Monday, January 21, 2019

የማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች


አሰልቺው የጎንዛሎ ሂግዌን ዝውውር ወደ መጠናቀቁ ደርሧል ከክረምት ጀምሮ ስሙ በሰፊው ከቸልሲ ጋ የተያያዘው ሂግዌን ዝውውሩ ወደ መጠናቀቁ ደርሶለታል እንደምክንያት የተቀመጠው ዛሬ ምሽት ኤሲሚላን ከጄንዋ  ከሚያደርጉት ጨዋታ ውጭ ሆኗል



ማቲዮ ዳርሚያን ከማንችስተር ዩናይትድ ወደ ጁቬንቱስ በውሰት ሊዘዋወር እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል ጁቬንቱስ ተጨዋቹን በውሰት ውል እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ወስዶ የውድድር አመቱ ሲጠናቀቅ በ7.1ሚፓ ለማስፈረም ከዩናይትድ ጋ ድርድር መጀመራቸው ተሰምቷል



አርሰናል የአትሌቲኮ ማድሪዱን ጊልሰን ማርቲንሰንን በውሰት ለማምጣት ተስማምቷል ሚል መረጃ ወቷል በተለይ የፖርቹጋሉ ኦዦጎ የተባለው ጋዜጣ ይዞት እንደወጣው ከሆነ በይፋ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ጥያቄ አቅርበዋል አትሌቲኮዎች ደግሞ ምናልባት ሞራታን የማግኘት እድላቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ማርቲንስን ለመስጠት ፍላጎት አሳይቷል የሚል መረጃ አውጥቷል



ሂግዌንን ወደ ቼልሲ ለመላክ እጅጉን የተቃረቡት ኤሲ ሚላኖች የሱን ምትክ ክሪትስቶስ ፒያቲክን በ31ሚ.ፓ ከጄንዋ ለማስፈረም እንደበስማማ እና ከተጨዋቹም ጋ በግል ከስምምነት እንደደረሰም ተነግሩዋል ልጁም ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ የጄንዋን ማልያ በመልበስ ቀጣይ ክለቡን ይገጥማል



ሜሱት ኦዚልን ሽጠው ሀሜስ ሮድሪጌዝን የማምጣት ፍላጎት ያላቸው አርሰናሎች ዝውውሩ ላይሳካ እንደሚችል መረጃዎች እያሳዩ ይገኛሉ ከትናንት ጀምሮ አርሰናሎች ኦዚልን ለባየርን ሙኒክ ሰተው ሀሜስን በውሰት መውሰድ ቢፈልጉም በዚህ የዝውውር መስኮት ልጁ ባየርን ሙኒክን መልቀቅ እንደማይፈልግ ተነግሩዋል



እንደ ስካይ ኢታሊያ ዘገባ ከሆነ ባርሴሎናዎች ኬቨን ፕሪንስ ቡአቴንግን ከሳሱሎ ለማዘዋወር  ተስማምተዋል።ጋናዊው ተጨዋች በካምፕኑ የስድስት ወር ውል ፈርሟል።



አልቫሮ ሞራታ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ማድሪድ ከተማ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ወተዋል



ቼልሲ ከሂግዌይን በተጨማሪ ብራዚላዊውን ፊሊፔ ኮቲንሆን ለማስፈረም እንደሚፈልግ ተነግሩዋል ቼልሲዎችም ከባርሴሎና ሰዎች ጋር ንግግር መጀመራቸውም ታውቋል ቸልሲ ለልጁ እስከ 100ሚፓ መክፈል ፍላጎት አላቸው



የጉዳት ዜና  በቅዳሜው ምሽት የለንደን ደርቢ ጨዋታ ጉዳት የደረሰበት ሄክቶር ቤላሪን በዚህ የውድድር አመት ወደ ሜዳ እንደማይመለስ ተነግሩዋል
ባርሴሎና ሌጋኜስን ሲገጥሙ ጉዳት የደረሰበት ኦስማን ዴምቤሌ ለሁለት ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ ይፋ አድርጉዋል ዴምቤሌ ባርሳ በኮፓ ዴላሬ ከሲቪያ ጋ በሚያደርጋቸው ደርሶ መልስ ጨዋታ እንዲሁም በላሊጋው ከቫሌንሲያ እና ከጄሮና ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ያመልጡታል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...