፈሰፈሰው የኳስ ሜዳ ጀግና የሚያሳሱትን ልጆቹን
እየተመለከተ ተፅናና። ለእነርሱ ሲል መኖር እንዳለበት ራሱን አሳመነ። እነርሱም
እንዲጠነክሩ የእርሱ መፅናት አስፈላጊ ነበር።
የከበደ ሃዘን ተጭኖት ከወደቀበት እንደ ምንም ሲነሳ ፈርዲናንድ "እናትም፣
አባትም ሆኖ መኖር" የሚለውን መፅሐፉን አሳተመ። የተጋፈጠው ፈተና
ተመሳሳይ ርዕስ ባለው የቴሌቪዥን ዘጋቢ ፊልም ላይ ተተረከ። ፊልሙን ያየ ሁሉ
ሪዮን አፅናናው።
"ከፊልሙ መለቀቅ በኋላ በየመንገዱ ላይ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ አዛውንቶችና
አያቶች ሲያገኙኝ ስለእግር ኳስ ማውራትን ትተው እንድበረታ በምክራቸው
ይደግፉኝ ነበር" ይላል ሪዮ - ስለዶክመንተሪው ሲናገር።
ሟች ሬቤካ፣ ሊዛ የተባለች ጓደኛ ነበረቻት። ከህልፈቷ በኋላ ሬቤካ ለሊዛ
የተናገረችውን ሪዮ የሰማው ዘግይቶ ነበር። ያቺ መልካም ሴት በሞት አፋፍ ላይ
ሳለች ስለሪዮ የወደፊት ህይወት ምኞቷን ለሊዛ ገልፃላታለች።
"ሪዮ የሌላ ሴት ስለመሆኑ ማሰብ በራሱ ለእኔ ሞት ነው። ነገር ግን ብቸኛ
ስለመሆኑ ማሰብ ደግሞ ይበልጥ የሞት፣ ሞት ይሆንብኛል። ስለዚህ እኔ ከሞትኩ
ከጎኑ የማትለይ አፍቃሪና ደጋፊ ታስፈልገዋለች። ሪዮ በህይወቱ ሁሉ ደስተኛ
እንዲሆን እፈልጋለሁና አፍቃሪ ማግኘት አለበት።"
ዘጋቢ ፊልሙ የባፍታን ሽልማት በማሸነፉ ስሙ ሲጠራ ፈርዲናንድ
ከመቀመጫው በመነሳት ኮቱን ቆልፎ የሳማት ሴት ኬት ራይት ትባላለች። የ27
ዓመቷ የሪያሊቲ ቴሌቪዥን ተዋናይት ተጫዋቹ ሃዘኑን እንዲረሳ ያስቻለችው፣
ሟች ባለቤቱ የተመኘችለት ሴት ሆና ተገኘች። በያዝነው የፈረንጆች ወር
መጀመሪያ በአቡዳቢ፣ ሪዮ ፈርዲናንድ ለሌላ ዘላቂ ህይወት በኬት ራይት ጣት
ላይ የቃልኪዳን ቀለበት አኖረ። ጥንዶቹ ሲተጫጩ ሶስቱም ህፃናት
በአጠገባቸው ቆመው የአባታቸውን ደስታ መመለስ ይመለከቱ ነበር።
ምንጭ - የጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ የፌስቡክ ገጽ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ!
