Monday, January 27, 2020

የዕለተ ሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

           አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ

ዩናይትዶች አሁን እንግሊዛዊውን ጀምስ ማዲሰንን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው በጥር የዝውውር መስኮት ዝውውሩ የመሳካት እድል ባይኖረውም ከክረምት በፊት ለሌስተር ይፋዊ ጥያቄ በማቅረብ ለድርድር ለመቀመጥ ዝግጁ ናቸው።




ጨራሽ አጥቂ እየፈለጉ የሚገኙት ባርሴሎናዎች ፊታቸውን ወደ ሞናኮ ዌሳም ቤንያደር አዙረው ነበር ለሞናኮም የዝውውር ጥያቄ አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል።




ሼፊልዶች ባሳለፍነው ሳምንት £20M የለጠፉበትን ጆን ፍሌክን ለመሸጥ ፍላጎት አሳይተዋል አርሰናል ልጁን ለማስፈረም ፍላጎት ያለው ክለብ ሆኗል።




በዩናይትድ እና በቸልሲ በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ኡራጊያዊው አጥቂ ኤዲሰን ካቫኒ በመጨረሻም አትሌቲኮ ማድሪድን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል በተቀሩት የዝውውር ቀናት ወደ አትሌቲኮ ማምራቱ እርግጥ ሆኗል።




ጁቬንቱስ ወጣቱን አማካይ ኢንዞ ባሬንቻን ዝውውር ለማጠናቀቅ ከጫፍ ደርሰዋል።




ማርኮስ ሮኾ ወደ ሀገሩ ክለብ ኢስቱዴንቴ በውሰት ውል ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል ዩናይትዶች ልጁን ለመሸጥ ቢፈልጉም እስካሁን ገዢ አደለሁም።





አርሰናሎች የፓብሎ ማሪን ዝውውር ዛሬ አልያም ነገ ይፋ ያደርጋሉ ተጨዋቹ የጤና ምርመራውን ዛሬ እንደሚያደርግ ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ዘግበውታል።




የዩናይትድ ተጨዋቾች በቦርዱ የተተወ አይነት ስሜት እየተሰማቸው ነው ምክንያቱ ደሞ ቦርዱ ሉካኩን እና ሳንቼዝን እና ሄሬራን ሲለቅ ሌላ ተጨዋች አለመተካቱ ነው በተጨማሪም ሀላንድን በዚህ የዝውውር መስኮት አለማስፈረማቸው ነው።




ክሪስቲያን ኤሪክሰን ዛሬ ዝውውሩን ለመጨረስ ወደ ጣሊያን ያመራል ሜዲካሉን ዛሬ ካደረገ ቡሀላ በይፋ የኢንተር ሚላን ንብረት ይሆናል።

Saturday, January 25, 2020

የዕለተ እሁድ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ




የዩናይትድእና ስፖርቲንግ ባለስልጣናት በብሩኖ ጉዳይ ትላንት በስልክ ተወያይተዋልዛሬም ንግግሩ ይቀጥላል ዩናይትዶች ለመጨረሻ ጊዜ ላቀረቡት 55ሚ. እና 10ሚ. እየታየ ሚጨመር ጥያቄ ከስፖርቲንጎች መልስ እየጠበቁ ነው።




አርሰናል ፓብሎ ማሪን ለማስፈረም እየሰራ ያለው እስከሲዝኑ መጨረሻ በውሰት ክረምት ላይ ቋሚ የሚደረግበት እድል የተካተተበት ነው ተብሏል።



ኤምሪ ካን ጁቬንቱስን በመልቀቅ ቦሩሲያ ዶርትመንድን ለመቀላቀል ንግግር መጀመሩ ይፋ ተደርጓል።




ጄርሜንዴፎ በርንማውዝን በመልቀቅ ሬንጀርስን በአንድ አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ተደርጓል።



አርቢሌብዢኮች በተለያዩ ክለቦች ሲፈለግ የነበረውን ስፔናዊውን የ21 አመት አማካይ ዳኒ ኦልሞን ከዳይናሞ ዛግሬብ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።





ኢንተር ሚላን እና ናፖሊ በማቲዮ ፖሊታኖ ዝውውር ጉዳይ ከስምምነት ደረሱ ተጨዋቹ ወደ ናፖሊ ሚያመራው በውሰት ነው ሰኞ የጤና ምርመራ እንደሚያደርግ ታውቋል።




ኤሲ ሚላኖች የቤኔፊካውን ተጫዋች ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ 18 ወራት ለሚቆይ የውሰት ውል ለማስፈረም ይፈልጋል ቤኔፊካ በውሰት የሚሰጥ ከሆነ £50m የመግዛት አማራጭ ጋር ነው የሚፈልገው።




ፓውሎዲባላ  ጁቬንቱስን ለመልቀቅ ተቃርቧል ዲባላ ስሙ ከዩናይትድ እና ከቶተንሀም ጋር በስፋት እየተያያዘ ይገኛል።

Friday, January 24, 2020

የዕለተ ቅዳሜ ስፖርታዊ ዜናዎች

               አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የሀገር ውስጥ ዜናዎች

ዛሬ እና ነገ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች መርሃ ግብር

ቅዳሜ
ስሑል ሽረ ከ ጅማ አባ ጅፋር - 9:00
ሰበታ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ - 9:00
ወላይታ ድቻ ከ መቐለ 70 አ.  - 9:00


እሁድ
ወልቂጤ ከተማ ከ ድሬደዋ ከተማ - 9:00
አዳማ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና  - 9:00
ፋሲል ከተማ ከ ሲዳማ ቡና - 9:00
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ባህር ዳር ከተማ - 9:00
ወልዋሎ ዓ.ዩ. ከ ኢትዮጵያ ቡና - 9:00

ምንጭ -ሶከር ኢትዮጵያ




የውጭ ሀገር ዜናዎች


የቶተንሃሙ አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል በቀጣዩ ሳምንት ለህክምና ምርመራ ወደ ሚላን እንደሚያመራ ይጠበቃል።ዴንማርካዊው ኢንተርናሽናል በጣሊያኑ ክለብ ሳምንታዊ £320,000 ደሞዝ እንደሚከፈለውም ተነግሯል።
(Sky Sports)





ማንቸስተር ዩናይትድ በቀጣይ ሳምንት ከዎልቭስ ጋር በሚኖረው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ደጋፊዎች የግሌዘር ቤተሰቦችን እና ኢድ ውድ ዋርድን በመቃወም ጨዋታው ሳይጠናቀቅ ከስቴዲየሙ ለመውጣት አቅደዋል።
(Mirror)





ሱዋሬዝን በጉዳት ለወራት ያህል ያጣው ባርሴሎና ምናልባትም አስገራሚ በሆነ መልኩ ፈረንሳዊውን የቼልሲ አጥቂ ኦሊቪየር ዥሩ ሊያዘዋውር ይችላል።
(Independent, via Mail)





አርሰናል ፈረንሳዊውን የክንፍ አጥቂ ቶማስ ሌማር ለማዘዋወር በአዲስ መልኩ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ድርድር ጀምሯል።
(RMC Sport, via Talksport)





ቶተንሃም የኤሲ ሚናኑን ፖላንዳዊ አጥቂ ፒያቴክ ለማዘዋወር ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም።ስፐርስ ለተጨዋቹ ዝውውር £30ሚ. አቅርቦ የነበረ ሲሆን ምናልባትም በዝውውር መስኮቱ መዝጊያ ግን ሊሳካ የሚችልበት ዕድል አለ።
(Star)





ሮማ ቤልጄሚያዊውን የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ በአሁኑ ሰዓት ሪያል ሶሴዳድ የሚገኘውን የክንፍ አጥቂ አድናን ያኑዛይ ለማዘዋወር እየሰራ ይገኛል።
(Calciomercato)





ብራዚላዊው ጋብሬል ማርቲኔሊ በሪያል ማድሪድ መፈለጉን ተከትሎ አርሰናል የተጨዋቹን ደሞዝ ሶስት እጥፍ በማሳደግ ሳምንታዊ  £30,000 ሊያደርግለት አቅዷል።
(Mail)





ቶተንሃም ኬንያዊውን አማካይ ቪክቶር ዋኒያማ የሚገዛው እምብዛም ባለማግኘቱ ተጨዋቹን ከ£7ሚ. በታች ለመሸጥ ወስኗል።
(Standard)





ሊቨርፑል በባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ በጥብቅ የሚፈልገውን የቤኔፊካውን ፖርቱጋላዊ ታዳጊ ራፋኤል ብሪቶ ለማዘዋወር የተጨዋቹን የውል ማፍረሻ £38ሚ. ለመክፈል ተሰናድቷል።
(Record via Star)

የዕለተ አርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች



ክርስቲያን ኤሪክሰን እና ኢንተር ሚላን ከስምምነት  ደርሰዋል እስከ ሰኞም ዝውውሩ ይጠናቀቃል ኢንተሮች ለኤሪክሰን የአራት አመት ከግማሽ አመት ኮንትራት እና ሳምንታዊ 260ሺ.ፓየሚከፍሉትይሆናል




ኒውካስትሎችየኢንተርሚላኑን ቫለንቲኖ ላዛሮን እስከዚህ አመት መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል አስፈርመውታል





በዘንድሮየውድድርአመት ከማድሪድ አርሰናልን በውሰት ተቀላቅሎ ብዙም ግልጋሎት ያልሰጠው ዳኒ ሴባዮስ ዩሮ 2020 ላይ ለብሄራዊ ቡድን ለመጠራት ሲል ወደ ማድሪድ ውሰቱን አቋርጦ መመለስ እንደሚፈለግ ተሰምቷል




