Wednesday, May 5, 2021

የዕለተ ረቡዕ ስፖርታዊ ዜናዎች

 

በቅርቡ በደጋፊ በደረሰባቸው ተቃውሞ ግራ የተጋቡ የሚመስሉት የማንቸስተር ዩናይትድ ባለሀብቶች ፤ የግሌዘር ቤተሰቦች ተቃውሞውን ጋብ ለማድረግ እንግሊዛዊውን የቶተንሀም አጥቂ ሀሪ ኬን ለማዘዋወር መስራት ጀምረዋል።£90ሚ. ደግሞ ለዝውውሩ የተሰናዳ ገንዘብ ነው።

(Sun)






ሪያል ማድሪድ የ26 አመቱን እንግሊዛዊ የመስመር አጥቂ ራሂም ስተርሊንግ ለማዘዋወር £75ሚ. ለውሃ ሰማያዊዎቹ አቅርቧል።ስተርሊንግ በአመቱ መጨረሻ ኤቲሀድን እንደሚለቅ ይጠበቃል።

(Football Insider)






ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በወቅታዊ አቋም መዋዠቅ ምክንያት የጄደን ሳንቾ የሚጠይቀውን የዝውውር ዋጋ ዝቅ አድርጓል።በዚህም ምክንያት ከሊቨርፑል እና ማንቸስተር ዩናይትድ በተጨማሪ ቼልሲም የተጨዋቹ  ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል።

(Bild, via Football London)






ከቶተንሀም ጋር ከተለያዩ ሳምንታት ያስቆጠሩት ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በይፋ የጣሊያኑን ሮማ ለመያዝ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

(Official)






ባየርን ሙኒክ ስፔናዊውን የኢንተር ሚላን አማካይ አሽረፍ ሓኪሚ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።የሰሜን ለንደኑ አርሰናልም የ22 አመቱ ተጨዋች ፈላጊ ነው።

(Express)



የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በውሰት ቶተንሀም የሚገኘው ዌልሳዊውን ኮከብ ጋሬዝ ቤል ወደ ጉዲሰን ፓርክ በማምጣት ዳግም አብረውት መስራት ይፈልጋሉ።

(El Chiringuito, via Sport Witness)






ቶተንሀም ብራዚላዊውን የቤኔፊካ አጥቂ ካርሎስ ቪኒሺየስ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ከዚህ በፊት ተጫዋቹን በውሰት ለመውሰድ ሞክረው ያልተሳካላቸው ስፐርስ አሁን በቋሚነት ለማዘዋወር እየሞከሩ ነው።

 (Sky Sports)






የ53 አመቱ ጣሊያናዊ አሰልጣኝ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ ወደ አሰልጣኝነት ሊመለሱ ነው።ዋነኛ ማረፊያቸው የቀድሞው ክለባቸው ዩቬንትስ ሊሆን እንደሚችል የሚጠበቅ ሲሆን ሪያል ማድሪድም ፈላጊያቸው ነው።

(Tuttosport - in Italian)


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...