ከሬዲንግ ጋር በነበረው ጨዋታ የተሻለ ነገር ቢያሳይም አሁንም ግን ሳንቼዝ
መልቀቅ እንደሚፈልግ ተዘግቧል አትሌቲኮ ማድሪድና ቫሌንሲያም ፈላጊዎቹ
ሆነዋል ሳንቼዝ ዩናይትድን የተቀላቀለው አምና በጥር የዝውውር መስኮት
እንደነበር ይታወሳል
ኤቨርተኖች የአታላንታው ተከላካይ ጂያንሉካ ማንቺኒ ኢላማቸው ሆኗል ጥሩ
ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ተጫዋቹ በውድድር አመቱ መጨረሻ የወደፊት
ውሳኔውን ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል ምንም እንኳን ኮንትራቱ 4 አመት
ቢቀረውም አታላንታዎች አሁንም እንዲያራዝም ይፈልጋሉ ኢንተርና ሮማም
ሌሎች የተጫዋቹ ፈላጊዎች ናቸው
ቸልሲ ካለም ዊልሰንን ማያገኙ ከሆነ ኤዲሰን ካቫኒን ለማስፈረም አስበዋል
ዩራጓዊውን የ 31 አመት የ ፒ ኤስ ጂ አጥቂ ለማምጣት እስከ 50 ሚ.ፓ
መመደባቸው ተዘግቧል
ፉልሀም የሊቨርፑሉን አጥቂ ዲቮክ ኦሪጊን በ15 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረም
ይፈልጋሉ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ላለመውረድ እየታገሉ መሆኑ ይታወቃል ወደ
ሊጉም የመጡት በአሁኑ ነው አዲሱ ካራቨን ኮቴጅ የሚገኙት አሰልጣኝ
ክላውዱዮ ራኔሪ ትኩረታቸውን ወደ ቤልጄየሚያው ኢንተርናሽናል እጥቂ
እድርገዋል እሱም በእዚህ ክለብ በተቀያሪ ወንበር ላይ ነው የሚገኘው
ከዎልፍስበርግ በውሰት የመጣው አጥቂ በዘንድሮ የውድድር አመት
በመርሲሳይድ ድረቢ ማስቆጠሩ ይታወሳል
በዘንድሮ የውድድር አመት ብዙም የመሰለፍ እድል ያላገኘው ፒተር ቼክ በጥር
ስለመልቀቅ እያሰበ ይገኛል ኡናይ ኤምሪም እሱ ከቡድናቸው ጋር አብሯቸው
እንደሚቆይ እርግጠኛ አይደሉም
ዩናይትዶች በሰፊው ስማቸው ከካራስኮ ጋር ተያይዟል የቀድሞ የአትሌቲኮ
ማድሪድ ተጨዋች ቀድሞ በሞናኮ ያሰለጠኑት እና ከሞናኮም እንዲለቅ
ምክንያት የሆኑት አሰልጣኝ አሁን የሚገኝበትን የቻይና ክለብ መቀላቀሉ
ይባሱንም ክለቡን እንዲለቅ እንደሚያስገድደው ታውቋል
ሊቨርፑል የtrabzonspor የ27 ዓመት ወጣት ለማስፈረም ተቃርቧል ሊቨርፑል
ለእዚህ ተጫዋች 27 ሚሊዮን ፓውንድ ሊከፍለው ነው የአዳም ላላንም የረጅም
ጊዜ ተተኪ ማረግ ይፈልጋል የርገን ክሎፕ ይህን ተጫዋች ከሲቲ አስጥለው
ማስፈረም ይፈልጋሉ የቱርክ ምርጥ ወጣት ተጫዋች የተሸለመው ይህ
ተጫዋች ክለቡ እስከ እዚህ ዓመት መጨረሻ እንዲያቆየው ይፈልጋል
ያቀረብኩላችሁ ኢብራሂም ሙሃመድ ነኝ

Sunday, January 6, 2019
የእሁድ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አልቫሮ ሞራታ በዚ ሲዝን 9 ጎሎችን ብቻ ነው ያገባው በፕሪሚየር
ሊጉ ደግሞ 5 ጎል ብቻ ለዚህም ነው ማውሪሲዮ ሳሪ በስፔኑ ኢንተርናሽናል ተጫዋች ላይ ተስፋ ቆርጠው ኤደን ሀዛርድን የአልቫሮ ሞራታን የማጥቃት ስራ የሰጡት ሳሪ ያለፈው ክረምት አሰልጣኝ ሆኖ ሲቀጠር ሂጉዌንን ወደ ሰማያዊዎቹ ማምጣት ፈልጎ እንደነበር ይታወቃል ሮናልዶ ጁቬንቱስን በመቀላቀሉ እና ሂጉዌን ለሮናልዶ ቦታ በመልቀቅ ወደ ሚላን ስለሄደ የሳሪ ምኞት ያለመሳካቱንም ነው ዘ ሰን ጋዜጣ የዘገበው አሁን ደግሞ አልቫሮ ሞራታን በሂጉዌን ሊቀያየሩ እንደሆነ እየተዘገበ ይገኛል
.
