ባርሴሎና ፊሊፔ ኩቲንሆን ለማዘዋወር ለሚፈልጉ ክለቦች በሩን ክፍት ማድረጉ እየተነገረ ነው።ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ የቀድሞ ብራዚለዊ የሊቨርፑል ተጨዋች ዋነኛ ፈላጊ ነው።
(Calciomercato, via Star)
ባርሴሎና በይፋ ብራዚላዊውን የቼልሲውን ዊንገር ዊልያን ለማዘዋወር ማክሰኞ ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ከተደረገበት በኋላ በድጋሚ ገንዘብ ጨምሮ ጥያቄ ሊያቀርብ ነው።
(Standard)
ቼልሲ የካጊላሪውን ጣሊያናዊ አማካይ ኒኮላ ባሬላ ለማዘዋወር በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሷል።የዜኒቱን አርጀንቲናዊ አማካይ ሊዬንድሮ ፓራዴስም ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።
(Telegraph)
የኔይማር ወኪል የሆነው ወላጅ አባቱ ብራዚላዊው የ26 አመት የአለማችን ውዱ ተጨዋች ወደ ቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና መመለስ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
(Express)
ሊቨርፑል እና ፉልሀም እስራኤላዊውን የራቢ ሳልዝቡርግ የ26 አመት አጥቂ ሞያኔስ ዳቡር ለማዘዋውር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Estadio Deportivo - in Spanish)
ጁቬንትሶች በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት ፈረንሳዊውን የ25 አመት የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ፖል ፖግባ በድጋሚ ወደ ቱሪን ለመመለስ የሚፈልጉ ሲሆን ቀያይ ሰይጣኖቹ በዝውውሩ ላይ ዳግላስ ኮስታ ከታከለበት ሊያጤኑበት ይችላሉ።
(Tuttosport, via Calciomercato)
አርሰናል አሮን ራምሴን ለጁቬንትስ ሲሰጥ ሞሮኳዊው ተከላካይ መህዲ ቤናቲያ የዝውውሩ አካል ሆኖ ወደ ኤምሬትስ እንዲመጣ ይፈልጋል።
(Gazzetta dello Sport, via Metro)
ባርሴሎና ስፔናዊውን የቼልሲ አጥቂ አልቫሮ ሞራታ በውሰት ለመውሰድ ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሲቪያ እና አትሌቲኮ ማድሪድም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(Sport - in Spanish)
የአርሰናሉ አምበል ላውረንት ኮሼልኒ ከሞናኮ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
(Le10 Sport, via Mirror)
No comments:
Post a Comment