ማንቸስተር ዩናይትድ ቤልጄምውያዊውን አማካይ ማርዋን ፌላኒ ለመውሰድ የሚፈልግ ክለብ ካለ ለመሸጥ ፈቃደኛ ሲሆን ከዝውውሩ የሚፈልገውም £15ሚ. ብቻ ነው።ኤሲ ሚላን፥ፖርቶ እና የቻይናው ክለብ ጉዋንግዙ ኤቨርግራንዴ የተጨዋቹ ዋነኛ ፈላጊዎች ናቸው።
(Mirror)
ቼልሲ የ31 አመቱን አርጀንቲናዊ የጁቬንትስ ንብረት ሆኖ በ ኤሲ ሚላን የሚገኘውን ጎንዛሎ ሂጎኢን ዝውውር በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንደሚጨረስ ይጠበቃል።
የኤሲ ሚላኑ አሰልጣኝ ጄናሮ ጋቱሶ ግን ሂጎይን ከክለቡ እለቃለው ብሎ አለነገረኝም ብሏል።
(Telegraph)
ሪያል ማድሪድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዴንማርካዊው የቶተናሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ላይ ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ሆኗል።ሎስብላንኮዎቹ ይህንን ዝውውር የመጨረስ ጥረታቸውን አጠናክረው አየቀጠሉ ሲሆን ፍሎረንቲኖ ፔሬዝም ወደ 'ጋላክቲኮስ' አስተሳሰብ የመመለስ ሀሳብ አላቸው።
(AS)
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ኦዚል ከክለቡ ቢለቅ እንደማይከፉ ከተናገሩ ወዲህ የጀርመናዊው አማካይ ስም ከተለያዩ ክለቦች ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።ዛሬ የወጡ ዜናዎች ደግሞ እንደሚጠቁሙት ኢንተር ሚላን ተጨዋቹን በውሰት መውሰድ ይፈልጋል።
(Mirror)
አርሰናል ቤልጄሚያዊውን ዊንገር ያኒክ ካራስኮ ከቻይናው ክለብ ዳሊያን ዪፋንግ የማስፈረም ፍላጎት ቢኖረውም ኦዚልን ካልሸጠ ግን ኤምሬ የተመደበላቸው በጀት ተጨዋቹን ለመግዛት አያስችላቸውም።
(Fox Sports Asia)
የቼልሲው አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ቸልሲን የመልቀቁ ነገር እርግጥ እየሆነ ነው ቅዳሜ እና እሁድን ያሳለፈው በማድሪድ ነበር እናም በማድሪድ ማሳለፉን ተከትሎ ስሙ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋ ተያይዟል ባሳለፍነው ሳምንት ስሙ በሰፊው ከሲቪያ ጋ መነሳቱ የሚታወስ ነው ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች ይፋዊ ጥያቄ እንዳላቀረቡ ነው መረጃዎች ሚያሳዩት።
(Goal)
ቤልጄማዊው የቶተንሀም አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ ወደ ቻይና መሄዱ ተረጋግጧል ትናንት ከሰአት ወደ ቤጂንግ ጉዋን ነበር ሊያመራ ነው የተባለው ነገር ግን ከ4 ሠአታት ቡሀላ ከዚ ከቤጂንግ ጉዋን ጋ የነበረው ድርድር ባለመሳካቱ ሌላው የቻይና ክለብ ዴምቤሌን የማግኘት እድሉ ሰፍቷል ተብሏል።
(Goal)
ቼልሲ ቤልጄሚያዊውን የጨዋታ ቀማሪ ኤድን ሃዛርድ የሚፈልግ ማንኛውም ክለብ £100M እንዲያቀርበለት ይፈልጋል።የሀዛርድ ስም በተደጋጋሚ ከሪያል ማድሪድ ጋር እንደሚያያዝ ይታወቃል።በተለይ ከሳምንታት በፊት ሃዛርድ ስለጉዳዩ ተጠይቆ "ሪያል ማድሪድ ለመሄድ አልፈልግም ብዬ አልዋሽም" ካለ ወዲህ የዚህ ዝውውር ጉዳይ ብዙ አያስባለ ነው።
(Telegraph)
ቶተንሃም በማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው 1-0 በተሸነፈበት ጨዋታ የቁርጭምጭሚት ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ሃሪ ኬን ለስድስት ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ተነግሯል።
No comments:
Post a Comment