በርንማውዞችኒውካስትልንበመከተል የዳኒ ሮዝን ዝውውር ተቀላቅለዋል በጥር የዝውውር መስኮት መልቀቁ አይቀሬ የሚመስለው ሮዝ አሁንም በተለያዩ የእንግሊዝ ክለቦች መፈለጉ ቀጥሏል





ኤሲሚላኖችለዊጋኑየ22 አመቱ አንቶኒ ሮቢንሰንን ለማስፈረም ዊጋኖች ሚፈልጉትን £10m ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ይፋ አርገዋል





ብራይተኖችበይፋየሀደርስፊልድ ንብረት የሆነውን አሮን ሞይን ሶስት አመት ከግማሽ አመት በሆነ ውል በ£5m አስፈርመውታል




ዩናይትዶችየፒኤስጂውንአማካይ ኤሪክ ኢቢምቤን እስከ አመቱ መጨረሻ በውሰት ለማስፈረም ከፒኤስጂ ጋር ንግግር እንደጀመሩ ተሰምቷል




አርሰናሎችኦባምያንግንለመልቀቅ ፍቃደኛ አደሉም ዛሬ በወጡ መረጃዎች ባርሴሎናዎች ለተጨዋቹ £70m ለመክፈል ዝግጁ ናቸው ከተጨዋቹ በግል ከስምምነት እንደደረሱ የካታሎን ጋዜጦች ቢፅፉም አርሰናሎች ግን ልጁን ለመልቀቅ ፍቃደኛ አደሉም




ክሪስታልፓላሶችየቀድሞውን የአትሌቲኮ ማድሪድ አጥቂ ያኒክ ካራስኮን ለማምጣት ፍላጎት አላቸው

Thursday, January 23, 2020

የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

ትናንት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተደረገ ጨዋታ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ፈታኙን ዎልቭስ በቫን ዳይክ እና ፈርሚንሆ ጎሎች ማሸነፍ ችሏል።በዚህም ሊቨርፑል ለተከታታይ 40 የሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፈም።




ማንቸስተር ዩናይትድ የቀድሞው ተጨዋቹን አርጀንቲናዊውን ኮከብ ካርሎስ ቴቬዝ ለጥቂት ጊዜ ሳይጠበቅ ሊያዘዋውረው አቅዷል።ቴቬዝ አሁን 35ተኛ አመቱ ላይ ሲገኝ በሀገሩ ክለብ ቦካ ጁኒየርስ በመጫወት ላይ ይገኛል።
(Tuttosport)





ቶተንሃም ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ለኢንተር ሚላን በ£20ሚ. ለመሸጥ በመርህ ደረጃ ተስማምቷል።ኤሪክሰን በተለይ ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር እምብዛም አለመስማማቱ ከክለቡ እንዲለቅ ምክንያት ሳይሆነው እንዳልቀረ ይገመታል።
(Sempreinter.com)





ቼልሲ በድጋሚ ፈረንሳዊውን አጥቂ ሞሳ ዴምቤሌ ከሊዮን ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሰማያዊዎቹ የ23 አመቱ አጥቂ ከዚህ በፊት ለማዘዋወር ሞክረው ባይሳካላቸውም አሁን የዝውውር ሂሳቡን ጨምረው ተጨዋቹን ስታንፎርድ ብሪጅ ለማክተም ወጥነው በመስራት ላይ ናቸው።
(Sun)




ማንቸስተር ዩናይትድ በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ኡራጋዊውን አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ ከፓሪሰን ዤርመን ለማዘዋወር በመስራት ላይ ይገኛል።
(Telegraph)




ጋቦናዊው የአርሰናል አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ የካታላኑን ክለብ ባርሴሎና ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል ሲል የካታላኑ ጋዜጣ ሙንዶ ዲፖርቲቮ አስነብቧል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)





ብሩኖ ፈርናንዴዝ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ሊያደርገው የነበረው ዝውውር ያለ መስማማት ተጠናቋል።ምክንያቱ ደግሞ ክለቡ ስፖርቲንግ ሊዝበን የጠየቀውን £68ሚ. ማን ዩናይትድ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው።
(Mail)




ሊቨርፑል ስፔናዊውን አማካይ ኢስኮ ከሪያል ማድሪድ ለማዘዋወር ፍላጎት አለው።ሎስብላንኮዎቹ ለተጨዋቹ £59ሚ. እንዲቀርብላቸው ይፈልጋሉ።
 (El Desmarque - in Spanish)





ኢንተር ሚላን የናፖሊውን አጥቂ ፈርናንዶ ሊዮሬንቴ ለማዘዋወር ጥያቄ አቅርቧል።አንቶኒዮ ኮንቴ በዋናነት ሲፈልገው የነበረው የቼልሲውን ኦሊቪየር ዥሩ የነበረ ቢሆንም ባለመሳካቱ ፊቱን ወደ ሊዮሬንቴ አዙሯል።
( Sky Sports )





ቶተንሃም የሪያል ሶሴዳዱን ብራዚላዊ አጥቂ ዊልያን ሆዜ ለማዘዋወር እየሰራ ሲሆን የዝውውር ገንዘቡን በጥቂቱ ካሳደገ ተጨዋቹን የማግኘት ዕድሉ ሰፊ ነው።
( ESPN )






የዕለተ ሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                        አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ



ከቶተንሀም በጥር አልያም በክረምት ሊለቅ እንደሚችል እየተነገረ የሚገኘውን ዳኒ ሮዝን ለማስፈረም ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ፍላጎት እንዳላቸው ተሰምቷል




ሌስተሮችየሳውዛንብተኑን ተከላካይ ጃኒክ ቬስትሬጋርድን ለማስፈረም እስከ £15m ለማውጣት ዝግጁ ሆነዋል በቀጣይ ሳምንት ዝውውሩ ሳይዘጋ ልጁን ለማምጣት እየሰሩ ነው





የጀደን ሳንቾ በብዙ ክለብ መፈለግ እና በክረምቱ ክለቡን መልቀቁ አይቀሬ መሆኑን ተከትሎ ዶርትመንዶች እሱን ለመተካት አይናቸውን ወደ ብራዚል ክለብ ኮከቦች ጥለዋል የግሬሜሮን ኤቨርተን እና የሳኦፖሎውን አንቶኒን ሳንቾን ለመተካት እጩ አርገዋቸዋል




ዌስትሀምዩናይትዶች የቀድሞውን ተጨዋቻቸውን ዲምትሪ ፓየትን መመለስ ይፈልጋሉ ነገር ግን ዝውውሩ የመሳካቱ እድል እጅግ የጠበበ መሆኑ ተሰምቷል




ማንችስተርዩናይትድ እና ባርሴሎና አርጀንቲናዊውን ኮከብ ላውታሮ ማሬቲኔዝን ለማስፈረም £100m ለማውጣት ፍቃደኛ ሆነዋል




ሲቪያዎችየሬንጀርሱን አጥቂ አልፍሪዶ ሞላሬስን በጥር የዝውውር መስኮት የማስፈረም ፍላጎት አላቸው




ኢንተርሚላኖች ዩናይትዶች ያቀረቡትን የማቲያስ ቬሲኖን የውሰት ዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርገውባቸዋል




ዌስትሀሞችበዚህ የዝውውር መስኮት የበርንማውዙን ሪያን ፍሬዘርን ማስፈረም ይፈልጋሉ ተጨዋቹ በዚህ የውድድር አመት ኮንትራቱን ይጨርሳል



አርሰናሎችዩክሬናዊውን ተከላካም ማትቪየንኮን ለማስፈረም ከሻካታር ዶኔስኮች ጋር ንግግር እንደጀመሩ የተጨዋቹ ወኪል ይፋ አድርጓል




ከትናንትምሽቱ የበርንሌ ሽንፈት  ቡሀላ በርካታ ጫና እየደረሰበት የሚገኘው ሶልሻየር ከክለቡ ቦርድ ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ስካይ ስፖርት አረጋግጫለው ብሏል

የዕለተ ሐሙስ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ቶተንሃም የሪያል ሶሴዳዱን ብራዚላዊ አጥቂ ዊልያን ጆዜ ለማዘዋወር ድርድር ጀምሯል።የ28 አመቱ አጥቁ ለንግግር ወደ ለንደን ማምራቱም ታውቋል።ቶተንሃም አጥቂውን ሀሪ ኬንን በጉዳት ለአራት ወራት እንዳጣ ይታወቃል።
(AS)





ቼልሲ ኡራጋዊውን አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ እስከ አመቱ መጨረሻ በውሰት ለመውሰድ ለፓሪሰን ዤርመን ጥያቄ አቅርቧል።ካቫኒ በበርካታ ክለቦች የሚፈለግ ሲሆን ወላጅ አባቱ አትሌቲኮ ማድሪድን ልጁ እንደሚቀላቀል ተናግሮ ነበር።
(Times - subscription required)





ፓሪሰን ዤርመን ፈረንሳዊውን ተከላካይ ላይቪን ኩርዛዋ ለአርሰናል ለመሸጥ €5ሚ. ጠይቋል።የ27 አመቱ ተከላካይ በፓርክ ደ ፕሪንስ ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ ይጠናቀቃል።
(Telegraph)





ሪያል ማድሪድ ዌልሳዊውን አጥቂ ጋሬዝ ቤል ወደ ቀድሞው ክለቡ ቶተንሃም ለመመለስ በቂ ገንዘብ ከቀረበለት ፈቃደኛ ነው።
(Telegraph)






ባየርን ሙኒክ ፌሊፔ ኩቲንሆን በቋሚነት የማዘዋወር ዕድሉን መጠቀም አልፈለገም።ባየርን ሙኒክ ብራዚላዊውን አማካይ ከባርሴሎና በውሰት ሲወስድ ከፈለገ በቋሚነት ማዘዋወር እንደሚችል የሚጠቅስ ውሉ የነበረው ቢሆንም አሁን ግን ተጨዋቹን ማዘዋወር አይሻም።
 (Bild, via Mirror)





