Friday, January 18, 2019

የቅዳሜ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

ሊቨርፑል ፖርቱጋላዊውን የ19 አመት የአጥቂ አማካይ ጃኦ ፌሊክስ ለማዘዋወር £61M ቢያቀርብም ቤኔፊካ ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።
(Correio da Manha - in Portuguese)



የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ዤርደን ክሎፕ ከ12 ወራት በፊት ለባርሴሎና በ£142M የሸጡትን ብራዚላዊውን አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ከተቻለ በድጋሚ ወደ አንፊልድ መመለስ ይፈልጋሉ።ኩቲንሆ ህይወት በካታላኑ ክለብ እምብዛም ምቹ እንዳልሆነችለት ይነገራል።
(Liverpool Echo)



ቡድኑን በማጠናከር ላይ የሚገኘው የሞናኮው አሰልጣኝ ቴሪ ሄንሪ የማንቸስተር ዩናይትዱን የ31 አመት አማካይ ማርዋን ፌላኒ በውሰት መውሰድ ይፈልጋል።
(RMC - in French)



ንብረተነቱ የጁቬንትስ የሆነው አርጀንቲናዊ አጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን ቼልሲን ለመቀላቀል ወደ ለንደን እንደሚያመራ ተነግሯል ፥ ሰን እንደዘገበው ከሆን በቀጣይ ሳምንት ሃሙስ በካራባኦ ካፕ ሰማያዊዎቹ ከ ቶተንሃም ላለባቸው ጭዋታ ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል።
(Sun)



ባየርን ሙኒክ ለቼልሲው የ18 አመት እንግሊዛዊ ዊንገር ካሉም ሂውደሰን-ኦዱው ሳምንታዊ 85,000k አቅርቧል።
(Sun)



ፈረንሳዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ አንቶኒ ማርሻል በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ለተጨማሪ አምስት አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ሊፈርም እንደሆነ ተነግሯል።የ23 አመቱ አጥቂ በአዲሱ አሰልጣኝ ኦሊጉናር  ሶልሻየር ደስተኛ መሆኑም ነው የተነገረው።
(Sky Sports)



ኤቨርተን ቤልጄሚያዊውን የቼልሲ አጥቂ ሚቺ ባትሹዋይ የማዘዋወር ፍላጎት ያለው ሲሆን ለዝውውሩም  £40M አሰናድቷል።የ25 አመቱ አጥቂ በውሰት በስፔኑ ክለብ ቫሌንሲያ ከቆየ በኋላ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ መመለሱ ይታወቃል።
(Sun)




በተደጋጋሚ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ እየተያያዘ የሚገኘው ማርኮ አርናቶቪች
ከዌስትሀም መውጫ በር ላይ ቆሟል ከቸልሲ እንዲሁም ከቻይና ክለቦች ለክለቡ
ጥያቄ ቢቀርብም ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል አሁን ላይ የልጁ ወኪል  ክለቡ
ላይ ጫና በማሳደራቸው ለመልቀቅ ተዘጋጅተዋል አሰልጣኙ ፔሌግሪኒም
በዝውውሩ ጉዳይ አስተያየት ሰተዋል ትክክለኛ ገንዘብ የሚመጣ ከሆነ
እንሸጠዋለን ብለዋል ዌስትሀም ለዝውውሩ ከ40ሚፓ ይፈልጋሉ።
(Goal)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...