Thursday, January 10, 2019
ሀሙስ ምሽት የወጡ ስፖርተዊ ዜናዎች
በዚ የዝውውር መስኮት ቤልጄማዊው ያኒክ ካራስኮ ወደ አርሰናል የመምጣት እድሉ ሰፊ ሆኗል ልጁም ወደ አርሰናል ለመምጣት ከክለቡ ጋር ተስማምቷል ተብሏል በአመት እስከ 10ሚ.ዩ ለመክፈል አርሰናሎች ተስማምተዋል ልጁ በኤሲሚላን በጥብቅ ቢፈለግም ምርጫውን ግን የለንደኑን ክለብ ምርጫው አድርጓል
አልቫሮ ሞራታ በአትሌቲኮ ማድሪድ እና በባርሴሎና እየተፈለገ ይገኛል ባርሴሎና የሱዋሬዝን እድሜ መግፋት ተከትሎ ተተኪ እያፈላለገ ይገኛል ከነዚህም ውስጥ አልቫሮ ሞራታ አንዱ ነው አትሌቲኮም ማድሪድ የኮስታ መጎዳት እና አቋም መውረድን ተከትሎ ግሪዝማንን የሚያጣምር ጥሩ ሚባል አጥቂ ይፈልጋሉ ምርጫቸውንም ሞራታን አርገውታል
ዌስትሀም ከአንድ የቻይና ክለብ ለማርኮ አርናቶቪች የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ለ29 አመቱ አጥቂ 35ሚፓ ቢያቀርቡም ክለቡ ዌስትሀም ውድቅ አድርገውታል ለልጁም ከ50ሚፓ በላይ ክፍያን ይፈልጋሉ
ቸልሲዎች ሂግዌንን የማስፈረም ፍላጎታቸውን ቀንሰውታል አሰልጣኙ ሳሪ በናፖሊ አብረውት የሰሩትን ተጨዋች ማስፈረም ይፈልጋሉ ዝውውሩም ቶሎ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋሉ ነገር ግን የቸልሲዋ ዳይሬክተር እድሜው 31 ለሞላው ተጨዋች ይሄን ያህል ገንዘብ ማውጣት አልፈለጉም ይሄን ተከትሎ በሳሪ እና በቸልሲ ባለስልጣናት መካከል ችግር ሳይፈጠር አይቀርም ተብሏል ከዚህ በፊት ኮንቴም በዝውውር ጉዳይ ከቼልሲ ባለስልጣናት በተለይ ከቴክኒክ ዳይሬክተሯ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቶ ሀላፊነቱን እንዳጣ ይታወቃል አሁን ደሞ በሳሪ እና በቸልሲ ቦርድ መካከል ችግር እየተፈጠረ ነው
አንደር ሄሬራ በዩናይትድ ኮንትራት የማደስ ጉዳይ ላይ ንግግር እያደረገ እንደሆነ ተነግሯል ተጨዋቹ ሶልሻየር ከመጣ ቡሀላ በተደጋጋሚ የመሰለፍ እድል እያገኘ ይገኛል በውድድር አመቱ መጨረሻ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ሄሬራ ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል
ፓሪሰንት ጄርሜን ሎሬንዞ ፔሌግሪኒን ከሮማ ማስፈረም ይፈልጋሉ ዝውውሩንም ለማሳካት እንቅስቃሴ ጀምረዋል በተጨማሪም ከዛው ከጣሊያን የናፖሊውን አለንን ለማምጣት 100ሚዩ ሊያወጣ እንደሚችል ተነግሯል
ፈርናንዶ ሊዮሬንቴ በአትሌቲኮ ቢልባኦ እየተፈለገ ይገኛል የቢልባኦ የስፖርቲንግ ዳይሬክተር ራፋ አልኮርታ ይባላሉ እኚ ሰው ሲናገሩም ሀቪ ማርቲኔዝ ኢባ ሆሜዝ አንደር ሄሬራን ሎሬንቴን የማስፈረም ፍላጎት አለን የሚል አስተያየት ሰተዋል
ዴኒስ ስዋሬዝ ከባርሴሎና ወደ አርሰናል እንዲዘዋወር የባርሴሎና ባለስልጣኖች ይፈልጋሉ ፕሬዝዳንቱ ባርቶሚዮም ልጁ ክለቡን መልቀቅ ከፈለገ እንለቀዋለን ብለዋል ልጁም ወደ አርሰናል እንዳይሄድ እያደረገ ያለው ችግር አርሰናል ተጨዋቹን አሁን በውሰት ወስዶ ክረምት ላይ ተጨዋቹን መግዛት ይፈልጋል ባርሴሎና ደሞ አሁን ላይ ከፍለው ተጨዋቹን እንዲያዘዋውሩ ይፈልጋሉ ይሄ ጉዳይ ነው ዝውውሩን ያጓተተው ተብሏል
ማንችስተር ዩናይትድ ግሪካዊውን ኮስታስ ማኖላስን የሮማውን ተከላካይ ሊያስፈርሙ ተቃርበዋል ሚሉ መረጃዎች ወተዋል 30.5ሚፓ ኮንትራት ማፍረሻ ነው ይህንንም ለመክፈል ፍላጎት አሳይተዋል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment