Monday, May 17, 2021

የዕለተ ሰኞ ስፖርታዊ ዜናዎች

 ቤልጄሚያዊው አማካይ ዪዎሪ ቴልማዝ በአዲስ ኮንትራት ጉዳይ ከሌስተር ሲቲ ጋር መነጋገር ጀምሯል።የኤፍ ኤ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ቼልሲ ላይ ግብ ያስቆጠረው ቴልማዝ በቀበሮዎቹ ቤት የሁለት አመት ኮንትራት ይቀረዋል።

(Mail)






ብራዚላዊው የመስመር አጥቂ ዊልያን ከአርሰናል ጋር ለመለያየት ከጫፍ ደርሷል።መድፈኞቹ ለ32 አመቱ ተጨዋች የሚመጣን የዝውውር ጥያቄ ለመስማት ዝግጁ ናቸው።

(Fabrizio Romano, via Mail)






ባርሴሎና በአሁኑ ሰዓት በካታሩ አል-ሷድ የሚገኘውን የቀድሞ አማካዩን ዣቪ ሀርናንዴዝ የሮናልድ ኪውመን ተተኪ ለማድረግ በመስራት ላይ ነው።ኪውመን በካምፕ ኑ የተጠበቀውን ያህል ስኬታማ መሆን አልቻለም።

(ARA Esports, via Football Transfers)






ናፖሊ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ስፓኒያርዱን ተከላካይ ፓው ቶረስ ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የ24 አመቱ ተጨዋች በቪያሪያል ድንቅ ጊዜን አሳልፏል።

(La Gazzetta dello Sport - in Italian)







የቀድሞው የዩቬንትስ አሰልጣኝ ወይም የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ሌጀንድ ራውል ጎንዛሌዝ በሪያል ማድሪድ ዚዳንን የመተካት ዕድል እንዳላቸው ማርካ አስነብቧል።

(Marca)





ሪያል ማድሪድ በድጋሚ አሽራፍ ሀኪሚን ከኢንተር ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ሎስብላንኮዎቹ የቀድሞው ተጫዋቻቸውን ለመመለስ €50ሚ. መድበዋል።

(Calciomercato)







የዶርትሙንዱ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሚኬል ዞርክ ከSky ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ ኤርሊንግ ሀላንድ ተጠይቀው "በቀጣይ አመትም ከኛው ጋር ይቀጥላል" ሲሉ እንደማይሸጥ አስረግጠው ተናግረዋል።

(Sky)



የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሮናልድ ኪውመን ያለ ሊዮኔል ሜሲ ባርሳን ማሰብ ከባድ እንደሆነ ተናግረዋል።ኪውመን አርጀንቲናዊው ኮከብ በካምፕ ኑ ይቆያል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም አክለዋል።

(Goal)






አዲሱ የሮማ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ጂጂ ቡፎንን ወደ ክለቡ የማምጣት ምንም ፍላጎት የላቸውም።ሆነኛ አላማቸው ፖርቱጋላዊውን የዎልቭስ ግብ ጠባቂ ፓው ሎፔዝ ማስፈረም ነው ተብሏል።

(Calciomercato)







ሪያድ ማህሬዝ የእግር ኳስ ህይወቱን በማንቸስተር ሲቲ መጨረስ እንደሚፈልግ ተናገረ።በዚህ ሲዝን በሁሉም የውድድር አይነቶች 14 ግቦችን ያስቆጠረው አልጄሪያዊው ፤ በሲቲ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።

(Goal)


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...