Wednesday, May 12, 2021

የዕለተ ረቡዕ ስፖርታዊ ዜናዎች

 



ሮማ የ23 አመቱን እንግሊዛዊ ተከላካይ ቤን ኋይት ከብራይተን  ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ጆዜ ሞሪንሆ ተጫዋቹን በጥብቅ ይፈልጉታል።

(Sun)






አርሰናል የ24 አመቱን ፈረንሳዊ አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር አቅዷል።ዴምቤሌ በውሰት ከሊዮ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ተሰጥቶ አመቱን እያሳለፈ መሆኑ ይታወቃል።

(Telegraph)




ቼልሲ በአመቱ መጨረሻ ለቶማስ ቱሀል የሶስት አመት አዲስ ኮንትራት እንደሚያቀርብለት ይጠበቃል።አሰልጣኙ ስታንፎርድ ብሪጅ ከደረሱ አንስቶ ድንቅ ጊዜን በተለይ በሻምፒዮንስ ሊግ በማሳለፍ ላይ ናቸው።

(Mail)






ባርሴሎና ቦሲኒያዊውን አማካይ ሚራለን ፒያኒች ከቼልሲ ጋር በጆርጊንሆ ለመቀያየር ጥያቄ አቅርቧል።

(Sport, via Star)






ባርሴሎና ስፔናዊውን የ20 አመት ተከላካይ ኤሪክ ጋርሲያ በነፃ ዝውውር ወደ ካምፕ ኑ ማምጣቱ ተረጋግጧል።

(Goal)






ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን አጥቂ ሄሪ ኬን ለማዘዋወር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል።የዳኒ ሌቪው ቶተንሀም ግን ቀላል ተደራዳሪ ሆኖ አልተገኘም።

(Football Insider)






የጣሊያኖቹ ኢንተር ሚላን እና ላዚዮ ፈረንሳዊውን አጥቂ ኦሊቪየር ዢሩ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ መግባታቸው ታውቋል።

(Calciomercato - in Italian)







የሮማ አሰልጣኝ ለመሆን የተስማሙት ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ አርጀንቲናዊውን ግብ ጠባቂ ሮሜሮ ከማንቸስተር ዩናይትድ ለማዘዋወር ይፈልጋሉ።

(Express)





No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...