Wednesday, March 31, 2021

የዕለተ ረቡዕ ስፖርታዊ ዜናዎች

 



ማንቸስተር ሲቲ ኤርሊንግ ሀላንድን ለማዘዋወር እያደረገ ያለው ጥረት አለመሳካቱን ተከትሎ አይኑን ሙሉ ለሙሉ ወደ እንግሊዛዊው የቶተንሀም አጥቂ ሀሪ ኬን አዙሯል።

(The Times)






በአመቱ መጨረሻ ከሲቲ ጋር እንደሚለያይ የተረጋገጠውን አርጀንቲናዊውን ኮከብ ሰርኺዮ አጉዌሮ ለማዘዋወር ማንቸስተር ዩናይትድ እየሰራ ነው።ቼልሲ ፣ ኢንተር ሚላን እና ፓሪሰን ዤርመንም ፈላጊዎቹ ናቸው።

(Foot Mercato, via Star)



አርጀንቲናዊ ምትሀተኛ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ የሀገሩ ልጅ የሆነው ሰርኺዮ አጉዌሮ ወደ ካምፕ ኑ እንዲመጣለት ይፈልጋል።ይህ ከሆነም ተጨማሪ ኮንትራት ለመፈራረም ዝግጁ ነው።

(Mundo Deportivo - in Spanish)






ሙሀመድ ሳላሕ ወደ ስፔን ወደፊት የሚሄድበት ዕድል እንዳለ መናገሩን ተከትሎ ከሁለት ሃያላን ክለቦች ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ጋር ስሙ እየተያያዘ ነው።

(Marca)






ኪልያል ምባፔ በቶኪዮ ለሚደረገው የኦሊምፒክ ጨዋታ ለፈረንሣይ ብሄራዊ ቡድን መጫወት እንደማይፈልግ ለፌድሬሽኑ አሳውቋል።ከዛ ይልቅ ወደ ፊት ስለሚኖረው ሁኔታ ማሰብ ይፈልጋል።የአለም ዋንጫ አሸናፊው ኮከብ በሊቨርፑል ፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ በጥብቅ ይፈለጋል።

(Le Parisien, via Mirror)



ማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ሊቨርፑል እና ቶተንሀም ኦስትሪያዊውን አማካይ ማርሴል ሳቢዘር ከአር.ቢ ሌብዚኽ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ናቸው።

(Bild, via Sun)






ኤቨርተን ኮሎምቢያዊውን ተከላካይ ይዬሪ ሚና ለመሸጥ ወስኗል።ቶፊዎቹ እሱን በመሸጥ እና ተጨማሪ ገንዘብ በማከል ካሊዱ ኩሊባሊን ከናፖሊ ለማምጣት እየሰሩ ነው።

(Football Insider)





ምንም እንኳን ለበርካታ ጊዜያት ስማቸው ሲያያዝ የቆየ ቢሆንም ፤ ማንቸስተር ሲቲ ኦስትሪያዊውን ተከላካይ ዳቪድ አላባ በዚህ ሰዓት ለማዘዋወር አይፈልግም።በአንፃሩ ቼልሲ እና ፓሪሰን ዤርመን አዲሶቹ የተጨዋቹ ፈላጊዎች ሆነዋል።

(Manchester Evening News)






ባርሴሎና በአመቱ መጨረሻ ከውል ነፃ ለሚሆነው የሊቨርፑሉ አማካይ ጂጂ ዋይናልደም የሶስት አመት ኮንትራት አቅርቦለታል።ዋይናልደም በቀጣይ ማረፊያው ካምፕ ኑ እንደሚሆን ይጠበቃል።

(Mundo Deportivo - in Spanish)





No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...