Wednesday, January 23, 2019
የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አርሰናል የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካዩን ኤሪክ ባይሊን በውሰት ለመውሰድ ለዩናይትድ ጥያቄ አቅርበው ነበር ኤምሪም ልጁን የማግኘት ተስፋ ነበራቸው ለማግኘት ነገር ግን ዩናይትዶች ጥያቄውን ውድቅ አድርገውባቸዋል ዩናይትዶችም ልጁን እንደሚፈልጉት እና እንደማይለቁትም ተናግረዋል
በፒኤስጂ እና በማንችስተር ሲቲ ሲፈለግ የነበረው ሆላንዳዊው የአያክስ አማካይ ፍራንክ ዲዮንግ በመጨረሻም ማረፊያው ባርሴሎና ሊሆን ነው ባርሳዎች ለልጁ እስከ 65ሚፓ ከፍለው ሊያመጡት ከጫፍ ደርሰዋል ባርሴሎና ዝውውሩን የሚያጠናቅቅ ቡድን ዛሬ ወደ ሆላንድ እንደሚልክ ነው የተሰማው ተጨዋቹም ወደ ስፔን መሄድ ይፈልጋል
ፒኤስጂ በፈረንሳይ ሊግ የስነምግባር ኮሚቴ ቅጣት ተላልፎበታል 100ሺዩ የተቀጣው ምክንያቱም ደሞ ወጣት ተጨዋቾችን ሲያስፈርም ዘርን መሰረት ያደረገ መረጃ መዝገቡ ላይ ያሰፍራሉ ሚል መረጃ ወቷል የፈረንሳዩ ዌብሳይት ሚዲያ ፓርት ይህን ዘገባ ይዞ ከወጣ ቡሀላ ምርመራ ሲደረግ ነበር በመጨረሻም ቅጣት ተላልፎበታል ፒኤስጂ ላይ
ኤሲ ሚላኖች የሂግዌንን ለመልቀቅ መቃረብን ተከትሎ የጄንዋውን አጥቂ ክሪትስቶስ ፒያቲክን ለማስፈረም ተቃርበዋል ለዝውውሩ 30ሚፓ ይከፍላሉ ዝውውሩም ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሏል ሜዲካሉንም ዛሬ እንደሚያደርግ ተነግሯል በሚላንም የአምስት አመት ኮንትራት ይፈርማል
ቶማስ ቱሄል ከማርኮ ቬራቲ መጎዳት እና ከራቢዮት አለመጫወት የተነሳ የመሀል ሜዳው ክፍል ሳስቷል ብለዋል ሌላ የመሀል ሜዳ ተጨዋች ያስፈልገዋልም ብለዋል የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት አማካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ ሊወጡ ነው በዝውውሩም የናፖሊውን አለንን እና የዋትፎርዱን ዶኮሬን ኢላማቸው ውስጥ አስገብተዋል
አርሰናልን እንደሚለቅ የተረጋገጠው አሮን ራምሴ አርሰናሎች ዴኒስ ስዋሬዝን ወይም ሀሜስ ሮድሪጌዝን ካገኙ በጥር የዝውውር መስኮት ሊለቁት እንደሚችሉ ተሰምቷል .
የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ሄሴ ሮድሪጌዝ ወደ ጣሊያኑ ቶሪኖ ለመዘዋወር ተቃርቧል
የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ በውሰት ለሬዲንግ ለመጫወት መፈረሙ ተረጋግጧል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment