Tuesday, January 15, 2019
የማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
ኡራጋዊው የፓሪሴንት ጄርሜን አጥቂ ኤዲሰን ካቫኒ በፒኤስጂ ጫማውን መስቀል እንደሚፈልግ ተናግሩዋል በክለቡ እስከ 2020 የሚያቆይ ኮንትራት ያለው በ2013 ከናፖሊ የተቀላቀለው አጥቂ በ117 ጎል የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪም መሆኑ ይታወቃል እስከ 2020 በዚ ክለብ ነው መቆየት የምፈልገው ከ2020 ቡሀላ ግን የመጫወት አቅም ይኖረኛል ብዬ አላስብም እድሜዬም እየሄደ ስለሆነ ስለዚ እግር ኳስ የመጫወት ጊዜን ማጠናቀቅ የምፈልገው ወይም ጫማዬን መስቀል ምፈልገው በዚ ክለብ ነው
የቼልሲው አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ቸልሲን የመልቀቁ ነገር እርግጥ እየሆነ ነው ቅዳሜ እና እሁድን ያሳለፈው በማድሪድ ነበር እናም በማድሪድ ማሳለፉን ተከትሎ ስሙ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋ ተያይዟል ባሳለፍነው ሳምንት ስሙ በሰፊው ከሲቪያ ጋ መነሳቱ የሚታወስ ነው ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች ይፋዊ ጥያቄ እንዳላቀረቡ ነው መረጃዎች ሚያሳዩት
ቤልጄማዊው የቶተንሀም አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ ወደ ቻይና መሄዱ ተረጋግጧል ትናንት ከሰአት ወደ ቤጂንግ ጉዋን ነበር ሊያመራ ነው የተባለው ነገር ግን ከ4 ሠአታት ቡሀላ ከዚ ከቤጂንግ ጉዋን ጋ የነበረው ድርድር ባለመሳካቱ ሌላው የቻይና ክለብ ዴምቤሌን የማግኘት እድሉ ሰፍቷል ተብሏል
አሮን ራምሴን በነፃ ከአርሰናል ያገኙት ጁቬዎች አርሰናልን ለመካስ ሞሮካዊውን ተከላካይ መህዲ ቤናቲያን ለአርሰናል ለመሸጥ መስማማታቸውን የተለያዩ መረጃዎች ወተዋል
ቼልሲ የፋብሪጋዝን መውጣት ተከትሎ ተጨዋች ለማስፈረም እያሰሱ ይገኛሉ ሳሪ እናም የሱን ቦታ ለመተካት ሁለት ተጨዋቾች የቸልሲ ራዳር ውስጥ ገብተዋል የመጀመሪያው የካግሊያሪው ኒኮሎ ባሬላ ነው ሁለተኛው ደግሞ የዜኒትስበርጉ ሊያንድሮ ፓራዴዝ ነው በተለይ ደግሞ ለፓራዴዝ ይፋዊ የሆነ ጥያቄ አቅርበዋል ተብሏል ለዜኒቶች 26.8ሚፓ ለመክፈል ጠይቀዋል ተብሏል
ኤቨርተኖች የኢድሪስ አጋናጉዬን ዋጋ ለፓሪሰንት ጄርሜን አሳውቀዋል ተብሏል እንደሚታወቀው ፒኤስጂ የአድሪያን ራቢዮት በክለቡ መቆየት አጠራጣሪ መሆኑን ተከትሎ የሱን ቦታ ሚሸፍን አማካይ እየፈለጉ ይገኛሉ ስለዚ በፒኤስጂ ይፈለጉ የነበሩት አማካዮች አለን የናፖሊው አንዱ ነበር 89ሚፓ በመጠየቃቸው አንፈልግም ብለው ነበር እንዲሁም ዊሊያን ቬግልም ከዶርትመንድ እንዲሁም በፒኤስጂ የሚፈለግ ተጨዋች ነው ዶርትመንድ ደሞ አማካዩን መልቀቅ አይፈልግም ስለዚ ያላቸው አማራጭ የኤቨርተኑ አጉዬ ነበር 28 ሚፓ መክፈል ከቻላቹ መውሰድ ትችላላቹ ብለዋቸዋል
ኡናይ ኤምሬ ሜሱት ኦዚልን ለመልቀቅ ፍቃደኛ መሆናቸው ተነግሯል በዚ የዝውውር መስኮት በውሰት እንጂ በቋሚነት ማስፈረም ስለማይችሉ ኦዚልን በመልቀቅ ሌላ አዲስ ተጨዋች ማምጣት ይፈልጋሉ አሁን በወጣ መረጃ ለጁቬንቱስ እና ለኢንተር ሚላን ይሄንን ተጨዋች እንዳቀረበ መረጃዎች ይጠቁማሉ በሳምንት 350ሺፓ የሚከፈለውን ኦዚልን ሽጠው ሁለት አዳዲስ ተጨዋቾችን በቋሚነት ማስፈረም ይፈልጋሉ ኦዚል እና አርሰናል መለያየታቸው እየተቃረበ ይመስላል
ማንችስተር ዩናይትድ ቶተንሀም እና አርሰናል የሊሊያም ቱራምን ልጅ ማርከስ ቱራምን ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብተዋል የ21 አመቱ አጥቂ ለጋንጎ ነው እየተጫወተ የሚገኘው በ17ጨዋታዎች 10ጎሎችን አስቆጥሯል እንዲሁም ቅዳሜ እለት ጋንጎ ከሴንቲቲያን ያደረጉትን ጨዋታ ሶስቱም ክለቦች መልማዮቻቸውን ልከው ማርከስ ቱራምን እንደተከታተሉት ታውቋል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment