ሪያል ማድሪድ ኢካርዲን ለማዘወዋር ከጫፍ ደርሷል
የኢንተር ሚላኑ አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ ወደ ሪያል መድሪድ ለመዘዋወር በግሉ ከስምምነት ላይ መድረሱን Don Balon አስነብቧል።
ጋዜጣው እንዳተተው ከሆነ አርጀንቲናዊው አጥቂ በሳንቲያጎ በርናቢዮ የስድስት አመት ኮንትራት የተዘጋጀለት ሲሆን የክለቡ ከፍተኛ ተከፋዮች ዝርዝር ውስጥም የሚገባ ይሆናል።
ዚነዲን ዚዳንን እና ክርስቲያኖ ሮናልዶን ካሰነበተ በኋላ ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ሎስብላንኮዎቹ በአመቱ ከሌሎች ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የግብ ድርቅ መቷቸዋል።
ኢካርዲ በዘንድሮ ሲዝን በሁሉም የውድድር አይነቶች ለኢንተር 13 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
No comments:
Post a Comment