፨ክርስቲያን ኤሪክሰን በቶተንሀም ቤት አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ድርድር ጀምሯል።የ26 አመቱ አማካይ በስፐርስ የ18 ወራት ኮንትራት የቀረው ሲሆን በሪያል ማድሪድ እና በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ይፈለጋል።
(Evening Standard)
፨ጁቬንትሶች ውሉ ክረምት ላይ የሚጠናቀቀውን ዌልሳዊውን የ28 አመት የአርሰናል አማካይ አሮን ራምሴ ለማዛዋወር ፍላጎት እንዳላቸው ይፋ አድርገዋል ።
(sky Sports)
፨ዎልቭስ የ21 አመቱን የቼልሲ አጥቂ ታሚ አብርሃም ለማስፈረም £18M ለሰማያዊዎቹ አቅርቧል።ታሚ አብርሀም በአሁኑ ሰዓት በሻምፒዮን ሺፕ ለአስቶን ቪላ በውሰት በመጫወት ላይ ነው።
(Sun)
፨የጀርመናዊው ሜሱት ኦዚል ወኪል ምንም እንኳን ሪያል ማድሪድ እና ኢንተር ሚላን ኦዚልን የማዘወር ፍላጎት ቢኖራቸውም ተጨዋቹ በአርሰናል ይቆያል ብሏል።
(Goal)
፨ዋትፎርድ £50M የሚገመተውን አብዱላሂ ዶኩሬ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለፓሪሰን ዤርመን ለመሸጥ እንደማይፈልግ ይፋ አደረገ ።
(Evening Standard)
፨ፔፕ ጋርዲዮላ ሊቨርፑል ቨርጅል ቫንዳይክን ለማዘዋወር የተከላካዮች ሪከርድ £75M ማውጣቱ ትክክል እንደነበር ተናግሯል ።
ማንቸስተር ሲቲ ኔዘርላንዳዊውን ተጨዋች የማዘዋወር ፍላጎት በሳውዝሀምተን ሳለ የነበረው ቢሆንም ባለመሳካቱ ኤምሪክ ላፖርቴን ከአትሌቲክ ቢልባኦ ማስፈረሙ ይታወሳል።
ሊቨርፑል በሰድስት ነጥብ ልዩነት የሊጉ መሪ እንዲሆን ቁልፉ ሰው የሆነው ቫንዳይክ በአንፊልድ ስኬታማ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
፨ዠርደን ክሎፕ ክለባቸው በዚህ ደረጃ መገኘቱ አስገራሚ መሆኑን ተናገሩ።
ዘጠኝ ተከታታይ ጨዋታዎችን በማሸነፍ የሊጉ አናት ላይ የተቀመጠው ሊቨርፑል በዚህ ደረጃ መገኘቱ አድገራሚ መሆኑን ጀርመናዊው አሰልጣኝ ተናግረዋል ።ቀያዮቹ ዛሬ ወደ ኤቲሀድ በመጓዝ ማንቸስተር ሲቲ የሚገጥሙ ሲሆን ለ20 ጨዋታዎች የቆየው ያለመሸነፍ ሪከርዳቸው ይቀጥል ይሆን ወይ የሚለው ጉዳይ ተጠባቂ ነው።
፨ኤቨርተን ባሳለፍነው የዝውውር መስኮት ከቦርዶ ወደ ባርሴሎና ተዘዋውሮ በካታላኑ ቤት በቂ የመሰለፍ ዕድል ያላገኘውን ማልኮም ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።
(Marca)
፨አርሰናል የቋሚ ተሰላፊነት ዕድል ያጣውን ኮስታሪካዊውን የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ኬይለር ናቫስ ለማዘዋወር ለሎስብላንኮዎቹ €15M አቅርቧል።
(Sport -
in Spanish)
፨አስደናቂ ጊዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኦሊገነር ሶልሻየር በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ቋሚ ኮንትራት ተሰጥቶት ለረዥም አመታት በክለቡ መቆየት ይፈልጋል።ኖርዌያዊው አሰልጣኝ በጊዜያዊነት የስድስት ወራት ኮንትራት እንደተሰጠው ይታወሳል።
(Goal)
No comments:
Post a Comment