ኤቨርተንን ከተቀላቀለ አንድ አመት ብቻ የሆነው ኮሎምቢያዊው አጥቂ ሀሜስ ሮድሪጌዝ በአሁኑ ሰዓት የመርሲሳይዱን ክለብ መልቀቅ ይፈልጋል።
(Defensa Central - in Spanish)
ማንቸስተር ሲቲ በካምፕ ኑ ያለው ውል ሊያበቃ ወራት ብቻ የቀረውን እና አዲስ ኮንትራት ያልፈረመው ሊዮኔል ሜሲን አሁንም ከባርሴሎና የማዘዋወር ፍላጎት አለው።
(Sun)
ቼልሲ ጀርመናዊውን የባየርን ሙኒክ የ25 አመት ተከላካይ ኒኮለላስ ሱለ ለማዘዋወር ይፈልጋል።
(AZ - in German)
አዲሱ የቼልሲ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሀል የሞንቼግላድባሁን ጀርመናዊ አማካይ ጆናስ ሆፍማን አጥብቆ ይፈልገዋል።
(Bild - in German)
ሊቨርፑል እና ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የዌስት ሀም አማካይ ዴክላን ራይስ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የ22 አመቱ ተጨዋች በቼልሲም ይፈለጋል።
(Star)
ደቡብ ኮሪያዊው የቶተንሀም አጥቂ ሰን ሂውንግ ሚን በአሁኑ ሰዓት ስለ ኮንትራት ማውራት አስፈላጊ አይደለም ተብሏል።የ28 አመቱ ኮከብ በስፐርስ እስከ 2022-23 የሚያቆይ ኮንትራት አለው።
(Sun)
ቶተንሀም በአሁኑ ሰዓት ጆዜ ሞሪንሆን የሚያባርር ከሆነ £40ሚ. ካሳ መክፈል እንዳለበት ውላቸው ላይ ሰፍሯል።
(A Bola - in Portuguese)
የሌብዚኹ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ማን ወይም የሌስተር ሲቲው ብሬንደን ሮጀርስ በቶተንሀም ጆዜ ሞውሪንሆን ይተካሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው ዕጩዎች ናቸው።
(Mail)
ኦሌ ጉናር ሶልሻየር በአዲስ ኮንትራት ዙሪያ ምንም አይነት ውይይት አለማድረጉን ተናገረ።ሶልሻየር ውሉ በክረምት ይጠናቀቃል።
(TeamTalk)
No comments:
Post a Comment