Saturday, January 12, 2019
የቅዳሜ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
የፊት መስመር ተጨዋች ችግር ውስጥ የገባው ሪያል ማድሪድ ፊታቸውን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ኮከቡቹ ኤሪክሰን እና ሀዛርድ ላይ አይናቸውን ጥለዋል የሀዛርድ የረጅም ጊዜ ፈላጊ የሆኑት ማድሪዶች አሁን ደግሞ ከሱ በተጨማሪ ኤሪክሰንን ፈልገዋል ማድሪዶች ለሁለቱ ኮከቦች ከ200 ሚ.ፓ በላይ ለማውጣት ፍላጎት አሳይተዋል
ቼልሲዎች ከባርሴሎና የቀረበላቸውን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል በቼልሲ ቤት የ18ወራት ኮንትራት ያለውን የ30 አመቱን ዊሊያንን ለማስፈረም በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ውድቅ ተደርጎባቸዋል ባርሳም በመጨረሻ 50ሚ.ፓ+ማልኮምን ለቸልሲ አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበታል
ጁቬንቱስ የአሮን ራምሴን ዝውውር ወደ ማጠናቀቁ እየተቃረበ ነው ታዋቂው ጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ጂያን ሉካ ዲማርዚዮ ከሱፐር ኮፓ ጨዋታ ቡሀላ ጁቬንቱስ ይህንን ዝውውር ይፋ ያደርጋል የሚል መረጃ ሰቱዋል አሁን ደግሞ ኢስኮንም ከማድሪድ ለመውሰድ ዝግጅቱን እንደጨረሰ መረጃዎች እየወጡ ነው በክረምቱም ልጁን እንደሚያስፈርሙት ተማምነዋል የሚል መረጃ ወተዋል
የአጥቂ ችግር ያለበት ቼልሲ አሁንም ሂግዌንን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል ተጨዋቹም ዝውውሩ እንዲጠናቀቅ ክለቡ ላይ ግፊት እያደረገ እንደሆነ ተነግሯል በተያያዘ ዜና አልቫሮ ሞራታ በውሰት ወደ ባርሴሎና ሊያመራ ይችላል የሚል በርካታ መረጃ እየወጣ ነው
አድራን ራቢዮት በፒኤስጂ ደጋፊዎች መጠላቱን ሌዲስ ስፖርት አስነብቧል በዘገባውም ከፒኤስጂ ደጋፊዎች በተሰበሰበ ድምፅ 88% የፒኤስጂ ደጋፊዎች ዳግመኛ ይሄንን ማልያ እንዳይለብስ ብለዋል በዚህ አመት ውሉ የሚጠናቀቀው ራቢዮት ኮንትራት ቀርቦለት አልፈርምም ማለቱ ይታወሳል ምናልባትም ወደ ባርሴሎና ወይ ባየርን ሙኒክ ሊያመራ ይችላል
በውሰት ብቻ ተጨዋች ማስፈረም እንደሚፈልጉ የተናገሩት ኡናይ ኤምሪ በውሰት ሊያስፈርሙዋቸው የሚችሉዋቸው ተጨዋቾች ዴኒስ ሱዋሬዝ እና ኤቨር ባኔጋ ናቸው የሱዋሬዝ ዝውውር በቅርብ ሊጠናቀቅ ይችላል ተብሏል ሁለቱም ተጨዋቾች ከኤምሪ ጋር አብረው ሰርተዋል በክረምቱ ደግሞ እስማኤል አሳር የሚባለውን የሬን ተጨዋች የማምጣት ፍላጎት አላቸው
ፉልሀሞች አሌክሳንደር ሚትሮቪችን ለማስፈረም ከአንድ የቻይና ክለብ ጥያቄ መቶላቸው ውድቅ አድርገውባቸውል የቻይናውም ክለብ ለፋልሀም ጠንካራ የዝውውር ጥያቄ አቅርበው ነበር ለሚትሮቪች ዝውውር ከ50ሚ.ፓ በላይ ቢያቀርቡም ጥያቄው ውድቅ ሆኗል
በኒውካስትሉ ጨዋታ ጉዳት የደረሰበት ፖል ፖግባ ለእሁዱ የዌምብሌ ጨዋታ 100% ዝግጁ እንደሆነ አሰልጣኝ ኦሊጎነር ሶልሻየር ተናግረዋል
ዳቪድ ሉዊዝ ኮንትራቱ ማይታደስለት ከሆነ ወደ ቀድሞ ክለቡ ቤኔፊካ መሄድ ይፈልጋል ተብሏል ከዛ ውጪ በስኮላሬ የሚሰለጥነው የብራዚሉ ፓልሜራስም ዳቪድ ሉዊዝን የመውሰድ ፍላጎት አለው ተብሏል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment