Thursday, January 3, 2019

የአርብ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

፨ክርስቲያኖ ሮናልዶ የግሎብ ሶከር አዋርድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ ተመረጠ።በዱባይ በሚካሄደው በዚሁ የሽልማት ስነ ስርዓት ፖርቹጋላዊው ኮከብ። ሪያል ማድሪድ ሳለ ጁቬንቱስ ላይ ያስቆጠራት ግብም የአመቱ ምርጥ ጎል ተብላ ስትመረጥ ፈረንሳይን በመምራት የአለም ዋንጫን ያሳካው ዲዲዬ ዴሾ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ  ተብሏል።


፨በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ትናንት ሲጠበቅ የነበረው የማንቸስተር ሲቲ እና የሊቨርፑል ጨዋታ በሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል ።በጨዋታው ሲቲ በአጉዌሮ ግብ ቀዳሚ የነበረ ሲሆን ሊቨርፑል በፈርሚንሆ ግብ አቻ በመሆን ወደ ጨዋታው ለመመለስ ሞክሮ ነበር።ሆኖም ሲቲ ሳኔ ባስቆጠራት ሁለተኛ ግብ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ሊቨርፑል በአንድ የጨዋታ አጋጣሚ አደገኛ ሙከራ አድርጎ በ Goal Line Technology መሻሩ እና ኮምፓኒ ሳላህ ላይ በሰራው ጥፋት ቀይ ካርድ ማየት ነበረበት የሚለው ጉዳይ እድካሁን አነጋጋሪ ሆኗል።


፨በስፔን ላሊጋ ትናንሽ ምሽት ሪያል ማድሪድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከቪያሪያል ጋር 2 አቻ በተለያየበት ጨዋታ ጋሬዝ ቤል ጉዳት አስተናግዷል ።


፨የአርሰናሉ አማካይ አሮን ራምሴ ከጁቬንትስ ጋር ቅድመ ኮንትራት መፈራረሙ ተገልጿል ።የ28 እፕመቱ ዌልሳዊ በዚህ ወር ወደ አሮጊቷ እንደሚጓዝ ይጠበቃል።
(Sport Mediaset via Calciomercato)



፨የሲቪያው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር   ጆዋኪን ካፓሮስ ክለባቸው የቀድሞውን የሪያል ማድሪድ እና የጁቬንትስ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት በቼልሲ ቤት በመጫወት ላይ የሚገኘውን አልቫሮ ሞራታ ለማዘዋወር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል ።
(Football.London)



፨አርሰናል ሜሱት ኦዚልን በጥር ወር የዝውውር መስኮት የመሸጥ ፍላጎት ባይኖረውም ኦዚል ግን ኡናይ ኤምሬ በቂ የመሰለፍ ዕድል ካልሰጡት በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት ከክለቡ ሊለቅ ይችላል።
(Goal)



፨ቼልሲ በአሁኑ ሰዓት በውሰት ኤሲ ሚላን የሚገኘውን አርጀንቲናዊ የ32 አመት አጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከጁቬንትስ ማዘዋወር ይፈልጋል።
(Goal)



፨ስፔናዊው የቼልሲ አማካይ ሴስክ ፋብሪጋዝ በቴሪ ሄንሪ ወደ ሚሰለጥነው የፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ ለመጓዝ ተቃርቧል።ቼልሲም የ31 አመቱን ተጨዋች ቦታ ለመሸፈን ገበያ ላይ ወጥቷል።
(Calciomercato)



፨ስሙ በስፋት ከአርሰናል ጋር በመያያዝ ላይ የነበረው የሪያል ማድሪዱ ግብ ጠባቂ ኬይለር ናቫስ ለተጨማሪ አመታት በበርናቢዮ የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።ኮስታሪካዊው የግብ ዘብ እስከ 2021 የሚያቆየውን ኮንትራት ነው የተፈራረመው።
(Marca)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...