ወደ ጁቬንቱስ መግባቱ እርግጥ የሆነው አሮን ራምሴ አሁን ደግሞ አርሰናሎች ለጁቬንቱስ አዲስ ጥያቄ አቅርበዋል ጁቬንቱስ የጥር የዝውውር መስኮት ከሆነ ራምሴን የሚፈልገው ከሆነ መክፈል ያለባቸውን ገንዘብ ገልፀውላቸዋል አርሰናልም ለራምሴ 18ሚ.ፓ መክፈል ከቻላቹ አሁኑኑ እንለቅላቹሀለን ብለዋቸዋል
.
ሪያል ማድሪዶች መልማዮቻቸውን ወደ ጣሊያን ልከዋል በክረምቱ በ4.5ሚ.ዩ ወደ ጄንዋ የተዘዋወረውን ክሪስቶፎ ፒያቲክን ለማዘዋወር ፍላጎት አሳይተዋል በሴሪያው ምርጥ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘውን አጥቂ ለማስፈረም ፉክክር ከናፖሊ ይገጥማቸዋል ናፖሊዎች ለልጁ እስከ 60ሚ.ፓ ከፍለው የማስፈረም ፍላጎት አላቸው
.
ኢንተር ሚላኖች የዩናይትዱን ቀኝ መስመር ተመላላሽ አንቶኒዮ ቫሌንሲያን ለመውሰድ ተቃርበዋል በዩናይትድ 10አመት የተጫወተውን ቫሌንሲያን በክረምቱ በነፃ ለማስፈረም ተቃርቧል
.
የፒኤስጂው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል አንድ አስተያየት ሰተዋል ከዝውውር ጋር በተያያዘ ተጠይቀው ከዚ ቡሀላ እንቅልፍ የምተኛው ቡድኔ ተጨዋች ሲያስፈርምልኝ ብቻ ነው የሚል አስተያየት ሰተዋል ፔዤ አንድ የተከላካይ አማካይ ለማስፈረም ይፈልጋሉ ከነዚህ ውስጥ ኢድሪስ አጉዬ ዶኮሬ እንዲሁም ፋቢንሆን እየፈለጉ ይገኛሉ
.
ትናንት የፋብሪጋዝን ዝውውር ያጠናቀቀው የሄነሪው ሞናኮ ቤልጄማዊውን ሚኪ ባትሽዋይን በውሰት ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል ህክምናውን ዛሬ እንደሚያጠናቅቅ እና ነገ ዝውውሩን ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል ከሄነሪ ጋ በቤልጄም ብ/ቡድን አብረው መስራታቸው ይታወሳል በተጨማሪም ዝውውሩ ከተጠናቀቀ በድጋሚ ወደ ፈረንሳይ ተመልሶ ይጫወታል ባትሹዋይ በአንድ አመት ለሶስተኛ ጊዜ ነው በውሰት ሲሰጥ አምና በቦሩሲያ ዶርትመንድ እንዲሁም ዘንድሮ በቫሌንሲያ ያልተሳካ ጊዜ አሳልፉዋል ሞናኮም በጥሩ የዝውውር መስኮት ባትሽዋይ አምስተኛ ፈራሚው ሆኗል
.
ሪያል ማድሪድ የቶተንሀሙን ሀሪ ኬንን ለማስፈርም ፍላጎት አለው AS እንዳለው ግን ቶተንሀሞች ማድሪድ ሀሪ ኬንን ማስፈረም ከፈለጋቹ 350ሚፓ መክፈል አለባቹ ብለዋቸዋል ተጨዋቹ ላይም ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ እንደለጠፉበት ዘግቧል
.
በወጣቶች ላይ ቡድናቸውን በመስራት የሚታወቁት ቦሩሲያ ዶርትመንዶች ከአርጀንቲናው ቦካ ጁንየርስ አንድ ተጨዋች ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል የቦካው ፕሬዝዳንትም ዝውውሩን ይፋ አርገውታል ለ19አመቱ ሊያናርዶ ባሌርቢ ዶርትመንዶች 15ሚ.ፓ ለመክፈል ተስማምተዋል በዚህ ሳምንት መጨረሻ የህክምና ምርመራውን እንደሚያጠናቅቅ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል
.
የቶተንሀም ሆትስፐር የአዲሱ ስታድየም ግንባታ እስከዚ ሲዝን መጨረሻ ላይጠናቀቅ እንደሚችል ተነግሯል ስታድየሙ 1ቢ.ፓ ወጪ ተደርጎበታል ቢያንስ ማርች ወር ላይ ከክሪስታል ፓላስ ጋ በሚኖረው ጨዋታ ለመክፈት ፍላጎት ነበረው ክለቡ ነገር ግን ለዚ ላይደርስ ይችላል ተብሏል ይህ ዜና በርካታ የቶተንሀም ደጋፊዎችን አስቆጥቷል
No comments:
Post a Comment