በጨራስ አጥቂ ችግር ውስጥ የሚገኘው ቼልሲ በውሰት ኤሲ ሚላን የሚገኘውን የ31 አመቱን አርጀንቲናዊ ጎንዛሎ ሂጎይን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሱዋል።
(Marca)
የቶተንሃሙ ሀላፊ ዳኒ ሌቪ ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ማስፈረም የሚፈልግ ክለብ £225M ማቅረብ አለበት ብለዋል፡፡ሪያል ማድሪድ የ26 አመቱን አማካይ በጥብቅ
አንደሚፈልገው ይታወቃል።
(AS - in Spanish)
የቶተንሃሙ አጥቂ ፈርናንዶ ሊዮሬንቲ ወደ ቀድሞ ክለቡ አትሌቲኮ ቢልባኦ በዚሁ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
(Mirror)
የአትሌቲኮ ቢልባኦው ሃላፊ ራፋኤል አልኮርታ የማንቸስተር ዩናይትዱን አማካይ አንደር ሄሬራ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ አንደሚፈልጉ ተናግረዋል።አዲሱ የቀያይ ሰይጣኖችሁ አለቃ ኦሊጉነር ሶልሻየር ግን ስፔናዊው አማካይ በክለቡ እንዲቆይ ይፈልጋል።
(Cadena Ser, via Mail)
ናፖሊዎች ለማንቸስተር ዩናይትድ ሴኔጋላዊውን ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ማስፈረም የሚችሉት በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት እንደሆነ ነግረዋቸዋል።
(ESPN)
የቀድሞ የአርሰናል አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር የካታር ብሄራዊ ቡድንን ለማሰልጠን በመነጋገር ላይ ናቸው።
(France Football)
ኢንተር ሚላን ኢቫን ፔሪሲችን ለማንችስተር ዩናይትድ በመሸጥ በምትኩ ሉካ ሞድሪችን ከሪያል ማድሪድ ለማዘዋወር ወጥኖ እየሰራ ነው።
(Tuttosport,via Calciomercato)
አርጀንቲናዊውን የኢንተር ሚላን የ25 አመት አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር የቼልሲው ባለቤት ሮማን አብረሃሞቪች ፍላጎቱ አላቸው።
(Mirror)
No comments:
Post a Comment