Tuesday, January 22, 2019

የማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


ሰሞኑ በተደጋጋሚ ከኮሎምቢያዊው ሀሜስ ሮድሪጌዝ ጋ ስሙ እየተነሳ የሚገኘው አርሰናል ከባየርን ሙኒክ ይልቅ ሪያል ማድሪድን ለማነጋገር ወስነዋል ተብሏል ምክንያቱም ሙኒኮች ልጁን በቋሚነት እንደማያስፈርሙት ብዙ ማረጋገጫዎች እየወጡ ነው መሆናቸውን ተከትሎ ከማድሪድ ጋር እየተነጋገረ ነው ሚለው መረጃ በሰፊው እየወጣ ነው
.
ሰሞኑ በሰፊው ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ የተነሳው የዌስትሀሙ ማርኮ አርናቶቪችን በተመለከተ ዌስትሀሞች በልጁ ጉዳይ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን መረጃዎች እያሳዩ ይገኛሉ ልጁ በዚ የጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን እንዲለቅ አይፈቀድለትም በቀጣይ ክረምት ግን ወደየትኛውም ክለብ መሄድ ከፈለገ እንደሚፈቀድለት ውሳኔ ላይ ደርሱዋል
.
የ38 አመቱ የቀድሞ የአርሰናል እና የቸልሲ ተጨዋች አሽሊ ኮል የቀድሞ የክለቡ አጋር ሚያሰለጥነውን ደርቢ ካውንቲን እስከዚ አመት መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል ተቀላቅሉዋል በቻምፒየን ሺፑ ከሚጫወቱ አንጋፋ ተጨዋች የመጀመሪያው ይሆናል ማለት ነው
.
ትናንት ምሽት ወጣቱን ማክቶሚናይን ውል ያራዘሙት ዩናይትዶች በዚ ሳምንት የወጣቱን ባለተሰጦ ተጨዋች የማርሻልን ኮንትራት ለማስፈረም ከጫፍ ደርሱዋል ከማርሻል በተጨማሪም ዴህያ ማታ እና ሄሬራም የተሳካ ድርድር እያደረጉ እንደሆነ ታውቋል
.

የሶስት ተጨዋቾች ዝውውር በፒያቴክ ዝውውር መጓተት ተይዟል ሂጉዌይን አሁንም በጣሊያን ይገኛል ኤሲ ሚላኖች የጄኑዋውን ፒያቴክ ዝውውር እንዳጠናቀቁ አርጀንቲናዊው አጥቂ ወደ ለንደን ያመራል ከዛም ሞራታ ወደ ወደ አትሌቲኮ እንዲዛወር በቼልሲ ፍቃድ ያገኛል

.
ሪያል ማድሪዶች ተጨዋች የማስፈረም አማራጫቸውን በሀሜስ ሮድሪጌዝ ላይ ጥለዋል በሙኒክ በውሰት የሚገኘውን ሀሜስን በክረምቱ ኤሪክሰንን ከቶተንሀም ለማምጣት አንድ የዝውውሩ አካል ሊያደርጉት አስበዋል በተጨዋቹ ምክንያት ይሄ ማይሳካ ከሆነ ሌላኛው ሚፈልጉትን ሀዛርድን ከቸልሲ ለመውሰድ አንድ የዝውውር አካል ሊያደርጉት ይፈልጋሉ ማድሪዶች ግን ዋና ኢላማቸው ኤሪክሰን ነው
.
️ቢቢሲ ስፖርት በመረጃው እንዳስነበበው ከሆነ ሜሱት ኦዚል ወደ ማንችስተር  ዩናይትድ ሊሄድ እንደሚችል እና ከአሌክሲስ ሳንቼዝ ጋር ዳግም ሊገናኙ እንደሚችል ዘግቧል ዩናይትዶችም ልጁን በቅርበት እየተመለከቱት ነው
.
የቀድሞ የቸልሲ እና የኒውካስትል አጥቂ ዴምባባ ወደ ኢስታንቡል ባሳክስዬር አምርቷል ዝውውሩም ለ6 የሚቆይ የውሰት ውል ነው በቻይና ሻንሺንዋ እየተጫወተ የነበረው ዴምባባ በድጋሚ ወደ ቱርክ ተመልሱዋል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...