Friday, January 18, 2019
የዕለተ አርብ ስፖርታዊ ዜናዎች
አርሰናል እና ዴኒስ ሱዋሬዝ ለመገናኘት ከጫፍ ደርሰዋል እንደ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘገባ አርሰናል ይህን የ25 አመት እስከ ዚህ የውድድር አመት መጨረሻ በውሰት ይወስደዋል ለዝውውሩም 2ሚዩ ይከፍላል ለውሰት ውሉ ባርሴሎና ይሄ ተጨዋች በቋሚነት እንዲፈርም ስለሚፈልጉ በቀጣይ አርሰናል 20ሚዩ ከፍሎ መውሰድ ይችላል
.
በተደጋጋሚ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ እየተያያዘ የሚገኘው ማርኮ አርናቶቪች ከዌስትሀም መውጫ በር ላይ ቆሟል ከቸልሲ እንዲሁም ከቻይና ክለቦች ለክለቡ ጥያቄ ቢቀርብም ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል አሁን ላይ የልጁ ወኪል ክለቡ ላይ ጫና በማሳደራቸው ለመልቀቅ ተዘጋጅተዋል አሰልጣኙ ፔሌግሪኒም በዝውውሩ ጉዳይ አስተያየት ሰተዋል ትክክለኛ ገንዘብ የሚመጣ ከሆነ እንሸጠዋለን ብለዋል ዌስትሀም ለዝውውሩ ከ40ሚፓ ይፈልጋሉ
.
ከሎሳንጀለስ ጋላክሲ ጋር ከተለያየ ቡሀላ ክለብ አልባ የነበረው የቀድሞ የአርሰናል እና የቸልሲ ተጨዋች አሽሊ ኮል ወደ ቀድሞ አጋሩ ክለብ ደርቢ ካውንቲ ሊያመራ እንደሚችል መረጃዎች አሳይተዋል
.
የዩናይትድ ተጨዋቾች ሶልሻየር በክለቡ ቋሚ እንዲሆን ፍላጎት አላቸው ተብሏል እንደ ዴይሊ ሜይሊ ዘገባ ከሆነ እስከዚ አመት መጨረሻ ኮንትራቱ ቢቆይም ሁሉም ተጨዋቾች ድጋፋቸውን ለሶልሻየር አሳይተዋል አሁን ላይ ዩናይትድ ተቀዳሚ ምርጫው አሁንም ፖቸቲንሆ ነው ነገር ግን የሱ ማይሳካ ከሆነ ሶልሻየርን ለመቅጠር ፍላጎት አላቸው
.
ቸልሲ ካሉም ሁድሰንን ላለማጣት እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ እስከ 70ሺፓ ሳምንታዊ ደሞዝ ሊያሳድጉለት ቃል እንደገቡለት ሚያሳይ የተለያዩ መረጃዎች ወተዋል ልጁ ግን አሁንም በቸልሲ ውሉን ማደስ እንደማይፈልግ ተነግሯል ለ18 አመቱ ሁድሰን ባየርን ሙኒክ 35ሚፓ አቅርቧል
.
የሂግዌን ዝውውር ሙሉ ለሙሉ ወደ መጠናቀቁ ደርሷል ታማኝ የሚባሉ የእንግሊዝ ሚዲያዎች እንደተቀባበሉት ከሆነ ሂግዌን ዝውውሩን በ24 ሰአት ያጠናቅቃል ብለዋል ዛሬ ማምሻውን ወደ ለንደን መቶ ሜዲካሉን በማድረግ ዝውውሩን ያጠናቅቃል ለሀሙሱም የሊግ ካፕ የመልስ ጨዋታ እንደሚሰለፍ ተነግሯል
.
ባርሴሎና በጥር አልያም በክረምት ሁለት ወሳኝ የሚባሉ ተጨዋቾችን ማስፈረም ይፈልጋሉ በባርሳ የሚፈለጉት ተጨዋቾች ፍራንክ ዲዮንግ እና ክርስቲያን እስቱዋኒን ከአያክስ እና ከጄሮና ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል የባርሴሎናውም አሰልጣኝ ቫልቬርዴ አዳዲስ ተጨዋቾችን ማስፈረም እንፈልጋለን ግን ስለልጆች መናገር አልፈልግም ብለዋል
.
በጉዳት ምክንያት ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን ያጡት ቶተንሀሞች በውሰት ተጨዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል ከተለያዩ ተጨዋቾች ጋር ስማቸው እየተያያዘ ይገኛል አሁን ደሞ ከእንግሊዝ ሳይወጡ የሊቨርፑሉን ዲቮክ ኦሪጊን የአጭር ጊዜ መፍትሄ አድርገው ለማስፈረም ጥረት ጀምረዋል ተብሏል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment