"ሶልሻየር ደስታችንን መልሶልናል ፥ ይሄ ትክክለኛው ማንቸስተር ዩናይትድ ነው" ዴሄያ
ዴቪድ ዴሄያ በጊዜያዊነት ማንቸስተር ዩናይትድን እያሰለጠነ የሚገኘው ኦሊጉናር ሶልሻየርን እውነተኛውን ዩናይትድ መልሶታል በማለት ከትናንቱ የስፐርስ ድል በኋላ ተናግሯል።
ዩናይትድ ከሶልሻየር መምጣት በኋላ በእጅጉ መሻሻሉ እየተነገረ ሲሆን በጆዜ ሞሪንሆ ስር ከነበረው የቡድን መንፈስም አሁን ያለው መነቃቃት ከፍተኛ ነው።
በስኳዱ ውስጥ ወደ በቃታቸው ከተመለሱ ተጨዋቾች አንዱ የሆነው እና በትናንቱ ፍልሚያ 11 ያለቀላቸው ኳሶችን ያዳነው ስፓኒያርዱ ግብ ጥባቂም አሁን ቡድኑ ላለበት ጠንካራ አቋም ኖርዊያዊው አሰልጣኝ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግሯል።
No comments:
Post a Comment