Thursday, January 24, 2019
የሀሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
ብዙ ክለቦች አይናቸውን የጣሉበት ወጣቱ ፍራንክ ዲዮንግ ትናንት በይፋ የባርሴሎና ተጨዋች ሆኗል በአያክሳምስተርዳም ሁለት አመት የቆየው የ21አመቱ ኮከብ በ75ሚዩ ባርሴሎናን መቀላቀሉ ይፋ ሆኗል በፒኤስጂ በጥብቅ ቢፈለግም ማረፍያው ስፔን ሆኗል 71ሚዩ መነሻ ሲሆን ብቃቱ እየታየ 11ሚዩ ለአያክሶች ይከፈላቸዋል
ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ፒኤስጂ ለማምራት ከፒኤስጂ ፕሬዝዳንት ከናስር አልኻላፊ ጋር ተነጋግሯል ተብሏል ከአሰልጣኝነት ከተነሳ ቡሀላ ወደ ኳታር አምርቶ ለቤይን ስፖርት በተንታኝነት እየሰሩ ባሉበት ጊዜ ከፒኤስጂ ፕሬዝዳንት ጋር ተነጋግረዋል ተብሏል
ቪክቶር ሞሰስ ወደ ፊነርባቼ ሊያመራ እንደሆነ መረጃዎች ወተዋል በአንቶኒዮ ኮንቴ ስር በቀኝ ተመላላሽነት በቋሚነት ሲሰለፍ የነበረው ሞሰስ ሳሪ ከመጣ ቡሀላ ግን ምንም እድል እየተሰጠው አደለም ይህን ተከትሎ ዛሬ ወይም ነገ በውሰት ወደ ቱርኩ ክለብ እንደሚያቀና ተነግሩዋል
ጁቬንቱስ በዚ የጥር የዝውውር መስኮት ራምሴን ለማስፈረም ለአርሰናል ኤሚል አውዱዮን የተባለ ግብ ጠባቂ አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ ሆኗል ልጁ አሁን ላይ ሳምፕዶርያ ነው የሚገኘው ከፒተር ቼክ ጋ ክረምት ላይ ሚለያዩት አርሰናሎች ሁለተኛ በረኛ ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ ይህን ተከትሎ ቀድሞውንም ሚፈልጉትን ተጨዋች በአማራጭ ሊያገኙት ይችላሉ
ከጥቂት ወራት በፊት ወደ ልጅነት ክለቡ ተመልሶ ማሰልጠን የጀመረው የቀድሞ ኮኮብ ሄነሪ ከቡድኑ ጋ ሊለያይ እንደሚችል ተሰምቷል ቡድኑን ከወራጅ ቀጠና ማሶጣት የከበደው ሄነሪ ሰሞኑ ከስራው በላይ የቡድኑ ህልውና እንደሚያሳስበው መናገሩ ይታወሳል እናም መረጃው እንዳወጣው የቀድሞ ኮከብ ከሶስት ወራት ቡሀላ ከክለቡ ጋር ሊለያይ ይችላል ብሏል ይህንን ተከትሎ ሄነሪ የተካው የቀድሞ አሰልጣኝ ሊዮናር ያርዲ በድጋሚ ወደ ሞናኮ ይመለሳሉ ተብሏል
አርሰናሎች ሞሮኮዋዊን የጁቬንቱስ ተከላካይ መህዲ ቤናቲያን ለመውሰድ ፍላጎት አላቸው ልጁን ከአርሰናል በተጨማሪ ፉልሀም እና ከተለያዩ የቻይና ክለቦች ጥያቄም ቀርቦለታል ከአርሰናል እና ፉልሀም ይልቅ የቻይና ክለቦች ለልጁም ሆነ ለጁቬንቱስ ከፍተኛ ገንዘብ ቀርቦላቸዋል
ሴድሪክ ሱዋሬዝ ወደ ኢንተር ሚላን ለማምራት እየተነጋገሩ ይገኛሉ ኢንተሮች በክረምቱ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ያስፈረሙት ሺሜቨር ሳልኮ በተጠበቀበት ደረጃ ባለመገኘቱ ወደ ገበያ ለመውጣት ተገደዋል ዋነኛ ኢላማቸውም ፖርቹጋላዊው ሴድሪክ ሱዋሬዝ ሆኗል
የአልቫሮ ሞራታ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ መግባቱ እርግጥ መሆኑን ተከትሎ ጊልሰን ማርቲኔዝ ወደ ሞናኮ ለመሄድ ተቃርቧል ዝውውሩም ለመጠናቀቅ ከጫፍ ደርሷል
ወደ ቼልሲ ያመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የዜኒቱ አማካይ ሊዮናርዶ ባራቴዝ ወደ ፒኤስጂ ለመሆድ ምርጫውን እንዳደረገ የተለያዩ ታማኝ ምንጮች አስነብበዋል በተጨማሪም ፖርቹጋላዊው የሙኒክ አማካይ ሬናቶ ሳንቼዝ ወደ ፒኤስጂ ሊያመራ እንደሚችል ተነግሩዋል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

አቀራረባቹ አሪፍ ነው! ምነው ጠፋቹ?
ReplyDelete