ስድስት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እንግሊዛዊውን የቶተንሃም የግራ መስመር ተከላካይ ዳኒ ሮዝ ለማዘዋወር ጥያቄ አቅርበዋል።ሮዝ በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ስፐርስን ሊለቅ እንደሚችል ይጠበቃል።
(Sky Sports)





በማንቸስተር ሲቲ በጥብቅ የሚፈለገው ዩክሬናዊውን የሻካታር ዶኔስክ ተከላካይ ሚኮላ ማትቪዬንኮ ከአርሰናል ጋር ድርድር መጀመሩን ወኪሉ ይፋ አድርጓል።
(Football London)





የአርሰናሉ የ18 አመት አጥቂ ጋብሬል ማርቲኔሊ በአመቱ መጨረሻ ውሉ ተሻሽሎ ደሞዙ አሁን ካለው ሶስት እጥፍ እንዲሆን ይፈልጋል።ማርቲኔሊ በሪያል ማድሪድ ይፈለጋል።
(Mail)





ባርሴሎና ጋቦናዊውን የአርሰናል አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ለማዘዋወር በተደጋጋሚ ሞክሮ ባለመሳካቱ የቫሌንሲያውን  ስፔናዊ አጥቂ ሮድሪጎ ሞሬኖ በውሰት ለመውሰድ ከጫፍ ደርሷል።
(Sport)

Wednesday, January 22, 2020

የዕለተ ረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                      አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

ማርከስ ራሽፎርድን በጉዳት ለሳምንታት ሚያጡት ዩናይትዶች ፊታቸውን ወደ ፖላንዳዊው የኤሲሚላን አጥቂ ፒያቴክ ማዞራቸውን የጣሊያን ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ




በክለቡ ባየርን ሙኒክ እንደማይፈለግ የተነገረውን ቦአቴንግን አርሰናሎች በዚህ የዝውውር መስኮት በውሰት ለማስፈረም ፍላጎታቸው ጨምሯል




ባሳለፍነው ሳምንት ከፒኤስጂ መልቀቅ እንደሚፈልግ ይፋ ያደረገውን ኤዲሰን ካቫኒን ለማስፈረም በርካታ ክለቦች ቢፈልጉም ቸልሲዎች ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ተቃርበዋል ለተጨዋቹ ቸልሲዎች የአንድ አመት ከግማሽ አመት ኮንትራት እና ዳጎስ ያለ ክፍያ አቅርበውለታል




የዴቪድ ቤካሙ ክለብ ኢንተር ሚያሚ የማንችስተር ሲቲውን አጥቂ ኩን አጉዌሮን በ2021 ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ማስፈረም እንደሚፈልግ ታውቋል




ባየርን ሙኒክ የሪያል ማድሪዱን ቀኝ መስመር ተመላላሽ አልቫሮ ኦርዲዮዞላ በግማሽ አመት የውሰት ውል ዛሬ አስፈርመውታል




ሼፍልድ ዩናይትዶች በአርሰናል የሚፈለገውን ጆን ፍሌክ ላይ £20m ዋጋ ለጥፈውበታል





ባርሴሎናዎች የሱዋሬዝ መጎዳትን ተከትሎ አጥቂዎችን እየፈለገ ይገኛል የኢንተር ሚላኑን ላውታሮ ማርቲኔዝ የመጀመሪያ ምርጫቸው አርገውታል ኢንተር ለተጨዋቹ የጠየቁትን £110m  ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል




በርንማውዞች የቀድሞውን የቸልሲ አጥቂ በርናንድ ትራኦሬን ከሊዮን ለማስፈረም ወደ £35m በማውጣት ልጁን ለማስረም ይፈልጋሉ




ሊቨርፑሎች በክለቡ የመሰለፍ እድል እየተሰጠው የማይገኘውን ዤርዳን ሻኪሪን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ለመሸጥ ፍቃደኛ መሆናቸው ተረጋግጧል ለልጁም እስከ £25m ይፈልጋሉ ነገር ግን በዚህ የዝውውር መስኮት ልጁን የመሸጥ ፍላጎት የላቸውም




ማንችስተር ሲቲ እና ፒኤስጂ አዲሱ ፔርሎ እየተባለ የሚጠራውን የብሬሺያ አማካይ ሳንድሮ ቶናሊን ለማስፈረም በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ተጨዋቹ እስከ £40m ያወጣል




ክሪስቲያን ኤሪክሰን በይፋ ትናንትና ለቶተንሀሞች የልቀቁኝ ደብዳቤ አስገብቷል

ለረዥም ጨዋታ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያልተሸነፉ 10 ክለቦች

ለረዥም ጨዋታ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያልተሸነፉ 10 ክለቦች

             አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


የዓለማችን ውዱ ሊግ በሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዘመናት ልዩነት አያሌ ድንቅ ቡድኖችን ተመልክተናል።ለዛሬ በዚህ ታላቅ ሊግ በተከታታይ ለብዙ ጨዋታ ያልተሸነፉትን 10 ቡድኖች እነሆ ብለናል


=9. ኖቲንግሃም ፎሬስት (1995) - 25 ጨዋታዎችን በተከታታይ አልተረታም



=9.ማንቸስተር ዩናይትድ (2016/17) - 25 ጨዋታዎችን በተከታታይ አልተረታም




=6. ማንቸስተር ዩናይትድ (2010-11) - 29 ጨዋታዎችን በተከታታይ አልተረታም





=6. ቼልሲ (2007/08) -  29 ጨዋታዎችን በተከታታይ አልተረታም





=6. ማንቸስተር ዩናይትድ (1998/99) - 29 ጨዋታዎችን በተከታታይ አልተረታም





=4. ማንቸስተር ሲቲ (2017/18) - 30 ጨዋታዎችን በተከታታይ አልተረታም




=4. አርሰናል  (2001/02) - 30 ጨዋታዎችን በተከታታይ አልተረታም



3.ቼልሲ (2004/05) - 40 ጨዋታዎች



2. ሊቨርፑል  (2019-? ) - የዚህ አመቱ ሊቨርፑል እስከ እዚህ ጽሁፍ ድረስ 42 ጨዋታዎችን አልተሸነፈም




2.ቼልሲ (2004/05) - 40 ጨዋታዎች




1.አርሰናል (2003/04) - 49 ጨዋታዎች

Tuesday, January 21, 2020

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ስፖርታዊ ዜናዎች

                  አቅራቢ  - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

                             የሀገር ውስጥ ዜናዎች


የ2022 የኳታር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ ድልድል የወጣ ሲሆን ኢትዮጵያ በምድብ G ከጋና ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ጋር ተደልድላለች።ኢትዮጵያ በዚህ ምድብ የመጀመሪያውን ጨዋታ በፈረንጆቹ ሴብቴምበር ወር የምታደርግ ይሆናል።
(Soccer Ethiopia)





                                 የውጭ ሀገር ዜናዎች



የዴቪድ ቤካም ክለብ የሆነው የሜጀር ሊግ ሶከሩ ኢንተር ሚያሚ ከአርጀንቲናዊው የማንቸስተር ሲቲ ኮከብ ኩን አጉዌሮ እና ስፓኒያርዱ ዴቪድ ሲልቫ ወኪሎች ጋር ንግግር ጀምሯል።
(Sun)





ከበርካታ ተደጋጋሚ እና አሰልቺ ጥያቄዎች በኋላ ማንቸስተር ዩናይትድ ፖርቱጋላዊውን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ማስፈረሙን በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
(Mirror)




ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ የቀኝ መስመር ተከላካይ አልቫሮ ኦሪዮዞላ ባየርን ሙኒክን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራ ለማድረግ ወደ ጀርመን ተጉዟል።የ24 አመቱ ተጨዋች ቀሪውን ሲዝን በባቫሪያው ክለብ የሚያሳልፍ ይሆናል።
(AS - in Spanish)




አዲሱ የባርሴሎና አሰልጣኝ ኪዮንኬ ሲቴይን ሊውስ ሱዋሬዝ መጎዳቱን ተከትሎ የሱን ቦታ ለመተካት አዲስ አጥቂ እንደሚያስፈርሙ ተናግረዋል።ዋነኛው እቅዳቸው ደግሞ የቫሌንሲያው ስፔናዊ አጥቂ ሮድሪጎ ሞሬኖ ነው።
(Marca)





የሌስተር ሲቲውን አልጄሪያዊ አጥቂ ኢስላም ስሌማኒ ለማዘዋወር ቶተንሃም ጥረት በማድረግ ላይ ነው።ጆዜ ሞሪንሆ የሀሪ ኬንን የረዥም ጊዜ ጉዳት ለመሸፈን አዲስ አጥቂ ይፈልጋሉ።
(Leicester Mercury)






ባርሴሎና ጋቦናዊውን የአርሰናል አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ኦባማያንግ እስከ ቀጣዩ አመት በአርሰናል የሚቆይ ከሆነ በውሉ መሰረት £15ሚ. የታማኝነት ክፍያ የሚከፈለው ሲሆን ከዛ በፊት ክለቡን ከለቀቀ ግን ያንን ያጣል።
(Star)




አሜሪካዊው ቢሊየነር ዳን ፍሬድኪን የጣሊያኑን ክለብ ሮማ ለመግዛት ለውይይት ሚላን ገብተዋል።
(Corriere dello Sport - in Italian)





ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች መርሃ ግብር

ሌስተር ሲቲ ከ ዌስት ሀም ዩናይትድ - 4:30

ቶተንሃም ሆትስፐር ከ ኖርዊች ሲቲ - 4:30

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ በርንሌይ - 5:15

የዕለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


የቀድሞ የዩናይትድ ኮከብ ሀቪየር ሄርናንዴዝ ቺቻሪቶ ወደ አሜሪካኑ ኤልኤ ጋላክሲ ተዘዋውሯል




ኒውካስትል ዩናይትዶች የቀድሞውን የቶተንሀም ተጨዋች ነቢል ቤንታሌብን እስከዚ የውድድር አመት መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል አስፈርመውታል




ኦልምፒክ ሊዮኖች ካርልቶኮ ኢካምቢን ከቪያሪያል £17m አስፈርመዋል




ኢንተር ሚላን ናይጄሪያዊውን ቪክተር ሞሰስን ከፊነርባቼ በውሰት ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል ከደቂቃዎች ፊት ሞሰስ በጣሊያን መታየቱን ታማኝ ሚባሉ ምንጮች በፎቶ አስደግፈው አውጥተውታ




አስቶንቪላ የጌንኩን አጥቂ ምብዋና ሳማታን በ £10m አራት አመት ከግማሽ አመት በሚቆይ ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አርገዋል




ወልቭሶች የኦሎምፒኮሱን የመስመር ተጨዋች ዳንኤል ፖዴንስን በ£21m ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል




ሼፍልድ ዩናይትዶች ጃክ ሮቢንሰንን ከኖቲንግሀም ሁለት አመት ከግማሽ አመት በሚቆይ ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል




አርሰናሎች ጀርመናዊውን ተከላካይ ጄሮሜ ቡአቴንግን የዝውውር መስኮቱ ሳይዘጋ ማስፈረም ይፈልጋሉ





ዩናይትድ እና ስፖርቲንግ ሊዝበኖች በብሩኖ ፈርናንዴዝ ዝውውር ላይ ከስምምነት ደርሰዋል ዩናይትዶች ዝውውሩን በቀጣይ ሳምንት እንደሚጨርሱ ተማምነዋል

የዕለተ ማክሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

ማንችስተር ሲቲዎች ፖርቹጋላዊውን የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ብሩኖ ፈርናንዴዝን ለማዘዋወር ዩናይትዶች ላይ ገብተውባቸዋል ይህንን ተከትሎ የልጁ የዝውውር ሂሳብ እስከ €100m ከፍ እንደሚል ተሰምቷል




በርንማውዞች የቦሩሲያ ዶርትመንዱን የመስመር ተጨዋች ጃኮብ ብሩን ላርሰንን በውሰት ለማስፈረም ንግግር ጀምረዋል በቋሚነት ማስፈረም ከፈለጉ ከ£13m እስከ £15m ያሶጣቸዋል




አርሰናሎች በአመቱ መጨረሻ በነፃ ያገኙታል ሲባል የቆየው የፒኤስጂው የግራ መስመር ተከላካይ ላይቪን ኮርዙዋን በጥር የዝውውር መስኮት ለማምጣት ፍላጎት አሳይተዋል ፒኤስጂ ከልጁ £6m ይፈልጋል




ክርስቲያን ኤሪክሰን ወደ ኢንተር ሚላን ለማምራት ከጫፍ ደርሱዋል በዚህ ሳምንት ዝውውሩ ይጠናቀቃል በቶተንሀም እና ኢንተር መካከል የነበረው ድርድር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል




የፒኤስጂው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሊዮናርዶ ካቫኒ ፒኤስጂን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረቡን ይፋ አርገዋል አያይዘውም ከዚህ በፊት ከአትሌቲኮ ማድሪድ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ እንዳደረጉም ተናግረዋል




ኤሲሚላኖች ጀርመናዊውን የጁቬንቱስ አማካይ ኤምሪ ካንን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው ከኤሲሚላን በተጨማሪ በብዙ ክለቦች ይፈለጋል




ሮማዎች የቀድሞውን የዩናይትድ ተጨዋች አድናን ያኑዛይን ከሪያል ሶሴዳድ በውሰት ማስፈረም እንደሚፈልጉ እና አመቱ ሲጠናቀቅ £13m በመክፈል ቋሚ ማድረግ ይፈልጋሉ




ፒኤስጂዎች ሴኔጋላዊውን የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊን ማስፈረም ይፈልጋሉ ለልጁም አመታዊ £12m ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል




ጁቬንቱሶች ፈርናንዶ ቤርናንዴስኪን ለባርሴሎና በመስጠት ኢቫን ራኪቲችን ለመቀያየር ንግግር ጀምረዋል





ዩናይትዶች የብሩኖ ፈርናንዴዝ ዝውውር ድርድር መቋረጡን ተከትሎ በጥር ለማዘዋወር ቢከብድም ፊታቸውን ወደ ሌስተሩ ኮከብ ማዲሰን አዙረዋል በሌላ ዘገባ ዩናይትድ እና ስፖርቲትግ ሊዝበን ለድርድር በዚህ ሳምንት ድጋሚ እንደሚቀመጡ ተነግሯል

Sunday, January 12, 2020

የዕለተ ሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


የውጭ ስፖርታዊ ዜናዎች


ቶተንሃም የቤኔፊካውን አማካይ  ጌድሰን ፈርናንዴዝ ለአስራ ስምንት ወራት በውሰት ለመውሰድ ከጫፍ ደርሷል።ዌስት ሀምም የ21 አመቱ አማካይ ፈላጊ ቢሆንም ስፐርስ ተጨዋቹን የማግኘት ከፍተኛ ዕድል አላት።
(Sunday Mirror)





ስሙ በስፋት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ የቆየው የአያክሱ ሆላንዳዊ አማካይ ዶኒ ቫን ደ ቢክ በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት ክለቡን እንደማይለቅ ተናግሯል።
(Fox Sports Netherlands, via ESPN)




ማንቸስተር ዩናይትድ ፖርቱጋላዊውን የስፖርቲንግ ሊዝበን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለማዘዋወር አርጀንቲናዊውን ማርከስ ሮሆ እና £60ሚ. አቅርቧል።
(Talksport)





የርገን ክሎፕ የባርሴሎናውን ፈረንሳዊ አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ ወደ አንፊልድ ማምጣት ይሻሉ።በዘንድሮው አመት ድንቅ ጊዜን በፕሪሚየር ሊጉ እያሳለፈ የሚገኘው ሊቨርፑል ሻምፒዮን የመሆን ዕድሉን አስፍቷል።
(ElDesmarque - in Spanish)





የርገን ክሎፕ ፈርሚንሆ ይቅርታ እንደጠየቃቸው ተናገሩ።ትናንት ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ቶተንሃምን በረታበት ጨዋታ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረውን ፈርሚንሆ ከጨዋታው በኋላ ክሎፕ ሊያቅፉት ሲሄዱ "ከዚህ በላይ ግብ ማስቆጠር ነበረብኝ" በማለት ይቅርታ እንደጠየቃቸው ተናግረዋል።
(Goal)





ኢንተር ሚላን ክርስቲያን ኤሪክሰንን ለማዘዋወር ስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን ዴንማርካዊው አማካይም እስከ 2024 በሳንሲሮ የሚቆይ ይመስላል።ኤሪክሰን በአመት €7.5ሚ. እንደሚከፈለውም ተነግሯል።
(Gazzetta dello Sport)











ማንቸስተር ሲቲ የመሀል ተከላካይ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ለማስፈረም እየሰራ ነው።ውሃ ሰማያዊዎቹ የኤምሪክ ላፖርቴን መጎዳት ተከትሎ ፈርናንዲንሆን በመሀል ተከላካይነት ለመጠቀም ተገደው እንደነበር ይታወሳል።
(Times)





ቶተንሃም የሳውዝሀምተኑን አጥቂ ዳኒ ኢንግስ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሀሪ ኬን ለሶስት ወራት ከሜዳ ውጪ እንደሚሆን ይፋ መደረጉን ተከትሎ ስፐርስ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ለማስፈረም ወደ ገበያ ወጥታለች።
(Daily Star)





የአርትሮ ቪዳል ቆይታ በኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ቆይታ ላይ ይወሰናል።ቫልቬርዴ ከክለቡ የሚሰናበቱ ከሆነ ቪዳል ወደ ኢንተር ሚላን እንደሚጓዝ ይጠበቃል።
(Mundo Deportivo)










Friday, January 10, 2020

የዕለተ ቅዳሜ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                    አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


የሀገር ውስጥ ስፖርታዊ ዜናዎች
ስምንተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መርሃ ግብር

ቅዳሜ
ሰበታ ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር - 9:00

እሁድ
ወልዋሎ ከ ሀዲያ ሆሳዕና - 9:00
ወላይታ ድቻ ከ ስሑል ሽረ - 9:00
አዳማ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ - 9:00
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬደዋ ከተማ - 9:00
ሲዳማ ቡና ከ ባህር ዳር ከተማ - 9:00
ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጵያ ቡና - 9:00
ወልቂጤ ከተማ ከ መቐለ 70 አ. - 9:00


የውጭ ሀገር ስፖርታዊ ዜናዎች
ማንቸስተር ዩናይትድ ሜክሲኳዊውን የዎልቭስ አጥቂ ራውል ሂሜኔስ  ወይም የሊዮኑን ፈረንሳዊውን አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ማስፈረም ይፈልጋል።ዴምቤሌን ጁቬንትስ እና ቼልሲም ይፈልጉታል።
(Sky Sports)