የማንቸስተር ሲቲው ወጣት ተጫዋች ብራሂም ዲያዝ በቀጣዮቹ 48 ሰአታት ውስጥ ወደ ሪያል ማድሪድ ሊዘዋወር እንደሚችል የዘገበው ኢ ኤስ ፒ ኤን ጋዜጣ ነው ዲያዝ በክረምቱ ውሉ ስለሚያልቅ በነፃ ዝውውር ከክለቡ ሊወጣ እንደሚችል ቢነገርም ሪያል ማድሪዶች ግን ከውሉ መጠናቀቅ በፊት 15 ሚሊየን ዩሮ በመክፈል ወደ ሳንቲያጉ በርናቤዉ ሊያመጡት እንደሚችሉ ፍንጭ ተሰቷል ምንጮች ዲያዝ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ወደ ማድሪድ ከተማ አቅንቷል ቢሉም አርብ እለት ደግሞ ማንቸስተር ሲቲዎች ልምምድ ሲሰሩ በካሜራ እይታ ውስጥ እንደገባ አረጋግጠዋል
.
በማን.ዩናይትድ ዕቅድ ውስጥ የነበረው የናፖሊው ተከላካይ ኩሊባሊ የማድሪድና ባርሳ ኢላማ ሆኗል እንደ Calcio Mercato ዘገባ ከሆነ ባርሳ 120€m አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል
.
አርሰናሎች የጁቬንቱሱን ተከላካይ መህዲ ቤናቲያን ማስፈረም ይፈልጋሉ መድፈኞቹ ራምሴን የዝውውሩ አካል በማድረግ በጉዳት እታመሰ ያለውን የተከላካይ መስመር ችግር በሞሮኳዊው ለመሸፈን አስበዋል
.
በክለቡ ቼልሲ ደስተኛ ያልሆነው ስፔናዊው ፋብሪጋዝ ሞናኮን ለመቀላቀል ተሰማማ ሞናኮዎች ለተጨዋቹ የ 3አመት ኮንትራት አቅርበውለታል ፊርማውን በአጭር ቀን ውስጥ ሊፈርም እንደሆነ ተረጋግጧል
.
ባለፈው ክረምት ከማንችስተር ዩናይትድ የ 3 አመት ኮንትራት ቀርቦለት ውድቅ በማድረግ በአትሌቲኮ ማድሪድ የቆየው ዲያጎ ጎዲን ኮንትራቱ በሚቀጥለው ክረምት ስለሚጠናቀቅ እና በአዲስ ኮንትራት ዙሪያ ከአትሌቲኮ ጋር ስላልተስማማ ዩናይትድ በክረምት በነፃ ወደ ኦልትራፎርድ ለማምጣት ድርድር ለመጀመር ተዘጋጅተዋል
.
