Tuesday, January 8, 2019

የእለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


አርሰናል ዴኒስ ስዋሬዝን ከባርሴሎና ለማስፈረም ተቃርበዋል የአርሰናል የጥር የመጀመሪያ ፈራሚ እንደሚሆን ተነግሯል የ24አመቱ ሱዋሬዝ በባርሳ የመሰለፍ እድል እያገኘ አደለም በዚ የውድድር አመት ሁለት ጨዋታዎችን ነው በላሊጋው ተሰልፎ መጫወት የቻለው ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ በግልፅ ተናግሯል ከአርሰናል ውጭ ዌስትሀም እንዲሁም የጣሊያኖቹ ሮማ ና ኤሲ ሚላን ናቸው አርሰናል ከሌሎች ክለቦች ልጁን የማግኘት እድላቸው የሰፋ ነው



ማንችስተር ዩናይትድ የጆዜን ስንብት ተከትሎ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሶልሻየርን መሾሙ ይታወሳል በውድድር አመቱ መጨረሻ ቋሚ አሰልጣኛቸውን እንደሚያሳውቁ ይጠበቃል ብዙ አሰልጣኞቹ ከዩናይትድ ጋር ስማቸው እየተያያዘ ይገኛል ነገር ግን እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ በመልበሻ ክፍል ውስጥ ተጨዋቾቹ ቋሚ አሰልጣኛቸው እንዲሆን ሶልሻየርን እንደሚመርጡ ተሰምቷል



የቼልሲውን አጥቂ አልቫሮ ሞራታን ለመውሰድ ፍላጎት እንዳለው ሲቪያ ታውቋል የተጨዋቹ ወኪል ሁዋን ማሎፔዝ ትላንት ወደ ሲቪያ አምርቶ ከክለቡ ሀላፊዎች ጋር ተነጋግሯል ተብሏል የሲቪያው አሰልጣኝ ማብሎ ማቼን የተጨዋቹ ፈላጊ ናቸው በተለይ ደግሞ ያለባቸውን የግብ ማስቆጠር ክፍተት ስላለባቸው እንደሱ ልምድ ያለው ተጨዋች ያስፈልገናል በሚል የክለቡን ሰዎች ማሳመናቸውን መረጃዎች ይዘው ወተዋል



አርሰን ቬንገር የኳታር ብ/ቡድንን እንዲያሰለጥኑ ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበር የፈረንሳዩ ፍራንስ ፉትቦል ይፋ አድርጓል ለ2022 ኳታር ለምታስተናግደው የአለም ዋንጫ ቬንገር አሰልጣኝ እንዲሆን ፈልገው ነበር ነገር ግን ቬንገር ጥያቄውን ሳይቀበሉ ቀርተዋል የቀድሞ የባርሴሎና ተጨዋች ፊሊክስ ሳንቼዝ ነው ቡድኑን እያሰለጠነ የሚገኘው አለም ዋንጫው መቃረቢያ ላይ ቡድኑ እያሳየው ባለው አቋም ፌዴሬሽኑ  ደስተኛ አደሉም ለ2022 ጥሩ ቡድን ይገነባል የሚል እምነታቸው ተሟጡዋል በዛም ምክንያት ቬንገርን ለማናገር ጥረት አድርገዋል ጥያቄውን ውድቅ ቢያረጉባቸው



ቤልጄማዊው የ31 አመት አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ ወደ ቻይና ለማምራት መቃረቡን ዘገባዎች እያሳዩ ነው ቤጂንግ ዋን የተባለው ክለብ ለልጁ 11ሚ.ፓ አቅርቧል በተደጋጋሚ ጉዳት ለቶተንሀም የሚጠበቀውን ነገር ያላደረገው ዴምቤሌ በጥሩ መልቀቁ እንደማይቀር ተነግሯል



አርሰናል ቤልጄማዊውን ካራስኮን ከቻይና ለማምጣት የተሻለ እድል አለው የሚል መረጃ እየወጣ ነው ምናልባት ማንችስተር ዩናይትድ የተሻለ ክፍያ መክፈል ሚችል ከሆነ ብቻ ካራስኮን እና አርሰናልን ሊለያቸው የሚችለው



ወደሞናኮ እንደሚሄድ እርግጥ የሆነውን ሴስክ ፋብሪጋዝን ለመተካት ቼልሲ ሁለት ተጨዋቾች ላይ አይኑን አሳርፏል የካግላሪውን ኒኮሎ ባሬላን ወይም የዜኒትፒስበርጉን ሊዮናርዶ ፓራዴዝን ከሁለት አንዳቸውን በዚ ሳምንት ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል ለክለቡ ሰዎቾም ተተኪ እንደሚፈልጉ አሳውቋቸዋል ተብሏል


አቅራቢ ኢብራሂም ሙሀመድ

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...