የቼልሲው አማካይ ንጎሎ ካንቴ ወደ ሪያል ማድሪድ መሄድ ይፈልጋል።ታታሪው ፈረንሳዊ አዲስ ፈተናን ፍለጋ ወደ ስፔን መጓዝን የሚሻ ሲሆን ሎስብላንኮዎቹም ለዝውውሩ £100ሚ. አሰናድቷል።ባየርን ሙኒክ እና ጁቬንትስም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(Sun)





ማንቸስተር ሲቲ የመሀል ተከላካይ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ለማስፈረም እየሰራ ነው።ውሃ ሰማያዊዎቹ የኤምሪክ ላፖርቴን መጎዳት ተከትሎ ፈርናንዲንሆን በመሀል ተከላካይነት ለመጠቀም ተገደው እንደነበር ይታወሳል።
(Times)





ቶተንሃም የሳውዝሀምተኑን አጥቂ ዳኒ ኢንግስ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሀሪ ኬን ለሶስት ወራት ከሜዳ ውጪ እንደሚሆን ይፋ መደረጉን ተከትሎ ስፐርስ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ለማስፈረም ወደ ገበያ ወጥታለች።
(Daily Star)





የአርትሮ ቪዳል ቆይታ በኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ቆይታ ላይ ይወሰናል።ቫልቬርዴ ከክለቡ የሚሰናበቱ ከሆነ ቪዳል ወደ ኢንተር ሚላን እንደሚጓዝ ይጠበቃል።
(Mundo Deportivo)





ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የስፖርቲንግ ሊዝበኑን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ አጥብቆ እንደሚፈልግ ተነግሯል።ፖርቱጋላዊው ኢንተርናሽናል ስሙ በስፋት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር መያያዝ ከጀመረ ሰነባብቷል።
(The Athletic)





ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ ጀርመናዊው አማካይ ለሮይ ሳኔ ቆይታ ተጠይቆ "ይሄ መጠየቅ ያለበት ለሳኔ ነው።እንዲሁም ለወኪሉ እና ለክለቡ ፥ እኔ እዚህ ላይ አልገባም" ብሏል። ሳኔ ስሙ በስፋት ከባየርን ሙኒክ ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።
(Goal)





ኦሊቪየ ዢሩ ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሷል።የዓለም ዋንጫን ከሀገሩ ጋር ያሳካው ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል በአንቶኒዮ ኮንቴ ቡድን ውስጥ ከሉካኩ ጋር እንደሚጣመር ይጠበቃል።
(Sky Sports)

የዕለተ አርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ቶተንሃም ከ ሳውዝሃምተን በነበረው ጨዋታ ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ሀሪ ኬን ለሶስት ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ይፋ ሆኗል።በዚህም ምክንያት ጆዜ ሞሪንሆ የእንግሊዛዊውን አጥቂ ቦታ ለመተካት አዲስ ተጨዋች ማስፈረም እንደሚጠበቅባቸው ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸው።
( Goal)





የቀድሞው የባርሴሎና ሌጀንድ ዣቪ ወደ ካምፕ ኑ የሚመለስበት ዕድል እየተፈጠረ ይመስላል።በኳታሩ ክለብ አል-አሳድ የሚገኘው ዣቪ ወደ ቀድሞው ክለቡ የሚመለሰው ቀውስ ላይ የሚገኙትን ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን በመተካት እንደሚሆን ይጠበቃል።ከባርሴሎና ባለ ስልጣኖች መሀከል የቀድሞው ተጨዋች ኤሪክ አቢዳል የሚመራው ልዑክ ዣቪን ለማነጋገር ወደ ኳታር ይጓዛልም ተብሏል።
(RAC1)





ማንቸስተር ዩናይትድ ኒማኒያ ማቲችን በተመለከተ የቀረቡለትን ሁለት የዝውውር ጥያቄዎች ውድቅ አድርጓል።በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት አስቸጋሪ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ሰርቢያዊ አማካይ በተለይ በአትሌቲኮ ማድሪድ እና ኢንተር ሚላን በጥብቅ ይፈለጋል።
(Daily Record)





ፍራንክ ላምፓርድ ክሪስቴንሰን ቼልሲን በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት እንደማይለቅ ተናግሯል።አንድሪያስ ክሪስቲየንሰን በኤሲ ሚላን ከሚፈለጉ ተጨዋቾች ዋነኛው ነው።
(Goal)





የቀድሞው የቶተንሃም ሌጀንድ ስሊቪ አለን የሀሪ ኬንን መጎዳት ተከትሎ ቦታውን ለመተካት ኤዲንሰን ካቫኒን ስፐርስ ማስፈረም አለበት ብሏል።በተጨማሪም ጋሬዝ ቤልን መመለስ ያስፈልጋል ሲል ተናግሯል።
(Goal)





ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የስፖርቲንግ ሊዝበኑን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ አጥብቆ እንደሚፈልግ ተነግሯል።ፖርቱጋላዊው ኢንተርናሽናል ስሙ በስፋት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር መያያዝ ከጀመረ ሰነባብቷል።
(The Athletic)





ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ ጀርመናዊው አማካይ ለሮይ ሳኔ ቆይታ ተጠይቆ "ይሄ መጠየቅ ያለበት ለሳኔ ነው።እንዲሁም ለወኪሉ እና ለክለቡ ፥ እኔ እዚህ ላይ አልገባም" ብሏል። ሳኔ ስሙ በስፋት ከባየርን ሙኒክ ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።
(Goal)





ኦሊቪየ ዢሩ ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሷል።የዓለም ዋንጫን ከሀገሩ ጋር ያሳካው ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል በአንቶኒዮ ኮንቴ ቡድን ውስጥ ከሉካኩ ጋር እንደሚጣመር ይጠበቃል።
(Sky Sports)

Thursday, January 9, 2020

የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ክርስቲያን ኤሪክሰን ከኢንተር ሚላን ጋር አነጋገር ወደ ጣሊያን ሊጓዝ መሆኑን የጋርዲያኑ ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።ኤሪክሰን በቶተንሃም ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ ይጠናቀቃል።ኢንተር ሚላን የቼልሲውን ፈረንሳዊ አጥቂ ኦሊቪየ ዢሩም ለማዘዋወር ጥረቱን ቀጥሏል።
(Guardian)





ባርሴሎና ምንም እንኳን ትናንት በስፔን ሱፐር ካፕ የ3ለ2 ሽንፈት ቢያጋጥመውም ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን የማባረር ዕቅድ የለውም።ቫልቬርዴ ከጨዋታው በኋላ ስራውን ሊያጣ እንደሚችል ስጋት ካለው ተጠይቆ "ይሄ ምንጊዜም ያለ ነው" ሲል መልሷል።
(Cope)





በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ የሚገኘው የሊዮኑ አጥቂ ሞሳ ዴምቤሌ በጆዜ ሞሪንሆው ቶተንሃምም ተፈልጓል።ሀሪ ኬንን በጉዳት ያጣው የ23 አመቱን አጥቂ አጥብቆ ይሻዋል።
(Goal)




የዌስት ሀሙ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ቤልጄሚያዊውን የ32 አማካይ ማርዋን ፌይላኒ ከቻይናው ክለብ ሻልዶንግ ሊዎንግ ማዘዋወር ይፈልጋል።ሞይስ ከዚህ በፊት በሁለት ክለቦች ከፌይላኒ ጋር አብሮ ሰርቷል።
(Sky Sports)





ቼልሲ እና ቶተንሃም የ24 አመቱን ፈረንሳዊ የክንፍ አጥቂ ቶማስ ሌማር እስከ አመቱ መጨረሻ በውሰት ለመውሰድ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ሌማር በአትሌቲኮ ማድሪድ ከባድ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(Telegraph)






ሪያል ማድሪድ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ዌልሳዊውን የክንፍ አጥቂ ጋሬዝ ቤል የመሸጥ ፍላጎት ያለው ሲሆን ወኪሉ ግን ዝውውሩ በአመቱ መጨረሻ እንዲፈጸም ነው የሚፈልገው።
(Telegraph)





ቶተንሃም ፖርቱጋላዊውን የ26 አመት የባርሴሎና የቀኝ መስመር ተከላካይ ኔልሰን ሴሜዶ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።
(Mirror)





የቀድሞው የአርሰናል አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ኤቨርተን ካርሎ አንቾሎቲን ከመሾሙ በፊት ለሶስት ሰዓት ያክል አነጋግሮት ባለመስማማት እንዳልተሳካ ተናግሯል።
(Mail)






ሌስተር ሲቲ ቱርካዊውን የጁቬንትስ ተከላካይ ሜርህ ዴሚራል ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ነው።ሌስተር ከዚህ በፊት ተጨዋቹን ሁለት ጊዜ ለማዘዋወር ሞክሮ ውድቅ የተደረገበት ሲሆን ማንቸስተር ሲቲም የተጨዋቹ ፈላጊ ነው።
(Mirror)





በዝውውሩ መስኮቱ ከሴሪ ኤ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሊመጡ የሚችሉ ተጨዋቾች

                   አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ከተከፈተ ቀናት ባለፉት የዝውውር መስኮት ከጣሊያን ሴሪ ኤ ወደ እንግሊዝ  ፕሪሚየር ሊግ ሊመጡ የሚችሉ ስምንት ተጨዋቾች ዝርዝር



ላውታሮ ማርቲኔዝ (ኢንተር ሚላን)
የመሸጫ ዋጋ  - €100ሚ.
ሊዘዋወር የሚችለበት ክለብ - ማንቸስተር ሲቲ



በዘንድሮው አመት ድንቅ ጊዜን በሳንሲሮ እያሳለፈ የሚገኘው አርጀንቲናዊ አጥቂ በተለይ ከሮሜሮ ሉካኩ ጋር ጥሩ ጥምረትን ፈጥሯል።በሁሉም የውድድር አይነቶችም 13 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን €100ሚ. ደግሞ የመሸጫ ዋጋው ነው።






