Friday, January 4, 2019

የአርብ ምሽት ስፖርታዊ መረጃዎች

➡️በዚ አመት መጨረሻ ኮንትራቱ ከአርሰናል ጋር  የሚጠናቀቀው አሮን ራምሴ ወደ ጁቬንቱስ የሚያደርገው ዝውውር  ወደመጠናቀቁ እንደደረሰ ስካይ ስፖርት አስነብቧል በቅርቡም ሊፈርም ይችላል ልጁን አሁንም በርካታ ክለቦች እየፈለጉት ነው የ11አመታት የአርሰናል ቆይታውንም አጠናቆ ሚያመራው ወደ ጁቬንቱስ እንደሆነ ስካይ አስነብቧል



➡️ባርሴሎና ከቤንጃሚን ፓቫርድ ወኪል ጋር ንግግር እያደረገ ነው የሚል መረጃ ጣሊያናዊው ፋብሪዚዮ ዲማርዚዮ ይዞ ወቷል። በክረምቱ ተጫዋቹን ወደ ካምፕኑ ለመውሰድ አስበዋል በዚህ የጥር የዝውውር መስኮት ተጨዋቹ ከስቱትጋርት እንደማይወጣ ተጨዋቹም ወኪሉም መናገራቸው ይታወሳል በቀጣይ ክረምት ግን ተጨዋቹን ለመውሰድ ናፖሊ እና ባየርንሙኒክን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ ክለቦች ይፈልጉታልና ባርሴሎናም እጁን አስገብቷል



➡️ጄርሜን ዴፎ ለ18ወራት በሚቆይ የውሰት ውል ወደሬንጀርስ ለማምራት መስማማቱን ስካይ ስፖርት አስነብቧል በዘንድሮ የስኮትላንድ ፕሪሚየር ሺፕ ሴልቲክ እና ሬንጀርስ ከፍተኛ ፉክክር እያደረጉ ነው የሚገኙት ሬንጀርስም የዘንድሮውን ዋንጫ ለመውሰድ ዋነኛ ኢላማቸው ዴፎ ነው የዝውውሩም ነገር ወደ መጠናቀቁ ደርሷል



➡️ፓሪሰን ጄርሜን ፍራንኪ ዲዮንግ እና ማታይስ ዴሊንግን ለመውሰድ ከፍተኛ ገንዘብ መመደቡን ጎል ዶትኮም አስነብቧል ለፍራንክ ዲዮንግ ብቻ ወደ 63ሚ.ፓ መድቧል ሚል መረጃ ወቷል እና ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበራት ህብረት የፌርፕሌይ ህግ አንፃር ክለቡ እየተመረመረ እንደሚገኝ  ይታወቃል። ክለቡ በቀጣይ ጊዜያት እነዚን ተጨዋቾች እንዴት ነው የሚያስፈርማቸው የሚለው ግን በጣም የሚጠበቅ ነው ነገር ግን እነኚን ሆላንዳዊያንን የማስፈረም ትልቅ እድል ያለው ባርሴሎና እንደሆነም መረጃው አያይዞ አውጥቷል።



➡️ዘንድሮ በፈረንሳይ ሊግ ደካማ ኦንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው ሞናኮ ብራዚላዊውን ተከላካይ ናልዶን አስፈርሟል ጥሩ ወጣት ተጨዋቾች ቢገኙም ልምድ ለመጨመር በሚመስል መልኩ የ36አመቱን ብራዚላዊ አስፈርመውታል በቅርቡም የቼልሲውን አማካይ ፋብሪጋዝን ለማስፈረም ከጫፍ መድረሱ ታውቋል



➡️ክርስቲያኖ ጆንቴሊ የተባሉት የናፖሊ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ጁቬንቱስ ከማምራቱ በፊት ቀድሞ ጥያቄ የቀረበልን ለኛ ነበር ነገር ግን ከፕሬዝዳንቱ ከዴላውሬንቴስ ጋር ከተነጋገርን ቡሀላ የሱን ፍላጎት ማሙዋላት ስለማንችል የገንዘብ አቅሙን ጥያቄውን ውድቅ አርገነዋል  ብለዋል።



