Monday, May 3, 2021

የዕለተ ሰኞ ስፖርታዊ ዜናዎች

 


የፓሪሰን ዤርመኑ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሊዮናርዶ ብራዚላዊውን ኮከብ ኔይማር ለተጨማሪ አመታት በክለቡ ለማቆየት እና ለማሳመን እየሰራ ነው።እስካሁን ግን የኔይማር ውሳኔ አልታወቀም።

(Marca)






ማንቸስተር ዩናይትድ ለፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ አዲስ ኮንትራት አቅርቦለታል።በአዲሱ ኮንትራት መሰረት ፖግባ የሚስማማ ከሆነ ሳምንታዊ £400,000 የሚያገኝ ይሆናል።በዚህ ውል ካልተስማማ ግን ቀያይ ሰይጣኖቹ ሊሸጡት ይፈልጋሉ።

(Mirror)




የዌስት ሀሙ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ በመጪው የዝውውር መስኮት ክለባቸው አጥቂ ለመግዛት እንደሚጥር ተናግረዋል።መዶሻዎቹ ፍላጎታቸው የቼልሲው ታሚ ኤብረሀም ሲሆን £45ሚ. አሰናድተዋል።

(Football London)






ሌስተር ሲቲ የ22 አመቱን ፈረንሳዊ የሊል አማካይ ባቦኩሬ ሱማሬ ለማዘዋወር £35ሚ. አቅርቧል።

(Sun)






ፔፕ ጓርዲዮላ "ተጨዋቾች በተለያዩ ቦታዎች ላይ የመጫወት ፍላጎት ከሌላቸው ማንቸስተር ሲቲ ትክክለኛው ቦታ አይደለም" ሲል ተናገረ።ፔፕ ተጨዋቾችን rotate በማድረግ እንደሚታወቅ ይታወቃል።

(Manchester Evening News)







የቀድሞው የቀያይ ሰይጣኖቹ ኮከብ ሮይ ኪን ማንቸስተር ዩናይትድ ለቀጣይ አመት ለፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮንነት መወዳደር ከፈለገ ሁለቱን እንግሊዛውያን ጃክ ግሪሊሽ እና ሀሪ ኬን ማስፈረም አለበት ብሏል።

(Sky Sports)







የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ዠርገን ክሎፕ ጊኒያዊው የ26 አመት አማካይ ናቢ ኪየታ ለረዥም ጊዜ በአንፊልድ የመቆየት ዕድል እንዳለው ተናገሩ።

(Mail)







ሆላንዳዊው የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠብቂ ኤድዊን ቫንደርሰን የኢድ ዉድ ዋርድን ቦታ ለመተካት መነጋገር ጀምሯል።

(ESPN)






ቶተንሀም የ18 አመቱን የኮረንቲያንስ ዊንገር ሮድሪጎ ቫራንዳ ለማዘዋወር ድርድር ላይ ነው።

(Sun)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...