"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።
ፖግባ በኦልድ ትራፎርድ ያለው ውል በአመቱ መጨረሻ የሚጠናቀቅ ቢሆንም እስካሁን ግን ውሉን አላደሰም።
"ፖግባ ጁን ላይ ያለው ውል ይጠናቀቃል።ስለዚህ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ተናጋግረን የሚሆነውን እናያለን።ቱሪን አሁንም በፖግባ ልብ ውስጥ አለ።ፖግባ ወደ ጁቬንትስ የሚመለስበት ዕድል ሊኖር ይችላል።ያ ግን በጁቬንትስ ፍላጎት ላይም ይወሰናል።" ነው ያለው ራዮላ ከ Rai Sport ጋር በነበረው ቆይታ።
ፖግባ በዘንድሮው አመት በአራት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሰባት ለግብ የበቁ ኳሶችን በማቀበል እየመራ ሲሆን አስደናቂ ጅማሮም አድርጓል።
No comments:
Post a Comment