የጁቬንትሱ አጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን በቀጣዩ ሳምንት ቼልሲን የሚቀላቀል ይሆናል።የ31 አመቱ አጥቂ ሰማያዊዎቹን የሚቀላቀላው በውሰት ሲሆን እስከ ሲዝኑ መጨረሻም በስታንፎርድ ብሪጅ የሚቆይ ይሆናል።አንድ ስታር ዘገባ ያሳለፍነውን ሲዝን በኤሲ ሚላን ያሳለፈው ሂጎይን በቼልሲ በሳምንት £270,000 የሚከፈለው ሲሆን ይህም ከፕሪምየር ሊጉ አምስት ከፍተኛ ተከፋዮች ዝርዝር ውስጥ ያስገባዋል።
(Star on Sunday)
ቼልሲ £100M የሚገመተውን የቀድሞው የሊቨርፑል አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ለማዘዋወር ለባርሴሎና ጥያቄ አቅርቧል።የ26 አመቱ ብራዚላዊ ሊቨርፑልም በድጋሚ ማስፈረም ይፈልጋል።
(Express)
ሪያል ማድሪድ የቼልሲውን ቤልጄሚያዊ አጥቂ ኤድን ሃዛርድ ከ£100ሚ ባነሰ ዋጋ የማስፈረም ተስፋ እንዳላቸው አስበዋል።ሃዛርድ በቼልሲ ያለው ኮንትራት በፈረንጆቹ ጁን 2020 ነው የሚጠናቀቀው።
(Marca)
ኤቨርተን በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ የሚገኘውን የቼልሲውን ቤልጄሚያዊ አጥቂ ሚቺ ባትሹዋይ ለማዘዋወር ለሰማያዊዎቹ £40ሚ አቅርቧል።
(Sun)
የፓሪሰን ዤርመኑ አጥቂ ኪልያን ምባፔ ከአንድ የፈረንሳይ ሚድያ ጋር በነበረው ቆይታ ለወደፊት ሪያል ማድሪድ እጫወታለው ብሎ እንደሚያስብ ተናገረ።ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ የተጨዋቹ ቀንድኛ አድናቂ እንደሆኑ ይታወቃል።
(AS, via Mirror)
የቶተንሃሙ አጥቂ ማውሪስዮ ፖቼቲንሆ ወሳኝ ተጨዋቻቸውን ሃሪ ኬን በጉዳት ማጣታቸውን ተከትሎ የሱን ቦታ ለመተካት ተጨዋች ከማስፈረም ይልቅ ከአካዳሚ ወጣት ተጨዋች ሊያመጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
(London Evening Standard)
የባርሴሎናው አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ወደ አርሰናል የሚያረገውን ዝውውር በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚጨርስ ይጠበቃል።
(Star)
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከዩናይትድ ከመባረራቸው በፊት ገና ሲዝኑ ከመጀመሩ በፊት የሊጉ ሻምፒዮን እንደማይሆኑ አስበው እንደነበር ተናግረዋል።ሞሪንሆ ከዩናይትድ ከወጡ በኋላ ከሶስት ክለቦች ጥያቄ እንደቀረበላቸውም ተናግረዋል፡፡
(Manchester Evening News)
No comments:
Post a Comment