ሰርሂዮ አጉዌሮ በአመቱ መጨረሻ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር እንደሚለያይ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከወዲሁ የተለያዩ ክለቦች ፍላጎት እያሳዩ ነው።ፓሪሰን ዤርመን እና የፖርቱጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን ደግሞ ዋነኞቹ ናቸው።
(Todo Fichajes - in Spanish)
MEN እንዳወጣው መረጃ ከሆነ ደግሞ ባርሴሎናም የአርጀንቲናዊው የአራት ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ አጉዌሮ ፈላጊ ነው።ዩቬንትስ እና ሪያል ማድሪድም እንዲሁ።
(Manchester Evening News)
ቀውስ ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል ቁልፍ ተጨዋች የሆነው ሙሀመድ ሳላሕ ወደ ስፔን ክለቦች ሊጓዝ እንደሚችል ተናገረ።ሊቨርፑል በአመቱ መጨረሻ በርካታ ተጨዋቾችን እንደሚያጣ ይገመታል።
(Marca - in Spanish)
ማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ሊቨርፑል እና ቶተንሀም ኦስትሪያዊውን አማካይ ማርሴል ሳቢዘር ከአር.ቢ ሌብዚኽ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ናቸው።
(Bild, via Sun)
ኤቨርተን ኮሎምቢያዊውን ተከላካይ ይዬሪ ሚና ለመሸጥ ወስኗል።ቶፊዎቹ እሱን በመሸጥ እና ተጨማሪ ገንዘብ በማከል ካሊዱ ኩሊባሊን ከናፖሊ ለማምጣት እየሰሩ ነው።
(Football Insider)
ምንም እንኳን ለበርካታ ጊዜያት ስማቸው ሲያያዝ የቆየ ቢሆንም ፤ ማንቸስተር ሲቲ ኦስትሪያዊውን ተከላካይ ዳቪድ አላባ በዚህ ሰዓት ለማዘዋወር አይፈልግም።በአንፃሩ ቼልሲ እና ፓሪሰን ዤርመን አዲሶቹ የተጨዋቹ ፈላጊዎች ሆነዋል።
(Manchester Evening News)
ባርሴሎና በአመቱ መጨረሻ ከውል ነፃ ለሚሆነው የሊቨርፑሉ አማካይ ጂጂ ዋይናልደም የሶስት አመት ኮንትራት አቅርቦለታል።ዋይናልደም በቀጣይ ማረፊያው ካምፕ ኑ እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
ጀርመናዊው የቼልሲ አጥቂ ቲሞ ዋርነር በስታንፎርድ ብሪጅ ደስተኛ ነው።ተጨዋቹ ስሙ በተለይ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር ሲያያዝ የቆየ ቢሆንም በሰማያዊዎቹ ቤት የሚቆይ ይሆናል።
(Goal)
No comments:
Post a Comment