ጁቬንቱስ አሁንም ተሰፋ አልቆረጠም የቀድሞ ኮከባቸውን ፖል ፖግባን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ካልቺዮ መርካቶ ዘግቧል
Saturday, January 5, 2019
የዕሁድ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች
ቼልሲ ለዩራጉዊያዊው የፓሪሰን ዤርመን ተጨዋች ኤዲንሰን ካቫኒ ዝውውር የሚሆን £50M ለፈረንሳዩ ክለብ አቅርቧል።ካቫኒ ከኔይማር መምጣት በኃላ በፓርክ ደ ፕሪንስ ደስተኛ እንዳልሆነ ይታወቃል።
(Sunday Express)
አርሰናል ስፔናዊውን አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ለማዘዋወር ከባርሴሎና
ጋር ድርድር የጀመረ ሲሆን በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮትም የማዘዋወር ዕድሉ ከፍተኛ ነው ተብሏል።ሱዋሬዝ በኤርኔስቶ ቫልቬርዴው ቡድን ውስጥ በቋሚነት መሰለፍ እንዳልቻለ ይታወቃል።
(Observer)
በርንማውዞች ቼልሲ ለ26 አመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ካሉም ዊልሰን የሚያቀርበውን የትኛውንም የዝውውር ጥያቄ ላለመቀበል ወስነዋል።
(Sunday Mirror)
ብራዚላዊው የ31 አመት ተከላካይ ዳቪድ ሊውዝ ትናትት ለቼልሲ የመጨረሻውን ጨዋታ ያደረገው ሴስክ ፋብሪጋዝ በእንግሊዝ ውስጥ ለበርካታ አመታት ከተጫወቱ ተጨዋቾች ከምርጦቹ መሆኑን ገልፆ እንደሚናፍቀውም ተናግሯል ።ፋብሪጋዝ በቴሪ ሄንሪ የሚሰለጥነውን ሞናኮ እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።
(Talksport)
የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሞኒ በማንቸስተር ዩናይትድ እየተፈለገ የሚገኘውን የ32 አመቱን ኡራጉዊያዊ ተከላካይ ዲያጎ ጎዲን በክለቡ ለማቆየት እየሰራ መሆኑን ተናገረ።
(Sunday Express)
ሩይ ቪቶሪያን ያሰናበተው የፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ ከማንቸስተር ዩናይትድ የተሰናበቱትን ጆዜ ሞሪንሆ ለመቅጠር ፍላጎት ቢኖረውም ጆዜ ግን ውድቅ አድርገውለታል ።
(Record - in Portuguese)
ማንቸስተር ሲቲ የ19 አመቱን ተጨዋች ብራሂል ዲያዝ ከሪያል ማድሪድ ይልቅ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ማዘዋወር እንደሚፈልግ ተነግሯል።ምክንያቱ ደግሞ ለሀገር ውስጥ ክለብ የሚሰጥ ከሆነ 40% ታክስ የሚያገኝ ሲሆን የማድሪድ ከሰጠው ግን 15% ነው የሚያገኘው ።
(Talksport)
ሪያል ማድሪድ በማንችስተር ዩናይትድ የሚፈለገውን ብራዚላዊውን የፖርቶ የ20 አመት ተከላካይ ኤደር ሚሊታኦ ለማዘዋወር ከፖርቹጋሉ ክለብ ጋር ድርድር ጀምሯል።

ጁቬንቱስ የአሰልጣኙን ማክሲሚሊያኖ አሌግሪን ኮንትራት ለማራዘም ፍላጎት አሳይተዋል ከቅርብ ግዜ ወዲህ እኚህ አሰልጣኝ በተለያዩ ክለቦች እየተፈለጉ ነው እንደ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድ የሰውዬው ፈላጊ ሆነው መተዋል ይሄንንም ተከትሎ ጁቬንቱስ ኮንትራቱን ለማደስ ፍላጎት አለው ሰውዬው በጁቬንቱስ እስከ 2020 ድረስ የሚያቆየው ኮንትራት አላቸው ነገር ግን የስፖርቲንግ ዳይሬክተሩ ፓራቲሲ አስተያየት ሰተዋል ቦርዳችን የአሰልጣኙን የወደፊት ቆይታ በተመለከተ እየተነጋገረ ነው የሚገኘው ስለዚ በጁቬንቱስ እንደሚቆዩ ተስፋ አደርጋለው ተጨማሪ ኮንትራት ለመስጠትም እየተደራደርን ነው ብለዋል
ዌልሳዊው አሮን ራምሴ ከጁቬንቱስ ጋር ቅድመ ኮንትራት እንደተፈራረም ተሰምቷል እንደውም በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ክለቡ ሊሄድ ይችላል ነገር ግን አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ተጨዋቹን በዚ የጥር የዝውውር መስኮት የመልቀቅ ፍላጎት የላቸውም ይሄን የውድድር አመት በክለቡ እንዲቆይ ይልጋሉ
