Wednesday, February 17, 2021

የዕለተ ረቡዕ ስፖርታዊ ዜናዎች

 ማንቸስተር ዩናይትድ የመሀል ክፍሉን ይበልጥ ለማጠናከር ፤ የሪያል ማድሪዱን ኡራጓዊ አማካይ ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ለማዘዋወር እየሰራ ይገኛል።

(Sun)






ኤቨርተን ከዚህ በፊት ሊያዘዋውረው ሞክሮ ያልተሳካለትን ፤ የዩቬንትሱን አማካይ አድናን ራቪዮ ጉዳይ አሁንም እየሰራበት ይገኛል።

(Mail)







እስከ 2022 በፓርክ ደ ፕሪንስ የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ኪልያን ምባፔ በአሁኑ ሰዓት በፓሪሰን ዤርመን ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።ስለ ቀጣዩ ጊዜ ግን የሚሆነውን ማየት እንደሚሻልም አክሏል።

(RMC Sport, via Metro)






ኦስትሪያዊው ተከላካይ ዴቪድ አላባ በአመቱ መጨረሻ ውሉ ሲጠናቀቅ መጓዝ የሚፈልገው ወደ ሪያል ማድሪድ ሲሆን ስፓኒሽ ቋንቋም መማር ጀምሯል።ማድሪድ ግን በመጀመሪያ የራሞስን ጉዳይ መፍታት ይጀምራል።

(Mirror)






ማንቸስተር ዩናይትድ አሁን እየፈለገው ያለውን ኡፓማካኖ ከስድስት አመት በፊት 2015 ላይ በ£1.9ሚ. የማዘዋወር ዕድል አግኝቶ እንደነበር ወኪሉ ተናገረ።

(Mirror)




አሜሪካዊው አጥቂ ክርስቲያን ፑሊሲች እና ሞሮኳዊው ሐኪም ዚያች በአዲሱ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሀል ስር የመሰለፍ ዕድል በማጣታቸው ከሁለት አንዱ በክረምት የመሸጥ ዕድላቸው ሰፊ ነው።

(Star)






ቶተንሀም በአሁኑ ሰዓት ጆዜ ሞሪንሆን የሚያባርር ከሆነ £40ሚ. ካሳ መክፈል እንዳለበት ውላቸው ላይ ሰፍሯል።

(A Bola - in Portuguese)






የሌብዚኹ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ማን ወይም የሌስተር ሲቲው ብሬንደን ሮጀርስ በቶተንሀም ጆዜ ሞውሪንሆን ይተካሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው ዕጩዎች ናቸው።

(Mail)






ኦሌ ጉናር ሶልሻየር በአዲስ ኮንትራት ዙሪያ ምንም አይነት ውይይት አለማድረጉን ተናገረ።ሶልሻየር ውሉ በክረምት ይጠናቀቃል።

(TeamTalk)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...