➡️የፈረንሳዩ ማርሴይ ባላቶሊን ለማስፈረም ድጋሚ ድርድር ጀምዋል በኒስ ከቬራ ጋር ያልተስማማው ባላቶሊ በዚ የጥር የዝውውር መስኮት ወደ ሌላ ክለብ እንደሚያመራ ሲነገር ነበር ቀዳሚ ማረፊያው እዛው ፈረንሳይ ውስጥ ማርሴይ ሊሆን ይችላል የሚል መረጃ ወቷል። ከማርሴ በተጨማሪ የቤኒቴዙ ኒውካስትል ልጁን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለመመለስ ፍላጎት አላቸው ።



➡️አርሰናል ጄንጊዝ ኡንደርን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነበር ዝውውሩ ግን አልተሳካም ከዝውውሩም ራሱን አግሏል። ለልጁ ክለቡ ከፍተኛ ብር ጠይቋል አሁን የመጨረሻ አማራጩ ኒኮላስ ፔፔ ነው ተብሏል አርሰናል ለልጁ 50ሚ.ዩ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል ክለቡ ሊል ግን ለልጁ እስከ 80ሚ.ዩ ይፈልጋል ልጁም በጥር ክለቡን እንደማይለቅ ስለተናገረ አርሰናል ሌላ አማራጭ ሳይፈልግ አይቀርም



➡️በርካታ የእንግሊዝ ሚዲያዎች ዛሬ ጠዋት ይዘው በወጡት መረጃ መሰረት ማንችስተር ሲቲ በዘንድሮ ወይም በቀጣይ አመት ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሊታገድ ይችላል የየሚል መረጃዎች ወተዋል ኢቭስሊትም የአውሮፓ የእግር ኳስ የፋይናንስ ጨዋነት ደንብ ዋና ዳይሬክተር ከቤልጄም ጣቢያ ጋ ቆይታ አድርገው ነበር ይሄ ዴርሽቴብል የሚባለው የጀርመን ጋዜጣ ስለ ሲቲ የገንዘብ ፋይናንሻል ፌርፕሌይ መተላለፉን ጉዳይ በርካታ ዝርዝር ያለውን ሚስጥር ይዞ ወቶ እንደነበር ይታወሳል ስለዛ ተጠይቀው ሲመልሱ ይሄ ዴርሽቴብል ያሰራጨው መረጃ ትክክል ሆኖ ከተገኘ ምንም ጥያቄ የለውም ማን  ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሊታገዱ ይችላሉ ብለዋል



➡️አርጀንቲናዊው ማውሮ ኢካርዲ በኢንተር አዲስ ኮንትራት ሊፈርም እንደሚችል ተነግሯል ነገር ግን ኢካርዲ አሁን ከሚከፈለው እጥፍ እንዲከፈለው ይፈልጋል ወኪሉ ወደ ኢንተር ሰዎች አምርቶ ስለኮንትራቱ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለመነጋገር አሁን ሚከፈለውን ገንዘብ እጥፍ የሆነ 9ሚ.ዩ ይፈልጋሉ ተብሏል እስከ 2021  ኮንትራት እንዳለው ይታወቃል ማድሪድ የተጨዋቹ ዋነኛ ፈላጊው ነው ኮንትራት ማፍረሻውም 110ሚ.ዩ እንደሆነ ይታወቃል ማድሪድም ይሄን የመክፈል ፍላጎት እንዳለው ይታወቃል ኢንተርም ልጁን የማቆየት ፍላጎት ካለው ደሞዙን እጥፍ የመጨመር ግዴታ ውስጥ ገብቷል።




አቅራቢ ኢብራሂም ሙሀመድ

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...