ኪሊያን ምባፔ የቀረበለትን አዲስ ኮንትራት የማይፈርም ከሆነ ፓሪሰን ዤርመን ግብፃዊውን ኮከብ ሙሐመድ ሳላሕ ከሊቨርፑል ለማዘዋወር ይሰራል።ምባፔ ስሙ በስፋት በሪያል ማድሪድ ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።
(Mirror)
የቶተንሀሙ እንግሊዛዊ አጥቂ ሄሪ ኬን ባርሴሎናን የመቀላቀል ፍላጎት አለው።ሆኖም የካታላኑ ክለብ የቦሩሲያ ዶርትሙንዱን ኤሪሊንግ ሀላንድ ማስፈረም የመጀመሪያ ዕቅዱ ነው።
(Sport)
በፓሪሰን ዤርመን ያለው ኮንትራት ክረምት ላይ የሚጠናቀቀው ጀርመናዊው አማካይ ድራክስለር የአንድ አመት ተጨማሪ ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል።
(Le Parisien)
የዎልቭስ አሰልጣኝ ኑኖ ኤስፕሪቶ ሳንቶ ክለቡን ሊለቁ እንደሆነ እየተሰማ ነው።ወኪላቸው ሆርኼ ሜንዴዝም ከአስቶን ቪላ ጋር መነጋገር ጀምሯል።
(Football Insider)
የቀድሞው የቼልሲ እና ዩቬንትስ አሰልጣኝ ማውሩዚዮ ሳሪ ወደ እንግሊዝ በመመለስ ከሁለቱ የሰሜን ለንደን ክለቦች ቶተንሀም እና አርሰናል አንዱን ሊይዙ ይችላሉ።
(Radio Punto Nuovo via Star)
ፖርቱጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ አዲስ ውል ሊቀርብለት እንደሆነ ተሰምቷል።በአዲሱ ውል መሰረት ተጨዋቹ ሳምንታዊ ደሞዙ በእጥፍ አድጎ £200,000 የሚያገኝ ይሆናል።
(Sun)
ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የመስመር አጥቂ ጄደን ሳንቾ ለማዘዋወር £80ሚ. ለቦሩሲያ ዶርትሙንድ አቅርቧል።
(Star)
የጀርመን እግር ኳስ ፌደሬሽን በአመቱ መጨረሻ ከባየርን ሙኒክ ጋር የሚለያዩትን ሀንሲ ፌሌክ የጆኣኪም ሎ ተተኪ አድርጎ አድርጎ ለብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነት እንዲያጫቸው ካርል ሄንዝ ሮሚንገ መክረዋል።
(Sky Germany - in German)
ምንም እንኳን ዩቬንትስ በሴሪ ኤው አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ጥረት እያደረገ ቢሆንም አንድሪያ ፒርሎ ከአሰልጣኝነቱ ለመልቀቅ ፍላጎት እንደሌለው ተናግሯል።
(Sky Italia via Tuttosport - in Italian)
No comments:
Post a Comment