ኤምሪ ቻን (ጁቬንትስ)
የመሸጫ ዋጋ - €30ሚ.
ሊዘዋወርበት የሚችለው ክለብ - ማንቸስተር ዩናይትድ ፣ኤቨርተን ወይም ኒውካስትል

ቻን በጣሊያን ከባድ እያሳለፈ ሲሆን ማውሩዚዮ ሳሪም በሻምፒዮንስ ሊግ ስኳዳቸው ውስጥ አላካተቱትም።






ሮቢን ጎሴንስ (አታላንታ)

የመሸጫ ዋጋ - £20ሚ.
ሊዘዋወር የሚችልበት ክለብ - ቶተንሃም ወይም ክሪስታል ፓላስ





ድረስ መርቲንስ (ናፖሊ)

የመሸጫ ዋጋ - €10ሚ.
ሊዘዋወር የሚችልበት ክለብ - ኤቨርተን





ሎሬንዞ ኢንሴኚ (ናፖሊ)

የመሸጫ ዋጋ - €50ሚ.
ሊዘዋወር የሚችልበት ክለብ - ኤቨርተን





ጄሮሚ ቦጋ (ሳሱሎ)

የመሸጫ ዋጋ - €20ሚ.
ሊዘዋወር የሚችልበት ክለብ - አርሰናል ወይም ቼልሲ





ሴኮ ፎፎና (ኡዲሲዜ)

የመሸጫ ዋጋ - €20ሚ.
ሊዘዋወር የሚችልበት ክለብ - ኒውካስትል ፣ በርንመዝ ወይም ክሪስታል ፓላስ





ኒኮላ ሚሊንኮቪች (ፊዮረንቲና)


የመሸጫ ዋጋ - €35ሚ.
ሊዘዋወር የሚችልበት ክለብ - አርሰናል











Tuesday, January 7, 2020

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

               አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ትናንት ምሽት በካራባኦ ካፕ በተደረገው ማንቹኒያን ደርቢ ማንቸስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ማንቸስተር ዩናይትድን 3-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።





ትናንት ምሽት የካፍ የአመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጨዋች ሽልማት ሥነ-ስርዓት የተደረገ ሲሆን ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ሽልማቱን ተቀዳጅቷል።ማኔ በዓመቱ ከክለቡ ሊቨርፑል ጋር አስደናቂ ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን ሀገሩንም ለአፍሪካዋ ዋንጫ ፍጻሜ አብቅቶ ነበር።
(CAF)





ቼልሲ አይቮሪኮስታዊውን አጥቂ ዊልፍሬድ ዛሃ በተከፈተው የዝውውር መስኮት የማስፈረም ዕቅድ ቢኖረም ክሪስታላ ፓላስ የጠየቀውን £80ሚ. ግን ለመክፈል ፈቃደኛ አይደለም።
(Express)





ማንቸስተር ሲቲ የአጥቂ ስፍራ መስመሩን ይበልጥ ለማጠናከር ስፔናዊውን የዎልቭስ ተጨዋች አዳማ ትራዎሬ ማዘዋወርን ይሻል።ፔፕ ጋርዲዮላ ዘንድሮ ደካማ ጊዜን እያሳለፈ እንደሆነ ይታወቃል።
(Calcio Mercato, via Manchester Evening News)






የቺሊያዊው የባርሴሎና አማካይ አርቶሮ ቪዳል ወኪል በዚህ ሳምንት በጥር ወር የዝውውር መስኮት ስለመዘዋወር ጉዳይ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እንደሚመክር ይጠበቃል።ቪዳል ኢንተር ሚላንን ጨምሮ በሌሎች ክለቦችም ይፈለጋል።
(Corriere Della Sera, via Mirror)






በጉዳት ለአምስት ወራት ከሜዳ ርቆ የቆየው ጀርመናዊው የማንቸስተር ሲቲ አጥቂ ለሮይ ሳኔ ወደ ልምምድ ሜዳ ተመልሷል።ይህም ለፔፕ ጋርዲዮላ በጎ ዜና ነው ተብሏል።
(Manchester Evening News)






ስሙ በስፋት ከቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና ጋር ሲያያዝ የሰነበተው ብራዚላዊው የወቅቱ ውድ ተጨዋች ኔይማር በፓሪሰን ዤርመን ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ነው።
( Le Parisien)





የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ ኦሊቪየር ዢሩ በቼልሲ ደስተኛ እንዳልሆነ ጠቅሰው ከክለቡ መውጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።የ33 አመቱ አጥቂ ስሙ በስፋት ከኢንተር ሚላን ፣ አስቶን ቪላ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ጋር እየተያያዘ ሲሆን በ2020ው የአውሮፓ ዋንጫ ሀገሩን ለመወከል በቂ የመሰለፍ ዕድል ወደ ሚያገኝበት ክለብ መሄድ እንዳለበት ዴሾ ተናግሯል።
(Goal)





ምንም እንኳን የክርስቲያን ኤሪክሰን ስም በስፋት ከኢንተር ሚላን ጋር ቢያያዝም የጣሊያኑ ክለብ ፕሬዝደንት ጁሴፔ ማሮታ ክለባቸው ከዴንማርካዊው አማካይ ጋር ምንም አይነት ንግግር እንዳላደረገ፡ተናግረዋል።የኤሪክሰን ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን በተከፈተው የዝውውር መስኮት ስፐርስን እንደሚለቅ ይጠበቃል።
(Goal)

የዕለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                 አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)





ስሙ በስፋት ከቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና ጋር ሲያያዝ የሰነበተው ብራዚላዊው የወቅቱ ውድ ተጨዋች ኔይማር በፓሪሰን ዤርመን ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ነው።
( Le Parisien)





የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ ኦሊቪየር ዢሩ በቼልሲ ደስተኛ እንዳልሆነ ጠቅሰው ከክለቡ መውጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።የ33 አመቱ አጥቂ ስሙ በስፋት ከኢንተር ሚላን ፣ አስቶን ቪላ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ጋር እየተያያዘ ሲሆን በ2020ው የአውሮፓ ዋንጫ ሀገሩን ለመወከል በቂ የመሰለፍ ዕድል ወደ ሚያገኝበት ክለብ መሄድ እንዳለበት ዴሾ ተናግሯል።
(Goal)





ምንም እንኳን የክርስቲያን ኤሪክሰን ስም በስፋት ከኢንተር ሚላን ጋር ቢያያዝም የጣሊያኑ ክለብ ፕሬዝደንት ጁሴፔ ማሮታ ክለባቸው ከዴንማርካዊው አማካይ ጋር ምንም አይነት ንግግር እንዳላደረገ፡ተናግረዋል።የኤሪክሰን ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን በተከፈተው የዝውውር መስኮት ስፐርስን እንደሚለቅ ይጠበቃል።
(Goal)







አርሰናል በተከፈተው የዝውውር መስኮት ተጨዋቾችን በቋሚነት ከማዘዋወር ይልቅ በውሰት መውሰድን እንደሚጠቀም ተዘግቧል።የዚህ ምክንያት ደግሞ ባልተለመደ መልኩ ባሳለፍነው የክረምት የዝውውር መስኮት £130ሚ. ስላወጣ በዚህ የዝውውር መስኮት ወጪ ለመቆጠብ ነው።
(Goal)





የቀድሞው የቶተንሃም ተጨዋች ዳረን ቤንስ ስለ ስፐርስ ወቅታዊ ሁኔታ ተጠይቆ የሀሪ ኬንን መጎዳት ተከትሎ ጆዜ ሞሪንሆ አዲስ የአጥቂ ስፍራ መስመር ተጨዋች ማስፈረም እንዳለባቸው ፥ ያ ተጨዋችም የሳውዝሀምተኑ ዳኒ ኢንግስ መሆን እንዳለበት መክሯል።
(Goal)




ጁቬንትስ የማንቸስተር ዩናይትዱን ታዳጊ ታሂት ቾንግ ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ነው።ሆላንዳዊው ዊንገር በቀያይ ሰይጣኖቹ ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ የሚያልቅ ሲሆን አሮጊቷ ካዘዋወረችው ሳምንታዊ £35,000 አሰናድታለች።
(The Sun)





ማንቸስተር ሲቲ ሴኔጋላዊውን የናፖሊ ተከላካይ ለማዘዋወር £100ሚ. አሰናድቷል።ከፍተኛ የመሀል ተከላካይ ችግር ያለበት ሲቲ ድንቁን ሴኔጋላዊ ለማዘዋወር በጥብቅ ይሻል።
(90min)





የክሪስታል ፓላሱ የክንፍ አጥቂ ዊልፍሬድ ዛሃ ወደ ባየርን ሙኒክ ሊጓዝ የሚችልበት ዕድል አለ።አይቮሪኮስታዊው አጥቂ በሌሎች በርካታ ክለቦችም ይፈለጋል።
(Sky Deutschland)







Monday, January 6, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ትናንት በፈረንጆቹ አዲስ አመት የጣሊያን ሴሪ ኤ ሲጀመር ጁቬንትስ ካጊሊያሪን አስተናግዶ 4ለ0 ያሸነፈ ሲሆን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀትሪክ ሰርቷል።ኢንተር ሚላንም ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ናፖሊን 3ለ1 አሸንፏል።ጁቬንትስ እና ኢንተር ሚላን በእኩል 45ነጥብ በግብ ልዩነት ተለያይተው ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ።






ቶተንሃም ፈረንሳዊውን የአትሌቲኮ ማድሪድ አማካይ ቶማስ ሌማር በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።ስፐርስ በውሉ ላይ ከፈለገች በ£60ሚ. ማስፈረም የምትችልበትን መንገድም እንዲሰፍር ትፈልጋለች።
(Independent)





