Sunday, January 6, 2019

የእሁድ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


አልቫሮ ሞራታ በዚ ሲዝን 9 ጎሎችን ብቻ ነው ያገባው በፕሪሚየር
ሊጉ ደግሞ 5 ጎል ብቻ ለዚህም ነው ማውሪሲዮ ሳሪ በስፔኑ ኢንተርናሽናል ተጫዋች ላይ ተስፋ ቆርጠው ኤደን ሀዛርድን የአልቫሮ ሞራታን የማጥቃት ስራ የሰጡት ሳሪ ያለፈው ክረምት አሰልጣኝ ሆኖ ሲቀጠር ሂጉዌንን ወደ ሰማያዊዎቹ ማምጣት ፈልጎ እንደነበር ይታወቃል  ሮናልዶ ጁቬንቱስን በመቀላቀሉ እና ሂጉዌን ለሮናልዶ ቦታ በመልቀቅ ወደ ሚላን ስለሄደ የሳሪ ምኞት ያለመሳካቱንም ነው ዘ ሰን ጋዜጣ የዘገበው አሁን ደግሞ አልቫሮ ሞራታን በሂጉዌን ሊቀያየሩ እንደሆነ እየተዘገበ ይገኛል
.
የማንቸስተር ሲቲው ወጣት ተጫዋች ብራሂም ዲያዝ በቀጣዮቹ 48 ሰአታት ውስጥ ወደ ሪያል ማድሪድ ሊዘዋወር እንደሚችል የዘገበው ኢ ኤስ ፒ ኤን ጋዜጣ ነው  ዲያዝ በክረምቱ ውሉ ስለሚያልቅ በነፃ ዝውውር ከክለቡ ሊወጣ እንደሚችል ቢነገርም ሪያል ማድሪዶች ግን ከውሉ መጠናቀቅ በፊት 15 ሚሊየን ዩሮ በመክፈል ወደ ሳንቲያጉ በርናቤዉ ሊያመጡት እንደሚችሉ ፍንጭ ተሰቷል ምንጮች ዲያዝ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ወደ ማድሪድ ከተማ አቅንቷል ቢሉም አርብ እለት ደግሞ ማንቸስተር ሲቲዎች ልምምድ ሲሰሩ በካሜራ እይታ ውስጥ እንደገባ አረጋግጠዋል
.
በማን.ዩናይትድ ዕቅድ ውስጥ የነበረው የናፖሊው ተከላካይ ኩሊባሊ የማድሪድና ባርሳ ኢላማ ሆኗል እንደ Calcio Mercato ዘገባ ከሆነ ባርሳ 120€m አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል
.
አርሰናሎች የጁቬንቱሱን ተከላካይ መህዲ ቤናቲያን ማስፈረም ይፈልጋሉ መድፈኞቹ ራምሴን የዝውውሩ አካል በማድረግ በጉዳት እታመሰ ያለውን የተከላካይ መስመር ችግር በሞሮኳዊው ለመሸፈን አስበዋል
.

በክለቡ ቼልሲ ደስተኛ ያልሆነው ስፔናዊው ፋብሪጋዝ ሞናኮን ለመቀላቀል ተሰማማ ሞናኮዎች ለተጨዋቹ የ 3አመት ኮንትራት አቅርበውለታል ፊርማውን በአጭር ቀን ውስጥ ሊፈርም እንደሆነ ተረጋግጧል
.
ባለፈው ክረምት ከማንችስተር ዩናይትድ የ 3 አመት ኮንትራት ቀርቦለት ውድቅ በማድረግ በአትሌቲኮ ማድሪድ የቆየው ዲያጎ ጎዲን ኮንትራቱ በሚቀጥለው ክረምት ስለሚጠናቀቅ እና በአዲስ ኮንትራት ዙሪያ ከአትሌቲኮ ጋር ስላልተስማማ ዩናይትድ በክረምት በነፃ ወደ ኦልትራፎርድ ለማምጣት ድርድር ለመጀመር ተዘጋጅተዋል
.
ጁቬንቱስ አሁንም ተሰፋ አልቆረጠም የቀድሞ ኮከባቸውን ፖል ፖግባን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ካልቺዮ መርካቶ ዘግቧል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...