ጁቬንቱስ የአሰልጣኙን ማክሲሚሊያኖ አሌግሪን ኮንትራት ለማራዘም ፍላጎት አሳይተዋል ከቅርብ ግዜ ወዲህ እኚህ አሰልጣኝ በተለያዩ ክለቦች እየተፈለጉ ነው እንደ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድ የሰውዬው ፈላጊ ሆነው መተዋል ይሄንንም ተከትሎ ጁቬንቱስ ኮንትራቱን ለማደስ ፍላጎት አለው ሰውዬው በጁቬንቱስ እስከ 2020 ድረስ የሚያቆየው ኮንትራት አላቸው ነገር ግን የስፖርቲንግ ዳይሬክተሩ ፓራቲሲ አስተያየት ሰተዋል ቦርዳችን የአሰልጣኙን የወደፊት ቆይታ በተመለከተ እየተነጋገረ ነው የሚገኘው ስለዚ በጁቬንቱስ እንደሚቆዩ ተስፋ አደርጋለው ተጨማሪ ኮንትራት ለመስጠትም እየተደራደርን ነው ብለዋል
ዌልሳዊው አሮን ራምሴ ከጁቬንቱስ ጋር ቅድመ ኮንትራት እንደተፈራረም ተሰምቷል እንደውም በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ክለቡ ሊሄድ ይችላል ነገር ግን አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ተጨዋቹን በዚ የጥር የዝውውር መስኮት የመልቀቅ ፍላጎት የላቸውም ይሄን የውድድር አመት በክለቡ እንዲቆይ ይልጋሉ
ማውሪሲዮ ፖቸቲንሆ እና ማንችስተር ዩናይትድ ባለስልጣናት በድብቅ እየተደራደሩ እንደሆነ ተሰምቷል እንዲያውም ከወዲሁ አንዳንድ ተጨዋቾችን እንዲያስፈርሙላቸው ጥቆማ ሰተዋል ተብሏል ከነዚህም መካከል አንደኛው የሌስተር ሲቲው የአጥቂ አማካይ ጄምስ ማዲሰን አንደኛው ነው ፖቸቲንሆ ክለቡን ከያዙ የኤሪክሰንን ሚና ሊሰጡት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል ተብሏል
የስፔኑ ሴቪያ በቼልሲ ያልተሳካ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘውን አልቫሮ ሞራታን በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ ለቼልሲ ማቅረቡ ተሰምቷል ከሲቪያ በተጨማሪ የጣሊያኑ ኤሲ ሚላን የልጁ ቁጥር አንድ ፈላጊ መሆኑ ታውቋል
ቼልሲዎች የፒኤስቪውን ሄርቪን ክሎዛኖን በ36ሚ.ፓ ለመግዛት እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ ተነግሯል ሌላኛው ተጨዋቻቸው ካሉም ሁድሰንሆዶይ ግን የዝውውር መልቀቂያ የልቀቁኝ ጥያቄ እንዳስገባ ተነግሯል ባይርን ሙኒኮች ይሄን ተጨዋች ይፈልጉታል ክሪስቲያን ፑሊስች ወደ ቸልሲ መዘዋወሩን ተከትሎ ኦዶይ በክለቡ የመቆየት ፍላጎት እንደሌለው ተነግሯል ሙኒኮችም ለልጁ 30ሚ.ፓ አቅርቧል
የጣሊያኑ ኢንተርሚላን ሁለቱን የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር ተጨዋቾችን አሽሊ ያንግን እና አንቶኒዮ ቫሌንሲያን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ፍላጎት ማሳየታቸውን ጣሊያናዊው ታማኝ ጋዜጠኛ ዲማርዚዮ ተናግሯል ዝውውሩም ሚሳካ ከሆነ ኢንተሮች ያንግን በጥር ቫሌንሲያን ደሞ በክረምቱ ማስፈረም ይፈልጋሉ
አርሰናል የባርሴሎናውን አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝን ለማስፈረም ተቃርቧል አማካዩ ከዚህ በፊት ከኡናይ ኤምሬ ጋ በሲቪያ አብረው መስራታቸው ይታወቃል
ከዩናይትድ የአሰልጣኝነት መንበራቸው በቅርቡ የተነሱት ጆዜ ሞሪንሆ ከተለያዩ ክለቦች ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ወደ ሀገራቸው ፖርቹጋል በድጋሜ በመመለስ ቤኔፊካን ለማስለጥን እያጤኑበት እንደሆነ ተሰምቷል
ሜሱት ኦዚል አዲስ ኮንትራት የፈረመው ባለፈው ጥር ላይ ነው ስለዚህም በአርሰናል ይቆያል የወደፊቱን የምናይ ቢሆንም አእምሮውን የሚያስቀይር ምንም ነገር የለም ሲል ወኪሉ ኤርኩት ተናግሯል
ማንችስተር ዩናይትድ በጥር የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር የሮማውን ግሪካዊ ተከላካይ ኮስታስ ማኖላስን ለማስፈረም ተዘጋጅተዋል የተከላካዩ ውል ማፍረሻ £34 million ነው ዩናይትድም ልጁን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል
No comments:
Post a Comment