ማንቸስተር ሲቲ ስሎቫኪያዊውን የኢንተር ሚላን ተከላካይ ሚላን ስክሪኒያር ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።የስፔኖቹ ሐያላን ክለቦች ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(Mirror)





ኢንተር ሚላን ዴንማርካዊውን የቶተንሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ለማዘዋወር £20ሚ. አቅርቧል።አንቶኒዮ ኮንቴ ግን የሚሳካለት ከሆነ በዋናነት የሚፈልገው የባርሴሎናውን ቺሊያዊ አማካይ አርቱሮ ቪዳል ነው።
(Mirror)





ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የሌስተር ሲቲ አማካይ ጄምስ ማዲሰን የማዘዋወር ፍላጎት ቢኖረም በተከፈተው የዝውውር መስኮት ግን ተጨዋቹን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ማምጣት አዳጋች መሆኑን ይረዳል።
(Sky Sports)




የሪያል ማድሪዱ ክሮኤሽያዊ አማካይ ሉካ ሞድሪች ወደ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ዲሲ ዩናይትድ ለመዘዋወር እየተነጋገረ ነው።ዲሲ ዩናይትድ የቀድሞው የዌይን ሩኒ ክለብ ነው።
(The Athletic - subscription required)





ማንቸስተር ዩናይትድ ሲን ሎንግ ስታፍን በጥብቅ እየፈለገ መሆኑን ተከትሎ ስለ ተጨዋቹ የተጠየቁት የኒውካስትል ዩናይትዱ አሰልጣኝ ስቲቭ ብሩስ ክለባቸው ተስፈኛ ታዳጊ  ተጨዋቾችን ወደ ገበያ እንደማያወጣ ገልጸዋል።
(Manchester Evening News)





ምንም እንኳን ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን ፍላጎት ቢኖርም ኤምሪ ቻንን እና አድሪያን ራቢዮን በተከፈተው የዝውውር መስኮት እንደማይሸጡ የጁቬንትሱ ዳይሬክተር ፋቢዮ ፓራቲቺ ተናግረዋል።
(Mail)





ኤቨርተን ፣ ኢንተር ሚላን ፣ ብራይተን እና ናፖሊ ጄሮሚ ቦጋን ከሳሱሎ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ቼልሲ ተጨዋቹን ለሳሱሎ ሲሸጥ በፈለገበት ጊዜ መመለስ እንደሚችል ውል የነበረው ቢሆንም ሰማያዊዎቹ ግን ተጨዋቹን አይፈልጉትም።
(Goal)





ዌስት ሀም የስቶክ ሲቲውን አማካይ አለን ለማዘዋወር ያደረገው የመጀመሪያ ሙከራ አልተሳካለትም።አዲሱ የመዶሻዎቹ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ዌልሳዊውን ኢንተርናሽናል ይፈልጉታል።
(Football Insider)





ቶተንሃም ቶማስ ሌማርን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ከተቻለ በቋሚነት ካልሆነ በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።ፈረንሳዊው የቀድሞው የናፖሊ ተጨዋች በዋንዳ ሜትራ ፖሊታኖ ስኬታማ ያልሆነ ጊዜን እያሳለፈ ሲሆን አርሰናልም ይፈልገዋል።
(Independent)


የዕለተ ሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                    አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ማንቸስተር ዩናይትድ የባርሴሎናውን አማካይ አርቶሮ ቪዳል የማዘዋወር ፍላጎት አለው።የ32 አመቱ ቺሊያዊ ከካታላኑ ክለብ በዚህ አመት እንደሚለቅ የሚጠበቅ ሲሆን በኢንተር ሚላንም በጥብቅ ይፈለጋል።
(DirectTV Chile)





ኤቨርተን ፣ ኢንተር ሚላን ፣ ብራይተን እና ናፖሊ ጄሮሚ ቦጋን ከሳሱሎ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ቼልሲ ተጨዋቹን ለሳሱሎ ሲሸጥ በፈለገበት ጊዜ መመለስ እንደሚችል ውል የነበረው ቢሆንም ሰማያዊዎቹ ግን ተጨዋቹን አይፈልጉትም።
(Goal)





ዌስት ሀም የስቶክ ሲቲውን አማካይ አለን ለማዘዋወር ያደረገው የመጀመሪያ ሙከራ አልተሳካለትም።አዲሱ የመዶሻዎቹ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ዌልሳዊውን ኢንተርናሽናል ይፈልጉታል።
(Football Insider)





ቶተንሃም ቶማስ ሌማርን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ከተቻለ በቋሚነት ካልሆነ በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።ፈረንሳዊው የቀድሞው የናፖሊ ተጨዋች በዋንዳ ሜትራ ፖሊታኖ ስኬታማ ያልሆነ ጊዜን እያሳለፈ ሲሆን አርሰናልም ይፈልገዋል።
(Independent)






ጋሬዝ ቤል ወደ ሜጀር ሊግ ሶከር ሊጓዝ እንደሆነ ተነግሯል።ፈላጊው ደግሞ በዴቪድ ቤካም ባለቤትነት የሚተዳደረው ኢንተር ሚያሚ ነው ተብሏል።
(El Desmarque)





የጁቬንትሱ ዳይሬክተር ፋቢዮ ፓራቲቺ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ኤምሪ ቻን እና አድናን ራቢዮ ከክለቡ ሊለቁ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል።
(Goal)





የፓሪሰን ዤርመኑ አጥቂ ኤድንሰን ካቫኒ ወደ ስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ሊዘዋወር  እንደሆነ ተነግሯል።ኡራጋዊያዊው በተለይ ከማውሮ ኢካርዲ መምጣት በኋላ የቋሚ ተሰላፊነት ዕድልን ያጣ ሲሆን በክለቡ ያለው ኮንትራትም በአመቱ መጨረሻ ያበቃል።
(L'Equipe)






ካሉም ቼምበርስ ጉዳት በማስተናገዱ ወደ መሰለፍ እንደሚመጣ ቢገመትም ሽኾድራን ሙስጣፊ ግን አሁንም አርሰናልን መልቀቅ ይፈልጋል።ጀርመናዊው ተከላካይ በዚህ አመት ብዙ ትችትን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።
(The Mirror)

Sunday, January 5, 2020

የዕለተ ሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ማንቸስተር ዩናይትድ ፖርቱጋላዊውን የስፖርቲንግ ሊዝበን  የጨዋታ ቀማሪ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለማዘዋወር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።ኦሊ ጉናር ሶልሻየር ቡድኑ ውስጥ ፈጣሪ አማካዮችን ማከል ይፈልጋል።
(Goal.com)





አርሰናል ጀርመናዊው የ31 አመት የባየርን ሙኒክ ተከላካይ ጄሮሚ ቦዋቲንግ ለማዘዋወር ከባቫሪያው ክለብ ጋር ንግግር ጀምሯል።
(Footmercato - in French)





ባርሴሎና ስፔናዊውን የዳይናሞ ዛግሬቭ አጥቂ ዳኒ ኦልሞ ለማዘዋወር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።የ21 አመቱን ተስፈኛ አጥቂ የእንግሊዞቹ ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድም ይፈልጉታል።
(Goal.com)





ከማንቸስተር ዩናይትድ ሊወጣ እንደሚችል የሚነገርለት እንግሊዛዊው ሄሴ ሊንጋርድ አወዛጋቢውን እና ታዋቂውን ወኪል ሚኖ ራዮላ ወኪሉ ሊያደርገው ንግግር ላይ ናቸው።
(Mail)





የአያክሱ ድንቅ ሞሮካዊያዊ አማካይ ሀኪም ዚያች በዚህ የዝውውር መስኮት ከክለቡ እንደሚለቅ ማረጋገጫ ተስጥቶታል።የ26 አመቱን አማካይ ለማዘዋወር ሁለቱ የሰሜን ለንደን ክለቦች አርሰናል እና ቶተንሃም የሚፎካከሩ ይሆናል።
(Football.London)





የአጥቂ መስመር ስፍራውን ለማጠናከር የሚፈልገው ፍራንክ ላምፓርድ አይኑን ወደ ጣሊያን በማማተር ብራዚላዊውን የኢንተር ሚላን አጥቂ ጋብሬል ባርቦሳ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለማምጣት እየሰራ ነው።ባርባሶ በዚህ አመት በውሰት ለሀገሩ ክለብ ፍላሚንጎ ተሰጥቶ ድንቅ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(Express)





ፈረንሳዊው አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ በኢንስታግራም ገጹ የሊቨርፑልን ማሊያ ለብሶ የለቀቀውን ፎቶ ተከትሎ ስሙ በስፋት ከቀያዮቹ ጋር ተያይዟል።የሊቨርፑል ደጋፊዎችም በማህበራዊ ድህረ ገጽ ዝውውሩ ቢሳካ እንደሚደሰቱ በመግለጽ ላይ ናቸው።
 (Daily Express)





ዎንቼክ ሼዝኒ በጁቬንትስ አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ነው።ፖላንዳዊው ግብ ጠባቂ የ18 ወራት ኮንትራት በቱሪን ያለው ሲሆን አሮጊቷ እስከ 2024 የሚያቆየውን ኮንትራት ነው ያቀረበችለት።
(Calciomercato)



ፍራንክ ላምፓርድ የአጥቂ ስፍራ መስመሩን ለማጠናከር ሶስት ተጨዋቾች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው።እነሱም የሊሉ ኦስማን ዴምቤሌ ፣ የቦሩሲያ ዶርትሙንዱ ጄደን ሳንቾ እና የክሪስታል ፓላሱ ዊልፍሬድ ዛሃ ናቸው።
(Footmercato)

