ዌልሳዊው የአርሰናል አማካይ አሮን ራምሴ በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ጁቬንቱስ ለመጓዝ ከስምምነት ላይ መድረሱን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል ።ጋዜጣው እንዳተተው ከሆነ ራምሴ የአምስት አመት ውል ይፈርማል።
(Guardian)
አትሌቲኮ ማድሪድ የ26 አመቱን ስፔናዊ የቼልሲ አጥቂ አልቫሮ ሞራታ በውሰት ወደ ዋንዳ ሜትራፖሊታኖ ለማዘዋወር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፤ ሲቪያም የተጨዋቹ ፈላጊ ነው።
(Goal)
ሪያል ማድሪድ በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ የሚፈለገውን ሴኔጋላዊውን የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ለማዘዋወር €90M አቅርቦ በመስራት ላይ ይገኛል።
(Il Mattino, via Talksport)
ዩናይትድ ሰርቢያዊውን የፊዮረንቲና ተከላካይ ኒኮላ ሚሊንኮቪች ለማዘዋወር ያለው ፍላጎት ከፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ስንብት በኋላ ቀዝቅዟል።
(ESPN)
ቶተንሀም የሳምፕዶሪያውን ተከላካይ ጆአኪም አንደርሰን ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ስፐርስ ይህንን የምታደርገው የቶቢ ኤልደርዊልድ በክለቡ መቆየት ጥያቄ ምልክት ውስጥ በመግባቱ ነው።
(Independent)
የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ማሪያ ባርቶሚዮ የ25 አመቱ ስፔናዊ አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ፍላጎቱ ከሆነ ከክለቡ መልቀቅ እንደሚችል ነግረውታል።ሱዋሬዝ ስሙ በስፋት ከአርሰናል ጋር በመያያዝ ላይ እንደሆነ ይታወቃል።
(Marca)
አርሰናል የፖርቶውን አማካይ ሄክቶር ሄሬራ ለማዘዋወር እየሰራ ይገኛል።መድፈኞቹ ሜክሲኳዊውን አማካይ የአሮን ራምሴ ቦታ እንዲሸፍንላቸው ይፈልጋሉ።
(Tutto Mercato Web)
ማንቸስትር ሲቲ የዌስት ሀሙን አይርላንዳዊ የ19 አመት አማካይ ዴክላን ሬስ በማዘዋወር የረዥም ጊዜ የፈርናንዲንሆ ተተኪ ማድረግ ይፈልጋል።
(Sun)
No comments:
Post a Comment