Saturday, January 5, 2019

የዕሁድ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

ቼልሲ ለዩራጉዊያዊው የፓሪሰን ዤርመን ተጨዋች ኤዲንሰን ካቫኒ ዝውውር የሚሆን £50M ለፈረንሳዩ ክለብ አቅርቧል።ካቫኒ ከኔይማር መምጣት በኃላ በፓርክ ደ ፕሪንስ ደስተኛ እንዳልሆነ ይታወቃል።
(Sunday Express)



አርሰናል ስፔናዊውን አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ለማዘዋወር ከባርሴሎና
 ጋር ድርድር የጀመረ ሲሆን በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮትም የማዘዋወር ዕድሉ ከፍተኛ ነው ተብሏል።ሱዋሬዝ በኤርኔስቶ ቫልቬርዴው ቡድን ውስጥ በቋሚነት መሰለፍ እንዳልቻለ ይታወቃል።
(Observer)






በርንማውዞች ቼልሲ ለ26 አመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ካሉም ዊልሰን የሚያቀርበውን የትኛውንም የዝውውር ጥያቄ ላለመቀበል ወስነዋል።
(Sunday Mirror)



ብራዚላዊው የ31 አመት ተከላካይ ዳቪድ ሊውዝ ትናትት ለቼልሲ የመጨረሻውን ጨዋታ ያደረገው ሴስክ ፋብሪጋዝ በእንግሊዝ ውስጥ ለበርካታ አመታት ከተጫወቱ ተጨዋቾች ከምርጦቹ መሆኑን ገልፆ እንደሚናፍቀውም ተናግሯል ።ፋብሪጋዝ በቴሪ ሄንሪ የሚሰለጥነውን ሞናኮ እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።
(Talksport)




የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሞኒ በማንቸስተር ዩናይትድ እየተፈለገ የሚገኘውን የ32 አመቱን ኡራጉዊያዊ ተከላካይ ዲያጎ ጎዲን በክለቡ ለማቆየት እየሰራ መሆኑን ተናገረ።
 (Sunday Express)




ሩይ ቪቶሪያን ያሰናበተው የፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ ከማንቸስተር ዩናይትድ የተሰናበቱትን ጆዜ ሞሪንሆ ለመቅጠር ፍላጎት ቢኖረውም ጆዜ ግን ውድቅ አድርገውለታል ።
 (Record - in Portuguese)



ማንቸስተር ሲቲ የ19 አመቱን ተጨዋች ብራሂል ዲያዝ ከሪያል ማድሪድ ይልቅ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ማዘዋወር  እንደሚፈልግ ተነግሯል።ምክንያቱ ደግሞ ለሀገር ውስጥ ክለብ የሚሰጥ ከሆነ 40% ታክስ የሚያገኝ ሲሆን የማድሪድ ከሰጠው ግን 15% ነው የሚያገኘው ።
(Talksport)




ሪያል ማድሪድ በማንችስተር ዩናይትድ የሚፈለገውን ብራዚላዊውን የፖርቶ  የ20 አመት ተከላካይ ኤደር ሚሊታኦ ለማዘዋወር ከፖርቹጋሉ ክለብ ጋር ድርድር ጀምሯል።
(Marca)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...