ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ!
ከሬዲንግ ጋር በነበረው ጨዋታ የተሻለ ነገር ቢያሳይም አሁንም ግን ሳንቼዝ
መልቀቅ እንደሚፈልግ ተዘግቧል አትሌቲኮ ማድሪድና ቫሌንሲያም ፈላጊዎቹ
ሆነዋል ሳንቼዝ ዩናይትድን የተቀላቀለው አምና በጥር የዝውውር መስኮት
እንደነበር ይታወሳል
ኤቨርተኖች የአታላንታው ተከላካይ ጂያንሉካ ማንቺኒ ኢላማቸው ሆኗል ጥሩ
ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ተጫዋቹ በውድድር አመቱ መጨረሻ የወደፊት
ውሳኔውን ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል ምንም እንኳን ኮንትራቱ 4 አመት
ቢቀረውም አታላንታዎች አሁንም እንዲያራዝም ይፈልጋሉ ኢንተርና ሮማም
ሌሎች የተጫዋቹ ፈላጊዎች ናቸው
ቸልሲ ካለም ዊልሰንን ማያገኙ ከሆነ ኤዲሰን ካቫኒን ለማስፈረም አስበዋል
ዩራጓዊውን የ 31 አመት የ ፒ ኤስ ጂ አጥቂ ለማምጣት እስከ 50 ሚ.ፓ
መመደባቸው ተዘግቧል
ፉልሀም የሊቨርፑሉን አጥቂ ዲቮክ ኦሪጊን በ15 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረም
ይፈልጋሉ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ላለመውረድ እየታገሉ መሆኑ ይታወቃል ወደ
ሊጉም የመጡት በአሁኑ ነው አዲሱ ካራቨን ኮቴጅ የሚገኙት አሰልጣኝ
ክላውዱዮ ራኔሪ ትኩረታቸውን ወደ ቤልጄየሚያው ኢንተርናሽናል እጥቂ
እድርገዋል እሱም በእዚህ ክለብ በተቀያሪ ወንበር ላይ ነው የሚገኘው
ከዎልፍስበርግ በውሰት የመጣው አጥቂ በዘንድሮ የውድድር አመት
በመርሲሳይድ ድረቢ ማስቆጠሩ ይታወሳል
በዘንድሮ የውድድር አመት ብዙም የመሰለፍ እድል ያላገኘው ፒተር ቼክ በጥር
ስለመልቀቅ እያሰበ ይገኛል ኡናይ ኤምሪም እሱ ከቡድናቸው ጋር አብሯቸው
እንደሚቆይ እርግጠኛ አይደሉም
ዩናይትዶች በሰፊው ስማቸው ከካራስኮ ጋር ተያይዟል የቀድሞ የአትሌቲኮ
ማድሪድ ተጨዋች ቀድሞ በሞናኮ ያሰለጠኑት እና ከሞናኮም እንዲለቅ
ምክንያት የሆኑት አሰልጣኝ አሁን የሚገኝበትን የቻይና ክለብ መቀላቀሉ
ይባሱንም ክለቡን እንዲለቅ እንደሚያስገድደው ታውቋል
ሊቨርፑል የtrabzonspor የ27 ዓመት ወጣት ለማስፈረም ተቃርቧል ሊቨርፑል
ለእዚህ ተጫዋች 27 ሚሊዮን ፓውንድ ሊከፍለው ነው የአዳም ላላንም የረጅም
ጊዜ ተተኪ ማረግ ይፈልጋል የርገን ክሎፕ ይህን ተጫዋች ከሲቲ አስጥለው
ማስፈረም ይፈልጋሉ የቱርክ ምርጥ ወጣት ተጫዋች የተሸለመው ይህ
ተጫዋች ክለቡ እስከ እዚህ ዓመት መጨረሻ እንዲያቆየው ይፈልጋል
ያቀረብኩላችሁ ኢብራሂም ሙሃመድ ነኝ
No comments:
Post a Comment