Monday, January 14, 2019

የሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


የባርሴሎናው የግራ መስመር ተጨዋች ጆርዲ አልባ ከባርሴሎና ጋር ረጅም አመት መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሮ የወደፊት ቆይታው ላይ ግን እርግጠኛ እንዳልሆነ ተናግሯል በካምፕኑ እስከ 2022 የሚያቆየው ኮንትራት ቢኖረውም ባርሴሎናዎች ግን ከ2015 ቡሀላ በኮንትራት ጉዳይ አናግረውት አያውቁም ክለቡም ለልጁ ያን ያህል ፍላጎት እንደሌለው እና ልጁ ግን በክለቡ ቢቆይ ደስተኛ መሆኑ ተናግሯል



በባርሴሎና በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ብራዚላዊው የቸልሲ ተጨዋች ዊሊያን ክለቡን እንደማይለቅ ተናገረ በቼልሲ ደስተኛ ነኝ በቸልሲም ቆያለው 1አመት ከ6 ወራት ኮንትራት ይቀረኛል ይሄንን ውል አጠናቅቃለው በቀጣይነትም የ30 አመቱ ዊሊያን ከቸልሲ ሰዎች ጋር ድርድር እንደሚጀምርም ተነግሩዋል



አብዱላሂ ዱኮሬ ከዋትፎርድ መልቀቅ እንደሚፈልግ ተናገረ ይህንንም ለክለቡ መናገሩ ተናግሩዋል የ26 አመቱ ተጨዋች ከ3 አመት በፊት ነበር ክለቡን የተቀላቀለው በ78 ጨዋታ ዘጠኝ ግቦችን አስቆጥሯል አማካዩ ባሳለፍነው አመት የክለቡ ኮከብ ተጨዋች መባሉ ይታወሳል በቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፍ ክለብ መቀላቅል እንደሚፈልግም ተናግሯል



ማሪዮ ባላቶሊ አሁንም በኒስ ከአሰልጣኙ ጋ አሁንም አልተስማም አሁን ላይ ከኒስ መውጣቱ እርግጥ እየሆነነ ነው ፍራንስ ፉትቦል እንዳወጣው መረጃ አሁንም ማርሴ ተጨዋቹን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረገ ነው በሌላ መረጃ ደግሞ ልጁ ከማርሴ ይልቅ ወደ ጣሊያን መመለስ እንደሚፈልግም እየተነገረ ነው ነገር ግን የቀድሞ ክለቦቹ ተጨዋቹን የማስፈረም ፍላጎታቸው ስለቀነሰ እዛው ፈረንሳይ ውስጥም እንደሚቆይ እርግጥ ሆኗል



ጁቬንቱስን ለመቀላቀል ጫፍ ላይ የደረሰው አሮን ራምሴ ዛሬ ጠዋት በለንደን የጤና ምርመራውን አድርጉዋል አሁን ወደ ጁቬንቱስ መግባቱ እርግጥ ሆኗል የአምስት አመት ውል ይፈርማል በጁቬንቱስ በአመት 7ሚዩ ይከፈለዋል በሌላ ዜና የራምሴ መምጣት ሳሚ ከዲራን ከጁቬ እንዲወጣ ሊያደርገው ይችላል



የአትሌቲኮ ማድሪድ የመስመር ተከላካይ ሁዋን ፍራን በአትሌቲኮ መቆየት እንደሚፍልግ ተናግሯል ስፔናዊው የ34 አመት ተከላካይ በ2011 ነበር ከኦሳሱና አትሌቲኮን የተቀላቀለው በዚህ አመት መጨረሻ ነው ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ትናንትም ከጨዋታው ቡሀላ በሰጠው አስተያየት አዲስ ኮንትራት መፈረም ፈልጋለው ቀጣይ አመታትንም በክለቡ መቆየት እፈልጋለው ብሏል



የቀድሞ የፒኤስጂ የኒውካስትል ፓላስ ተጨዋች ፈረንሳዊው ሁዋን ካባይ ከአልናስር ክለብ ጋ መለያየቱ መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ የ33 አመቱ ተጨዋች ወደ እንግሊዝ ተመልሶ ወደ ቀድሞ ክለቡ የሚመለስበት እድል አለ ተብሉዋል የኒውካስትሉ አሰልጣኙ ቤኒቴዝ ተጨዋች እንደሚፈልጉ በግልፅ መናገራቸው ይታወሳል እናም  ይሄንንም ተከትሎ የቀድሞ ልጃቸውን በነፃ ማግኘት የሚችሉበት እድል አለ ሚል ዘገባ ወቱዋል



የኢንተር ሚላኑ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ጁሴፔ ማሮታ ስለ ኢካርዲ አስተያየት ሰተዋል ደጋፊዎች በማውሮ ኢካርዲ ዙሪያ ደጋፊዎች ምንም አይነት ስጋት ሊገባቸው አይገባም ብለዋል በክለቡ ያለው የውል ማፍረሻ 110 ሚዩ ነው ከጁን 1-15 ባለው ጊዜ ነው ክለቦች ከፍለው መውሰድ የሚችሉት ማለት ከጣሊያን ውጭ ያሉ ክለቦች ከነዚህም ውስጥ ባርሴሎና ፒኤስጂ ማድሪድ እየተፈለገ ይገኛል በኢንተር ግን እንደሚቆይ ተስፋ አደርጋለው ብለዋል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...