Tuesday, January 15, 2019

የማክሰኞ ምሳ ሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ጀርመናዊው ኢንተርናሽናል ሜሱት ኦዚል በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከክለቡ እንዲሰናበት ይፈልጋሉ።ኤምሬ ከዝውውሩ በሚገኘው ገንዘብ ሁለት ተጨዋቾችን ለማዘዋወር አቅደዋል።ኦዚል በሳምንት £350,000k የሚከፈለው ሲሆን የክለቡ ከፍተኛ ተከፋይም ነው።
(Mail)



ቼልሲ ቤልጄሚያዊውን የጨዋታ ቀማሪ ኤድን ሃዛርድ የሚፈልግ ማንኛውም ክለብ £100M እንዲያቀርበለት ይፈልጋል።የሀዛርድ ስም በተደጋጋሚ ከሪያል ማድሪድ ጋር እንደሚያያዝ ይታወቃል።በተለይ ከሳምንታት በፊት ሃዛርድ ስለጉዳዩ ተጠይቆ "ሪያል ማድሪድ ለመሄድ አልፈልግም ብዬ አልዋሽም" ካለ ወዲህ የዚህ ዝውውር ጉዳይ ብዙ አያስባለ ነው።
(Telegraph)



ቶተንሃም በ ማንቸስተር ዩናይትድ በተሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው ሃሪ ኬን ለአንድ ወር ያክል ከሜዳ ላይ ሊርቅ እንደሚችል እየተነገረ ነው።በዚህም ምክንያት ስፐርስ የባርሴሎናውን አጥቂ ማልኮም በውሰት ለማዘዋወር ጥረት ጀምራለች።
(Guardian)



የዌስት ሀሙ አጥቂ ማርኮ አርናውቶቪች በዚህ ሳምንት ውስጥ የህክምና ምርመራውን አጠናቆ በ £35M ወደ ቻይናው ክለብ ቻይኒዝ SIPG ይዘዋወራል ተብሎ ይጠበቃል።
(Sun)



አልቫሮ ሞራታን ለማዘዋወር £40M  አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ሲቪያ ካቀረበው ገንዘብ በላይ የመክፈል አቅም ስለሌለው ስፔናዊው አጥቁ ወደ ዲዬጎ ሲሞኒው አትሌቲኮ ማድሪድ የመዘዋወር ዕድሉ እየሰፋ መጥቷል።
(Marca)



በኦሊጉናር ሶልሻየር ስር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ዴቪድ ዴሄያ በማንቸስተር ዩናይትድ ለመቆየት የሚፈልግ ሲሆን ደሞዙ ግን በሳምንት £300,000k እንዲሆንለት ይፈልጋል።
(Mail)



የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች በጊዜያዊነት ክለቡን የተረከበው ኖርዌያዊው አሰልጣኝ ኦሊጉናር ሶልሻየር በቋሚነት ዕድሉ ተሰቶት ቀያይ ሰይጣኖቹን ለረዥም ጊዜ እንዲያሰለጥን ይፈልጋሉ።
(Telegraph)



ቼልሲ የዜኒት ፒተርስበርጉን አርጀንቲናዊ አማካይ ሊዮናርዶ ፓራዴስ ለማዘዋወር ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን ለክለቡ £27M አቅርቧል።
(Mirror)



No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...