Thursday, January 17, 2019

የዕለተ ሀሙስ ስፖርታዊ ዜናዎች


የሱዋሬዝ እድሜ መገፋት ተከትሎ ባርሴሎናዎች የተለያዩ አጥቂዎችን እየተመለከቱ ይገኛሉ ከሰሞኑ በተደጋጋሚ ከሰርቢያዊው አጥቂ ሉካ ዮቪች ጋር ስሙ እየተሳ ይገኛል አጥቂው በዘንድሮ የቡንደስሊጋ ውድድር 12 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል ባርሴሎናዎች የአያንትፍራንክፈርቱን አጥቂ የግላቸው ለማድረግ እንቅስቃሴም መጀመራቸውንም ዘገባው አስነብቧል



በክረምቱ ባርሴሎናን የተቀላቀለው ማልኮም ከባርሳ ለመልቀቅ ከጫፍ መድረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል በላሊጋው አንድ ጨዋታ ላይ ብቻ የተሰለፈውን ማልኮምን ለማስፈረም የተለያዩ የእንግሊዝ የጣሊያን እና የቻይና ክለቦች የልጁ ፈላጊ ሆነዋል



ቼልሲ እና ጁቬንቱስ በጎንዛሎ ሂግዌን የዝውውር ጉዳይ ላይ መስማማታቸው ታውቋል ተጨዋቹን እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ ለመውሰድ ነው የተስማሙት ውድድር አመቱ ሲጠናቀቅ ደሞ ለ12 ወራት የውሰት ውል የማራዘም መብት ይኖረዋል



የሀሜስ ሮድሪጌዝ ወደ አርሰናል መዘዋወር ዜና በሰፊው እየተነገረ ይገኛል ባየርኖች ይሄ አመት ሲጠናቀቅ በ37ሚፓ ማዘዋወር ይችላሉ  ይሄንንም ተከትሎ የባይርን ሙኒኩ ስፖርት ዳይሬክተር ሀሰን ሰሊሀሚዚች አስተያየት ሰተዋል በሁለተኛው የውድድር አመት አጋማሽ ተጨዋቹ የሚያሳየውን አቅሙን ተመልክተን በአመቱ መጨረሻ እኖስናለን ሚል አስተያየት ሰተዋል



የቶተንሀሙ አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን  ከ18 ወራት ቡሀላ ኮንትራቱ ይጠናቀቃል ይሄ የውድድር አመት ሲጠናቀቅ ኮንትራት የማይፈርም ከሆነ ቶተንሀም ሊሸጠው ይፈልጋል AS የተባለው የስፔን ጋዜጣ እንደዘገበው ይህንን ድንቅ ዴንማርካዊ ለማስፈረም ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ተፋጠዋል ተጨዋቹ ግን ወደ ሪያል ማድሪድ ማምራት ነው ፍላጎቱ ተብሏል



ወደ ጁቬንቱስ ማምራቱ እርግጥ ነው እየተባለ የተወራለት አሮን ራምሴ ዝውውሩን በትንሹም ቢሆን ቀዝቀዝ ሚያረገው ዜና ትናንት ተሰምቷል በጣሊያን ሱፐር ካፕ ሻምፒዮን የሆኑት የጁቬንቱስ አሰልጣኝ አሌግሪ ስለራምሴ ተጠይቀው ነበር ጋዜጠኛውም ራምሴን በጥር የዝውውር መስኮት የማስፈረም ፍላጎት አላቹ ተብለው ሲጠየቁ የአርሰናል ተጨዋች ነው አሁን ላይ ለማስፈረምም ጥረት እያደረግንም አደለም አሁን ባለን ስኳድ ደስተኛ ነኝ ብሏል



የቀድሞ የቸልሲ ግብ ጠባቂ ፒተር ቼክ ከትናንት በስቲያ በዚህ አመት ጓንቱን እንደሚሰቅል አሳውቆ ነበር እናም ቸልሲዎች የቀድሞ ልጃቸውን በዚህ አመት መጨረሻ ወደ ቸልሲ ለመመለስ አስበዋል ቸልሲዎችም ከተጨዋቹ ጋ ንግግር ጀምረዋል ቸልሲም ቼክን የክለቡን አካዳሚዎችን ወይም ወጣቶችን እንዲያሰለጥንላቸው ካሎነም የክለቡ አምባሳደር አርጎ መሾም እንደሚፈልጉ ተነግሯል

1 comment:

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...