ማውሪሲዮ ፖቸቲንሆ እና ማንችስተር ዩናይትድ ባለስልጣናት በድብቅ እየተደራደሩ እንደሆነ ተሰምቷል እንዲያውም ከወዲሁ አንዳንድ ተጨዋቾችን እንዲያስፈርሙላቸው ጥቆማ ሰተዋል ተብሏል ከነዚህም መካከል አንደኛው የሌስተር ሲቲው የአጥቂ አማካይ ጄምስ ማዲሰን አንደኛው ነው ፖቸቲንሆ ክለቡን ከያዙ የኤሪክሰንን ሚና ሊሰጡት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል ተብሏል
የስፔኑ ሴቪያ በቼልሲ ያልተሳካ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘውን አልቫሮ ሞራታን በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ ለቼልሲ ማቅረቡ ተሰምቷል ከሲቪያ በተጨማሪ የጣሊያኑ ኤሲ ሚላን የልጁ ቁጥር አንድ ፈላጊ መሆኑ ታውቋል
ቼልሲዎች የፒኤስቪውን ሄርቪን ክሎዛኖን በ36ሚ.ፓ ለመግዛት እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ ተነግሯል ሌላኛው ተጨዋቻቸው ካሉም ሁድሰንሆዶይ ግን የዝውውር መልቀቂያ የልቀቁኝ ጥያቄ እንዳስገባ ተነግሯል ባይርን ሙኒኮች ይሄን ተጨዋች ይፈልጉታል ክሪስቲያን ፑሊስች ወደ ቸልሲ መዘዋወሩን ተከትሎ ኦዶይ በክለቡ የመቆየት ፍላጎት እንደሌለው ተነግሯል ሙኒኮችም ለልጁ 30ሚ.ፓ አቅርቧል
የጣሊያኑ ኢንተርሚላን ሁለቱን የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር ተጨዋቾችን አሽሊ ያንግን እና አንቶኒዮ ቫሌንሲያን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ፍላጎት ማሳየታቸውን ጣሊያናዊው ታማኝ ጋዜጠኛ ዲማርዚዮ ተናግሯል ዝውውሩም ሚሳካ ከሆነ ኢንተሮች ያንግን በጥር ቫሌንሲያን ደሞ በክረምቱ ማስፈረም ይፈልጋሉ
አርሰናል የባርሴሎናውን አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝን ለማስፈረም ተቃርቧል አማካዩ ከዚህ በፊት ከኡናይ ኤምሬ ጋ በሲቪያ አብረው መስራታቸው ይታወቃል
ከዩናይትድ የአሰልጣኝነት መንበራቸው በቅርቡ የተነሱት ጆዜ ሞሪንሆ ከተለያዩ ክለቦች ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ወደ ሀገራቸው ፖርቹጋል በድጋሜ በመመለስ ቤኔፊካን ለማስለጥን እያጤኑበት እንደሆነ ተሰምቷል
ሜሱት ኦዚል አዲስ ኮንትራት የፈረመው ባለፈው ጥር ላይ ነው ስለዚህም በአርሰናል ይቆያል የወደፊቱን የምናይ ቢሆንም አእምሮውን የሚያስቀይር ምንም ነገር የለም ሲል ወኪሉ ኤርኩት ተናግሯል
ማንችስተር ዩናይትድ በጥር የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር የሮማውን ግሪካዊ ተከላካይ ኮስታስ ማኖላስን ለማስፈረም ተዘጋጅተዋል የተከላካዩ ውል ማፍረሻ £34 million ነው ዩናይትድም ልጁን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል

'ያ ምሽት ያ ማሊያ'
ፅሁፉ የጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ነው
Moments:
ያ ምሽት፣ ያ ማሊያ
(የአሸናፊውና ተሸናፊው ወግ)
"ስለዚያ የፍፃሜ ጨዋታ ሳስብ፣ የሚታወሰኝ የመጨረሻው 30 ደቂቃ ነበር"
ይላል ኤሪክ አቢዳል። ስለ2011ዱ ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ እያወራ ነው። ገና
ሊጠናቀቅ ግማሽ ሰዓት እየቀረው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች
መሸነፋቸውን አምነው ተቀበሉ። የባርሴሎናን የምሽቱን ኃያልነት ምንም አይነት
ጥረት ሊቀለብሰው እንደማይችል ዩናይትዶች ቀድመው ተረዱ። እንደው ቦክስ
አይደል ፎጣ አይወረወር ነገር!
የባርሳ ልጆች ይጫወቱታል። በእግሮቻቸው ቅብብል ሜዳውን በአይነ ህሊናዊ
መስመሮች ይሸረካክቱታል፣ ያለ እጅ ንክኪ ይከፋፍሉታል፣ ያለ ቢላዋ
ይበልቱታል። እኒያ ታላቅ ጀግና ሰር አሌክው ፈርጉሰን እንኳን ዓይኖቻቸው
በካታላኑ ጥበባዊ ትርምስ ቦዘው ስልት የተሟጠጠበት የጦር መሪ መስለዋል።
ኢኒዬሽታ ለቻቪ…፣ ቻቪ ለሜሲ ይሰጠዋል።… ከዚያ ቡስኬትስ ይመጣና
ይቀበላል፣ መልሶ ያቀብላል። ፒም-ፓም…፣ ፒም-ፓም…፣ ፒም-ፓም…።
"እንግሊዛዊያኑ ተጫዋቾች ተማረሩ" አቢዳል ስለመጨረሻው 30 ደቂቃ
ትውስታውን ቀጠለ።
"ዌምብሌይን ወደ ግዙፍ ሮንዶ (መሐል ባልገባ) ስለቀየርንባቸው ብስጭት
ገባቸው። ሊያቆሙን አቃታቸው። አቅመ ቢስ ሆኑ።
"የብልግና ቃላትን ጨማምረው የብስጭታቸውን ያህል ይናገራሉ። ምን
ቀራቸው…፣ ከፀሃይ በታች ባለ ስድብ ሁሉ ይጮሃሉ። ይገርማል። ከቡድን ጓደኞቼ
አንዳንዶቹ ተጫዋቾቹ በቋንቋ ምክንያት ምን እያሉ እንደሆነ አልገባቸውም ነበር።
እኔ ግን ተረድቼዋለሁ። "…በቃኮ! አልቆልናል፣ ሞተናልኮ። በቃ! ለምን
አይበቃችሁም?" ሲሉን ጨዋታው ሊያልቅ ገና 25 ደቂቃ ይቀረው ነበር።
ቻቪ፣ ኢኒዬሽታ፣ ቡስኬትስ ቀጠሉ። ፒም-ፓም…፣ ፒም-ፓም…፣ ፒም-ፓም…።
አቢዳል እንከን የለሽ የቡድን ስራ፣ ወደ ውብ ጨዋታ ሲቀየር እያስተዋለና ራሱም
እየተጫወተ ነበር። በህልም ዓለም የሚታሰበው ሁሉ እየሆነ ነው። ለእርሱ ልዩ፣
ከልዩም ልዩ ጨዋታ ነበር።
አቢዳል በመጀመሪያው አሰላለፍ ውስጥ ይካተታል ብሎ የገመተ አልነበረም።
በጉበቱ ላይ የካንሰር ዕጢ መገኘቱ ከተነገረ ገና ሁለት ወር መሆኑ ነው።
መጥፎው ዜና በተሰማ ማግስት ከጨዋታ በፊት መልበሻ ቤት ገብቶ ጓደኞቹን
አበረታቷል። ከሁለት ቀን በኋላ ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል ሲገባ፣ ምንም
እንዳልተፈጠረ ሁሉ ለተጨዋች ጓደኞቹ "ጉበቱን የሚሰጠኝ" እያለ ይቀልድባቸው
ነበር። ሜይ 28 ደግሞ በዌምብሌይ ለፍፃሜው ተሰለፈ።
"ልዩ የሆነብኝ ፑዮልና ቻቪ ዋንጫውን እንዳነሳ ዕድል ስለሰጡኝ ወይም
በዌምብሌይ የሞቀ ድባብ ምክንያት እንዳይመስላችሁ። በፉትቦሉ ጥራት
እንጂ…" ይላል።
ያኔ አንድሬስ ኢኒዬሽታ በችሎታው ተራራ ጫፍ ላይ ነበር። ዌምብሌይ ከጉዳት ነፃ
የሆነበት የመጀመሪያው የፍጻሜ ጨዋታ ሆነለት። እንደ እምቦሳ እየፈነጠዘ፣ እንደ
ልባም ፈረስ እየጎደፈረ፣ ኳሷን በተዓምራዊ ፍጥነትና ጥበብ ወደፈለገው ቦታ
እየላካት ያዛታል።
የኦርኬስትራው አካል ቢሆንም አቢዳል ተመልካችም ጭምር ነበር። ካታላኑ በኳስ
ቅብብል ያለድምፅ ያዜማሉ። ጥበብ በኢኒዬሽታ ያማረ መልኳን ስትገልጥ
ፈረንሳዊው ተከላካይ እየታዘበ ይደመማል።
ቻቪ የአቢዳልን ትውስታ ያጠናክራል።
"…አዎን! አቢ እውነቱን ነው። ሩኒ ወደ እኔ መጣና አነጋገረኝ። 'አይበቃችሁም
እንዴ? በቃ አሸንፋችኋልኮ' አለኝ። ሰዓቱ ግን 80ኛ ደቂቃ ገደማ ነበር። 'በቃ ኳሱን
ማንሸራሸራችሁ ይብቃ ' ይለኝ ነበር።…"
አያልቅ የለ የፍፃሜው ፊሽካ ተሰማ። ፔፕ ጋርዲዮላና ልጆቹ አሳምነው 3ለ1
አሸነፉ። ባርሳ የአውሮፓ ሻምፒዮን ተባለ።
ካርለስ ፑዮል የአምበልነቱን ጥብጣብ በፍቃደኝነት በአቢዳል ክንድ ላይ
አሰረው። ከካንሰር ህመም በህክምና ጥበብ የተመለሰው አቢ ዋንጫውን
በክብር ሲያነሳ ስኮልስ ባለ 18 ቁጥሩ ነጭና ቀዩን ማሊያ ለብሶ ትዕይንቱን ፈዞ
ይመለከታል። በእውነት ይህን ያህል ተበልጠን እንሸነፋለን ብሎ አልገመተም
ነበር።
በዚያች ምሽት፣ በለንደን የእግር ኳስ ካቴድራል ተሸናፊው ሰራዊት ዩናይትድ
ቢሆንም፣ የድል አድራጊዎቹን ልብ ቀድሞ በአድናቆት ያቀለጠ ተጫዋች ከዚያ
ወገን ውስጥ አለ። የባርሳ ከዋክብት ከፖል ስኮልስ ጋር መጫወትን ሲመኙ
ኖረዋል። ቻቪ እጅጉን ያደንቀዋል፣ ኢኒዬሽታ "ምነው ከእርሱ ጋር በአንድ ቡድን
ውስጥ ባጫወተኝ" እያለ አልሟል።
የእርሱን ማሊያ "እኔ እወስድ፣ እኔ እወስድ" እያሉ ሲጨቃጨቁበት አቢዳል
ሰምቷል። በዚያ ምሽት አድናቂዎቹ በድል ደስታ ሰክረው ሳለ ስኮልስ ግን ከእነ
ማሊያው ቆሞ የሽንፈቱን ራስ ምታት ያዳምጥ ነበር።
ተሸናፊው የአሸናፊዎቹን ፓርቲ እየታዘበ የዌምብሌይ ሜዳ አልበቃህ ብሎት፣
በእግሩ የነካው ሁሉ ወርቅ ሲሆንለት ያየው አንድሬስ ወደ እርሱ መጥቶ
ማሊያውን ሲጠይቀው ሳይደነቅ አልቀረም።
… ኢኒዬሽታ በተወለደበት ፎንቴያልቢያ የወይን እርሻ ባለቤት ነው። ከእርሻውም
ጎን የወይን ጠጅ መጥመቂያ ፋብሪካ አለው። እዚያው መኖሪያ ቤቱን ገንብቷል።
ከቤቱ ጓዳዎች በአንዱ፣ በወይን ጠጅ ማከማቻ ክፍል ግድግዳ ላይ በመስተዋት
ፍሬም ውስጥ አንድ ብርቅዬ ማሊያ በክብር ተሰቅሏል። ፖል ስኮልስ
በዌምብሌይዋ ምሽት የለበሰው ያ ማሊያ።

Friday, January 4, 2019