የዕለተ እሁድ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

             አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)




ኦሊ ጉናር ሶልሻየር ፖል ፖግባ በጥር ወር የዝውውር መስኮት እንደማይሸጥ ተናገረ።ፈረንሳዊው አማካይ በተለይ ከሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ ጋር ስሙ በስፋት እየተያያዘ ቢገኝም የቀያይ ሰይጣኖቹ አለቃ ሶልሻየር ግን ተጨዋቹ በኦልድ ትራፎርድ እንደሚቆይ ተናግሯል።
(Goal)





አርሰናል የአያክሱን  አማካይ ሀኪም ሲያች ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሞሮኮዋዊው አማካይ የሽያጭ ገንዘቡ £43ሚ. እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን መድፈኞቹም ይህንን ገንዘብ ለመክፈል ፍቃደኝነቱን አሳይተዋል።ዚያች በዘንድሮው አመት በኤርዴቪዜው ለአያክስ 6ግብ ያስቆጠረ ሲሆን 12 አሲስትም አድርጓል።
(Calcio Mercato)





የአስቶን ቪላው አሰልጣኝ ዲን ስሚዝ  ክለባቸው ኦሊቪየር ዢሩን ማዘዋወር ዋነኛው ዕቅዱ መሆኑን ይፋ አድርጓል።ፈረንሳዊው አጥቂ በዘንድሮው ሲዝን በስታንፎርድ ብሪጅ በቂ የመሰለፍ ዕድል ያልተሰጠው ሲሆን በተከፈተው የዝውውር መስኮትም የመልቀቅ ዕድሉ ሰፊ ይመስላል።
(The Athletic)





ቶተንሃም የኖርዊች ሲቲውን ተከላካይ ማክስ አሮንስ ለማዘዋወር £15ሚ. አሰናድቷል።ጆዜ ሞሪንሆ የተከላካይ መስመራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ከአሮንስ በተጨማሪ ሌሎች ተጨዋቾችም የዳኒ ሌቪ አስተዳደር እንዲያመጣለቸው ይሻሉ።
(The Sun)





ማንቸስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ራውል ሂሜኔስን እና ሩበን ኔቬስን ለማዘዋወር በመስራት ላይ ይገኛል።ቀያይ ሰይጣኖቹ በተጨዋቾቹ ዙሪያ ከክለባቸው ጋር መነጋገር የጀመሩ ሲሆን የአቋሚ መዋዠቅ በየጊዜው የሚታይበትን ቡድኑን ለማጠናከር ሶልሻየር አዳዲስ ተጨዋቾችን ይፈልጋል።
(Goal)




አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በሪያል ማድሪድ አብረውት የሰሩትን ኮሎምቢያዊውን የጨዋታ ቀማሪ ሀሜስ ሮድሪጌዝ በውሰት ወደ ጉዲሰን ፓርክ ለማዘዋወር እየሰሩ ነው።
(Sunday Mirror)





ዌስት ሀም በቀጣዩ ሳምንት ከቤኔፊካ ጋር ይወያያል።ውይይቱ የሚያተኩረው ፖርቱጋላዊውን አማካይ ጌዲሰን ፈርናንዴዝ በውሰት ስለመውሰድ ላይ ይሆናል።
(Record, via Star on Sunday)





ቶተንሃም በውሰት ከሪያል ቤቲስ አምጥቶት የነበረውን አርጀንቲናዊውን አማካይ ጂዮቫኒ ሌ ሶልሶ በቋሚነት ለማዘዋወር ለስፔኑ ክለቡ £27ሚ. አቅርቧል።ጆዜ ሞሪንሆ አማካዩን በጥብቅ ይፈልጉታል።
(Sun)





Saturday, January 4, 2020

የዕለተ እሁድ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                  አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የሌስተር ሲቲ አማካይ ጄምስ ማዲሰን ለማዘዋወር ለቀበሮዎቹ £45ሚ. እና ጄሴ ሊንጋርድን አቅርቧል።
(Sunday Mirror)






ዌስት ሃም ሴኔጋላዊውን የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።የ28 አመቱ ተከላካይ በማንቸስተር ሲቲም ይፈለጋል።
(Sunday Express)




ማንቸስትር ዩናይትድ ለኢንተር ሚላኑ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ እንደሚፈልጉት እና በምትኩ ደግሞ ፈረንሳዊውን አማካይ ፖል ፖግባ ወደ ሳንሲሮ መሰኘት እንደሚሹ ነግረውታል።
(Sunday Mirror)





ጁቬንትስ ከብራዚላዊው የቼልሲ የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ወኪሎች ግራ መነጋገር መጀመሩን ከወደ ጣሊያን ያሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
(Calciomercato)





አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በሪያል ማድሪድ አብረውት የሰሩትን ኮሎምቢያዊውን የጨዋታ ቀማሪ ሀሜስ ሮድሪጌዝ በውሰት ወደ ጉዲሰን ፓርክ ለማዘዋወር እየሰሩ ነው።
(Sunday Mirror)





ዌስት ሀም በቀጣዩ ሳምንት ከቤኔፊካ ጋር ይወያያል።ውይይቱ የሚያተኩረው ፖርቱጋላዊውን አማካይ ጌዲሰን ፈርናንዴዝ በውሰት ስለመውሰድ ላይ ይሆናል።
(Record, via Star on Sunday)





ቶተንሃም በውሰት ከሪያል ቤቲስ አምጥቶት የነበረውን አርጀንቲናዊውን አማካይ ጂዮቫኒ ሌ ሶልሶ በቋሚነት ለማዘዋወር ለስፔኑ ክለቡ £27ሚ. አቅርቧል።ጆዜ ሞሪንሆ አማካዩን በጥብቅ ይፈልጉታል።
(Sun)





ክሪስታል ፓላስ ቱርካዊውን የኤቨርተን አጥቂ ሴንክ ቶሱን በውሰት ለማዘዋወር ለመርሲሳይዱ ክለብ ጥያቄ አቅርቧል።
(Mail on Sunday)





የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሞኒ በአርሰናል እና ቶተንሃም እየተፈለገ ያለውን ፈረንሳዊውን አማካይ ቶማስ ሌማር ማጣት አይፈልጉም።
(Mirror)





ቼልሲ ፣ ክሪስታል ፓላስ እና ብራይተን ሩሲያዊውን የሲኤስኬ ሞስኮ አጥቂ ፌዶር ቻሎቭ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Sky Sports)



የዕለተ ቅዳሜ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                     አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)




ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን አማካይ ፖል ፖግባ ለማዘዋወር ከገንዘብ በተጨማሪ ለማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውሩ አካል ሆኖ ጀርመናዊውን አማካይ ቶኒ ክሩስ የመስጠት ዕቅድ አለው።
(Sun)





በሌላ ዜና ደግሞ ጁቬንትስም የቀድሞው ተጨዋቹን ፖል ፖግባን ለማዘዋወር አድናን ራቢዮ ላይ ገንዘብ ጨምሮ ለማንቸስተር ዩናይትድ ጥያቄ አቅርቧል።
(Sun)





አርሰናል የኖርዊች ሲቲውን እንግሊዛዊ ተከላካይ ማክስ አሮንስ ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ሲሆን የከተማ ተቀናቃኙ ቶተንሃምም የ19 አመቱ ተከላካይ ፈላጊ ነው።ስፐርስ ተጨዋቹን የማግኘት ዕድሏ ሰፉ፡ነውም ተብሏል።
(Daily Mail)





አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ 2015 ላይ ሊቨርፑል ብሬንደን ሮጀርስን ካሰናበተ በኋላ ሊሾማቸው ጥያቄ አቅርቦላቸው ባለመስማማት እንዳልተሳካ ተናገሩ።ሊቨርፑል እሳቸውን ካናገረ እና ካልተሳካ በኋላ ነበር የርገን ክሎፕን የሾመው።
(Telegraph)





ማንቸስተር ዩናይትድ ኖርዌያዊውን አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ለማዘዋወር ከፍተኛ ፍላጎት አሳድሮ የነበር ቢሆንም ወደ ቦሩሲያ፡ዶርትመንድ መዘዋወሩ ይታወሳል።በዚህም የተጨዋቹን ወኪል ሚኖ ራዮላ ተቀይመውታል ተብሏል።ራዮላ የፖል ፖግባም ወኪል እንደሆነ ይታወቃል።
(Daily Mail)






ዴንማርካዊው የቶተንሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ወደ ጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።
(Ekstra Bladet, in Danish)




ቦሩሲያ ዶርትመንድ በቼልሲ የሚፈለገውን እንግሊዛዊውን አጥቂ ጄደን ሳንቾ ቢያንስ እስከ አመቱ መጨረሻ በክለቡ የማቆየት እቅድ እንዳለው ታውቋል።በዚህም ቼልሲ ሙሉ ለሙሉ ትኩረቱን ወደ ራ.ቢ ሌብዚኩ ጀርመናዊ አጥቂ ቲሞ ዋርነር አዙሯል።
(Goal.com)





የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሞኒ በአርሰናል እና ቶተንሃም እየተፈለገ ያለውን ፈረንሳዊውን አማካይ ቶማስ ሌማር ማጣት አይፈልጉም።
(Mirror)





ቼልሲ ፣ ክሪስታል ፓላስ እና ብራይተን ሩሲያዊውን የሲኤስኬ ሞስኮ አጥቂ ፌዶር ቻሎቭ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Sky Sports)

Thursday, January 2, 2020

የዕለተ ሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

               አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)




ኔይማር እስከ አመቱ መጨረሻ በፓሪሰን ዤርመን ሊቆይ ይችላል።ስሙ ከቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና ጋር በስፋት የተያያዘው ