Saturday, January 19, 2019

የቅዳሜ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


ሪያል ማድሪድ አሁንም ኤሪክሰንን እና ሀዛርድን ለማስፈረም ማሰቡን ማርካ አስነብቧል በተለይ ሀዛርድ ከቸልሲ የቀረበለትን የውል ማራዘሚያ አልፈርምም ማለቱ በክረምቱ ማድሪድን ለመቀላቀል ፍላጎት ስላለው ነው ተብሏል እንዲሁም 18 ኮንትራት የቀረውንም ኤሪክሰንን ማስፈረም ይፈልጋሉ



አርሰናሎች ፍራንቺስኮ ቲርካቲርናኮኦ የሚባል የፖርቱጋል ወጣት ተጨዋችን ከብራጋ ለማምጣት መልማዮቻቸውን ልከዋል ልጁ የአርሰናል የረጅም ጊዜ እቅድ እንደሆነም ተነግሯል ልጁ ከአርሰናል ውጭ በጁቬንቱስም እየተፈለገ ይገኛል



ቼልሲዎች ሊዮናርዶ ፓራቴስ የተባለውን የዜኒቱን አማካይ ለማስፈረም ቼልሲዎች ተቃርበዋል ፋብሪጋስ ክለቡን ከለቀቀ ቡሀላ የሱን ተተኪ በመፈለግ ላይ የሚገኙት ቸልሲዎች ከብዙ ድርድር ቡሀላ ዝውውሩ ለመሳካት ከጫፍ ደርሱዋል



ሜሱት ኦዚል ክለቡን ብትለቅ ይሻላል ብለውት እንደነበር ኡናይ ኤምሪ ለክለቡ ቅርብ የሆነው የቢቢሲ ጋዜጠኛ  ዴቪድ ኦርነስቴን ተናገረ  



ሊቨርፑል እና ቼልሲ የላዚዮውን አጥቂ ቺሮ ኢሞቢሌን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው ተብሏል የርገን ክሎፕ እንደውም እሁድ ከናፖሊ ላዚዮ የሚያደርጉትን ጨዋታ መልማዮችን እንደሚልኩ እየተነገረ ይገኛል



አንቶኒዮ ሳናብሪያን በቶተንሀም እየተኘለገ ይገኛል ፖቸቲንሆ በጉዳት ለብዙ ሳምንታት ከሜዳ የሚርቀውን ሀሪ ኬንን ለመተካት ፍላጎታቸው እሱ ነው ተብሏል




ሊቨርፑል ለቤነፊካው የ 19 አመት ታዳጊ ጆአኦ ፌሊክስ ሚዩ61 አቅርቦ ውድቅ እንደተደረገበት ዘገባዎች እያመላከቱ ነው ሊቨርፑል ወደ ሀያልነቱ እየተመለሰ መሆኑን ተከትሎ የበለጠ ለመጠንከር ዝውውሮች ላይ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል



በማድሪድና ጁቬንቱስ እየተፈለገ ሚገኘው የዩናይትድ ወጣት አጥቂ
ራሽፎርድ በክለቡ መቆየት እንደሚፈልግ እየተዘገበ ይገኛል ዩናይትድም ደሞዙን እጥፍ በማረግ አዲስ የረጅም አመት ኮንትራት ለማስፈረም ፍላጎት አለው



ሪያል ማድሪድ የፖርቶውን የመሀል ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል ከልጁ ወኪል ዊሊያኖ ቤርቶሎጂ ጋር ተነጋግረዋል ማድሪዶች ለተከላካዩ እስከ 50ሚ.ዩ ለመክፈል ፍቃደኛነታቸውን አሳይተዋል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...