Sunday, January 20, 2019

የዕሁድ አመሻሽ ስፖርታዊ ዜናዎች


ከዩናይትድ ከተባረሩ ቡሀላ በዚህ ሳምንት ወደ ስራ ተመልሰው በቤይን ስፖርት ትንተና በመስጠት ላይ የሚገኙት ሞሪንሆ ከዩናይትድ ከተባረሩ ቡሀላ ሶስት ትላልቅ ስራዎች መተውልኝ ሶስቱንም ውድቅ አድርጌያለው ብለዋል



የጁቬንቱሱ አጥቂ ጎንዛሎ ሂጉዌን በሚቀጥለው ሳምንት ሙሉ ለሙሉ ዝውውሩን ያጠናቅቃል ሂግዌን  ይህ የውድድር አመት እስኪጠናቀቅ ድረስ ቸልሲን በውሰት ይቀላቀላል በፕርሪሚየር ሊጉም ቶፕ 5 ተከፋዮች ከሚባሉት ውስጥ ይካተታል በሳምንት በሚያገኘው £270,000- ሳምንታዊ ደሞዝ ይከፈለዋል በቸልሲ



ዩናይዶች አሠልጣኝ ማፈላለጉን አሁንም ተያይዘውታል ምንም እንኳን ሶልሻየር አስደናቂ ስራ እየሠራ ቢገኝም በቋሚ አሠልጣኝነት ይቀጥላል ተብሎ አይታሰብም በመሆኑም የቶተንሃሙን ማውሪሲዎ ፖቼቲኖን ለማምጣት ዩናይትድ ሙከራ በማድረግ ላይ ይገኛል



ቨርጅል ቫንዳይክ ከቀድሞ የሊቨርፑል አሰልጣኝ ኬኒ ዳግሊሽ ጋር ቶሎ ቶሎ እንደሚደዋወል ተናገረ ስልካቸውን ሰተውኛል ያለችግር እደውላለው ብሏል ስለቡድኑ ሙሉ ነገር በየጊዜው አሳውቃቸዋለው እሳቸውን ማግኘት ባለብኝ ሰአትም አግኝቼ አወራቸዋለው ብሏል



በሪያል ማድሪድ የአንድ አመት ተኩል ኮንትራት የሚቀረው ሉካ ሞድሪች በማድሪድ ብዙ አመት መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሩዋል ሲቪያን ባሸነፉበት ምሽት ወሳኙዋን ጎል ያስቆጠረው ሞድሪች ከተለያዩ ክለቦች ጋር በተደጋጋሚ ስሙ ቢነሳም እሱ ግን ምርጫው ማድሪድ እንደሆነና መልቀቅም እንደማያስብ ተናግሩዋል



የኢንተር ሚላኑ CEO ማውሮ ኢካርዲ ከክለቡ ጋር እንደማይለያይ ተናግረዋል አሁን እስከ 2021 የሚያቆይ ኮንትራት አለው ከዚም ቡሀላ በሳንሴሮ ረጅም አመት እንደሚቆይ ለፈላጊ ክለቦቹ በይፋ አረጋግጠዋል



ወደ ሪያል ማድሪድ ሊሄድ ከጫፍ ደርሱዋል ቢባልም ዩናይትዶች አሁንም ብራዚላዊውን የፖርቶ ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው መረጃዎች አሳይተዋል



ኮሪዮ ዴሎ እስፖርት ባወጣው መረጃ ኤሲ ሚላን ኦዚልን በውሰት እንዲወስድ ቀርቦለት የነበረውን ጥያቄ ማልዲኒ ተቀብሎት  ተጫዋቾች በመሸጥ ለኦዚል ቦታ ለማስለቀቅ ዝግጁ የነበረ ቢሆንም አሁን በሚላን የሚገኙትየቀድሞ የመድፈኞቹ አለቃ ጋዚዲስ ከ 25 አመት በላይ የሆነ ተጫዋች አንፈልግም ብለው ጥያቄውን ውድቅ አድርገውታል



በቢቲ ስፖርት በተንታኝነት እየሰራ የሚገኘው የቀድሞ የዩናይትድ ኮከብ ፖል ስኮልስ ወደ ልጅነት ክለቡ ኦልድሀም አሰልጣኝ ለመሆን ተቃርቧል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...