Friday, January 11, 2019

የአርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


በባይርን ሙኒክ በውሰት ውል እየተጫወተ የሚገኘውን ሀሜስ ሮድሪጌዝ ውል ለማደስ እያቅማማ የሚገኘው ሙኒክ ልጁን ሊያጣ ተቃርቧል ሀሜስ በተለያዩ ክለቦች በጥብቅ እየተፈለገ ነው የእንግሊዞቹ አርሰናል እና ሊቨርፑል እንዲሁም ጁቬንቱስ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል ነገር ግን ከሁሉም በላይ ሙኒክ ልጁን ቋሚ አርጎ የማስፈረም መብት አለው



የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ በዝውውር ጉዳይ ለአርሰናል ደጋፊዎች አስደንጋጭ ነገር ተናግረዋል በዚህ የዝውውር መስኮት ተጨዋቾችን የመግዛት አቅም የለንም ነገር ግን በውሰት ተጨዋቾችን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል



ከዩናይትድ የተባረሩት ጆዜ በዚህ ሳምንት የቤኔፊካው ፕሬዝዳንት እሳቸውን ለማምጣት ፈልገው እንደነበር አስተያየት ሰተው ነበር ጆዜም ትናንት ለዚ ጥያቄ መልሳቸውን ሰተዋል ቤኔፊካን የማሰልጠን ፍላጎት እንደሌላቸው እና በቅርቡም ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል ከዛም ባለፈም በቤይን ስፖርት በተንታኝነት እንደሚሰሩ ተረጋግጧል



የሞልድ ማኔጂንግ ዳይሬክተር እስከዚ የውድድር አመት መጨረሻ ነው የተስማማነው አሰልጣኛችንን ለዩናይትድ ስንሰጥ ስለዚ በጊዜው ይመለሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን አሁን በእቅዳችን ውስጥ ያለው ፕላን A ፕላን B ሶልሻየር ወደኛ እንደሚመለስ ነው ሌላ ምንም አይነት እቅድ የለንም ሌላም አሰልጣኝ የማምጣት ፍላጎት የለንም ብሏል



የሳውዝሀምብተኑ ቻርሊ ኦስቲን ቅጣት ተላልፎበታል በ20ኛ ሳምንት ከሲቲ ጋ በነበራቸው ጨዋታ በጣቱ ምልክት በማሳየት ያልተገባ እና ደጋፊዎችን የሚያበሳጭ ደርጊት ፈፅሟል ኤፌውም ክስ መስርቶበት ነበር ተጨዋቹም ሁለት ጨዋታዎችን ተቀቷል ሳውዛንብተን ከሌስተር እና ከደርቢ የሚያደርጋቸው ጨዋታ ያመልጡታል



ባርሴሎና ዊሊያን ላይ ያለው ፍላጎት አሁንም ተነስቷል ባለፈው ክረምት ሶስት ጊዜ ጥያቄ ለቼልሲ  አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸው ባርሴሎናዎች አሁንም ድጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል ክረምት ላይ ዊሊያንን ሲያጡ ከቦርዶ ማልኮምን ማስፈረማቸው ይታወሳል እና አሁን ላይ ይሄንን ተጨዋች በዝውውሩ ላይ ለማካተት አላቸው



እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ኤቨርተን ሚኪ ባትሽዋይን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ነገር ግን ኤቨርተኖች ዝውውሩን በቋሚነት ነው ማረግ ሚፈልጉት ቸልሲዎች ደሞ ጥሩ አጥቂ እስኪያገኙ ድረስ በቋሚ ዝውውር መሸጥ አይፈልጉም



የላስቬጋስ ፖሊስ የሮናልዶን የዲኤንኤ ሳምፕል እንዲመጣለት ጠይቋል ምክንያቱም ከአስገድዶ መድፈር ጋ በተያያዘ ክስ እንደሚጠብቀው እና ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል መረጃዎች እያሳዩ ይገኛሉ

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...