ማንቸስተር ዩናይትድ የቀድሞው ኮከቡን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ለማምጣት እየሰራ ነው።ጁቬንትስ በምትኩ ፈረንሳዊውን አማካይ ፖል ፖግባ ወደ ቱሪን ለመውሰድ ይፈልጋል።
(Gazzetta dello Sport via Express)
ቶተንሀም ብራዚላዊውን አጥቂ ጋብሬል ሄሱስ ከማንቸስተር ሲቲ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ሲቲ ደግሞ ሄሱስ ላይ ገንዘብ በመጨመር ሄሪ ኬንን ወደ ኤቲሀድ ማምጣት ይፈልጋል።
(Star)
ሁለት አመታትን በውሰት በአርሰናል ቤት ያሳለፈው ስፔናዊው አማካይ ዳኒ ሴባዮስ በቀጣዩ ሲዝን ወይ በሪያል ማድሪድ መጫወት ካልሆነ ደግሞ ሎስብላንኮዎቹ በቋሚነት እንዲሸጡት እንደሚፈልግ ተናግሯል።
(Mail)
ማንቸስተር ዩናይትድ ሄሪ ኬንን ለማዘዋወር እያደረገ ያለው ጥረት ብዙ መሰናክሎች እያጋጠሙት በመሆኑ አይኑን ዳግም ወደ ሌላኛው እንግሊዛዊ የዶርትሙንድ ተጨዋች ጄደን ሳንቾ አዙሯል።
(Mail)
በርንሌይ የ24 አመቱን እንግሊዛዊ የኖቲንግሀም ፎረስት ተከላካይ ጆይ ዎሮል ለማዘዋወር £10ሚ. አቅርቧል።
(Sun)
ኤሲ ሚላን እንግሊዛዊውን ተከላካይ ፌካዮ ቶሞሪ በቋሚነት ከቼሌሲ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ሰኞ ለድርድር እንደሚቀመጡም ይጠበቃል።
(Sport Witness)
ዛምቢያዊውን የሬድ ቡል ሳልዝቡርግ አጥቂ ፓትሶን ዳካን ለማዘዋወር ዌስት ሀም ፣ ሊቨርፑል ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንቸስተር ሲቲ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Zam Foot)
የጆዜ ሞሪንሆው ሮማ ግራኒት ዣካን ከአርሰናል ለማዘዋወር እየሰራ ነው።መድፈኞቹ £17ሚ. ለዝውውሩ ይፈልጋሉ።
(Gazzetta dello Sport)
No comments:
Post a Comment