Friday, January 4, 2019

የቅዳሜ ማለዳ አዳዲስ ስፖርታዊ ዜናዎች

፨ቼልሲ በውሰት ኤሲ ሚላን የሚገኘውን የ31 አመቱን አርጀንቲናዊ እጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን ለማዘዋወር ከባለቤት ክለቡ ጁቬንትስ ወደ መስማማት ተቃርቧል ፤ አልቫሮ ሞራታም ወደ ኤሲ ሚላን በውሰት የሚጓዝ ይሆናል።



፨የቻይናው ሱፐር ሊግ ክለብ ቤጂንግ ሲኖቦ ጉዋን የ31 አመቱን ቤልጄሚያዊ የቶተንሀም አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።



፨ኤሲ ሚላን ስሙ በስፋት ከቶተንሀም እና ቼልሲ ጋር በመያያዝ ላይ ያለውን አይቮሪኮስታዊውን የ22 አመት አማካይ ፍራንክ ኬሲ ለማዘዋወር የሚፈልግ ክለብ €45M ማቅረብ አለበት ብሏል።



፨የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል አሮን ራምሴ በዚህ ወር ወደ ጁቬንትስ ከሚጒዝ እስከ አመቱ መጨረሻ በክለቡ እንዲቆይ ይፈልጋሉ።




፨የቀድሞው የቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ፒተር ኬናዮን ኒውካስትል ዩናይትድን ለመግዛት ከክለቡ ባለቤት ማይክ አሽሊ ጋር ንግግር ሊያደርጉ ነው ተብሏል።



፨ሊቨርፑል እንግሊዛዊውን የ30 አመት ተጨዋች አዳም ላላና በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ በየትኛውም ክለብ የመሸጥ ፍላጎት የለውም ።



፨የፓሪሰን ዤርመኑ አማካይ አድራን ራቢዮ እስከ አመቱ መጨረሻ በፓርክ ደ ፕሪንስ ቆይቶ በነጻ ወደ ባርሴሎና በአመቱ መጨረሻ የሚጓዝ ይሆናል ሲል ዘ ጋርዲያን አስነብቧል ።



፨ኦሊ ጉነር ሶልሻየር ማንቸስተር ዩናይትድ ከቀናት በፊት በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ተጨዋች ያስፈርማል ብሎ እንደማይጠብቅ ተናገረ።በተለይ ብዙዎች ቀያይ ሰይጣኖቹ የመሀል ተከላካይ ችግር እንዳለባቸው ቢናገሩም በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ቲያትር ኦፍ ድሪምስ የደረሰው ሶልሻየር ግን ዝውውር ላይ ክለቡ እምብዛም ፍላጎን እንደሌለው ተናግሯል ።



አቅራቢ አብዱልቃድር በሽር (የሪሀና ልጅ)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...