Wednesday, January 16, 2019

የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


ፓውሊንሆ ወደ ቻይናው ጉዋንግዙ ኤቨርግራንዴ በቋሚነት ተዘዋውሯል ይህ ብራዚላዊ ኮከብ በ2017 ነበር ወደ ባርሴሎና በ40ሚፓ የተዘዋወረው ባለፈው ሲዝን ለባርሴሎና ትልቅ ግልጋሎት ሲሰጥ ነበር በላሊጋውም 9ግቦችን ማስቆጠር ችሎ ነበር በዘንድሮ ሲዝን ግን ለኤቨርግራንዴ በውሰት ተሰቶ ነበር ነገር ግን ይሄን ተጨዋች በቋሚነት የማስፈረም ስምምነት ነበራቸው ትናንት  የ30 አመቱን ፓውሊንሆን ከ42 እስከ 50 ዩሮ በሚጠጋ ቋሚ ማረጋቸው ታውቋል



ፉልሀም የቀድሞውን የሊቨርፑል አጥቂ ሆላንዳዊውን ሪያን ባብልን እስከዚ አመት መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል ከቤኪሽታሽ አስፈርመውታል



የፋብሪጋስን ቦታ ለመተካት ወደ ገበያ የወጡት ቸልሲዎች ለዜኒቱ ሊያንድሮ ፓርዴዝ የተሻሻለ ሂሳብ አቅርበውለታል ከዚህ በፊት 26ሚፓ አቅርበው ነበር ዜኒት 36ሚፓ ነው የምፈልገው ብሎ አሁን ደሞ ቸልሲዎች የተሻሻለ 31ሚፓ አቅርበዋል ከተጨዋቹ ጋር በግል ተስማምተዋል ተብሏል አራት አመት ተኩል በሳምንት 80ሺ ፓዎንድ እየከፈሉት ለማስፈረም ተስማምተዋል ነገር ግን አሁንም ከዜኒት ጋር አልተስማሙም



ካሊዱ ኩሊባሊ በጣሊያን እየደረሰበት ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት ከጣሊያን መልቀቅ እንደሚፈልግ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ ማረፊያው ደግሞ ዩናይትድ ሊሆን እንደሚችል እየተገረ የሚገኘው



የአትሌቲኮ ማድሪዱ ተከላካይ ዲያጎ ጎዲን ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል ተስማማ ኡራጋዊው ተከላካይ በመጪው ክረምት ኢንተርን በነፃ ይቀላቀላል ጎዲን ኢንተርን በሁለት አመት ውል ሚቀላቀል ሲሆን በአመት 6ሚዩ ክፍያ ያገኛል



ያያ ቱሬ ከግሪክ መልስ ወደ ስኮትላንድ አምርቶ ሴልቲክን ለመቀላቀል ተቃርቧል



ባርሴሎናዎች ሉዊስ ሱዋሬዝን ለመተካት የፍራንክፈርቱን አጥቂ ሉካ ዮቪችን ለማዘዋወር ጥረት እያደርጉ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው



ብዙዎቻችን ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ምናቃቸው ማርቲን ኦኔል አዲሱ የኖቲንግሀም ፎረስት አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል ሰሞኑ በተደጋጋሚ ከክለቡ ጋር ሲያያዙ የነበሩት የ66አመቱ አሰልጣኝ በይፋ መግባቱን ክለቡ ይፋ አድርጓል



የስፔን ላሊጋ ፕሬዝዳንት ሀቭዬር ቴባስ ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ስፔን ላሊጋ ቢመለሱ ደስ ይለኛል ብለዋል ከካታላን ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስተያየቱን የሰጡት ማድሪዶች ፍላጎት አላቸው እየተባለ ነው ሳንቲያጎ ሶላሬን እስከ 2021 በክለቡ የሚያቆየው ውል ቢኖረውም ፊዮሬንቲኖ ፔሬዝ ግን ጆዜ ሞሪንሆን ካገኙ አይጠሉም እየበባለ ነው



የአውሮፓ የእግር ኳስ ማህበር ቼልሲዎች ላይ ደጋፊዎች ላይ ከፀረ ሴማዊነት እና ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ጩኸት አሰምተዋል ሞልዲቪ ከተባለው የሀንጋሪ ክለብ ጋር ሲጫወቱ በሚል ክስ መስርቶባቸዋል የቼልሲው ሊቀመምበርም ብሩስ  ባክ ክለቡ እንደማይደግፈው እና ደጋፊዎች መቀጣት እንዳለባቸው ሲናገሩ ነበር አሁን ይህ ነገር ተግባራዊ ከሆነ የተወሰኑ ጨዋታዎችን በግማሽ ሜዳ እንደሚያደርግ ተነግሯል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...