የቅዳሜ ማለዳ አዳዲስ ስፖርታዊ ዜናዎች
፨ቼልሲ በውሰት ኤሲ ሚላን የሚገኘውን የ31 አመቱን አርጀንቲናዊ እጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን ለማዘዋወር ከባለቤት ክለቡ ጁቬንትስ ወደ መስማማት ተቃርቧል ፤ አልቫሮ ሞራታም ወደ ኤሲ ሚላን በውሰት የሚጓዝ ይሆናል።
፨የቻይናው ሱፐር ሊግ ክለብ ቤጂንግ ሲኖቦ ጉዋን የ31 አመቱን ቤልጄሚያዊ የቶተንሀም አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።
፨ኤሲ ሚላን ስሙ በስፋት ከቶተንሀም እና ቼልሲ ጋር በመያያዝ ላይ ያለውን አይቮሪኮስታዊውን የ22 አመት አማካይ ፍራንክ ኬሲ ለማዘዋወር የሚፈልግ ክለብ €45M ማቅረብ አለበት ብሏል።
፨የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል አሮን ራምሴ በዚህ ወር ወደ ጁቬንትስ ከሚጒዝ እስከ አመቱ መጨረሻ በክለቡ እንዲቆይ ይፈልጋሉ።
፨የቀድሞው የቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ፒተር ኬናዮን ኒውካስትል ዩናይትድን ለመግዛት ከክለቡ ባለቤት ማይክ አሽሊ ጋር ንግግር ሊያደርጉ ነው ተብሏል።
፨ሊቨርፑል እንግሊዛዊውን የ30 አመት ተጨዋች አዳም ላላና በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ በየትኛውም ክለብ የመሸጥ ፍላጎት የለውም ።
፨የፓሪሰን ዤርመኑ አማካይ አድራን ራቢዮ እስከ አመቱ መጨረሻ በፓርክ ደ ፕሪንስ ቆይቶ በነጻ ወደ ባርሴሎና በአመቱ መጨረሻ የሚጓዝ ይሆናል ሲል ዘ ጋርዲያን አስነብቧል ።
፨ኦሊ ጉነር ሶልሻየር ማንቸስተር ዩናይትድ ከቀናት በፊት በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ተጨዋች ያስፈርማል ብሎ እንደማይጠብቅ ተናገረ።በተለይ ብዙዎች ቀያይ ሰይጣኖቹ የመሀል ተከላካይ ችግር እንዳለባቸው ቢናገሩም በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ቲያትር ኦፍ ድሪምስ የደረሰው ሶልሻየር ግን ዝውውር ላይ ክለቡ እምብዛም ፍላጎን እንደሌለው ተናግሯል ።
አቅራቢ አብዱልቃድር በሽር (የሪሀና ልጅ)

Subscribe to:
Posts (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...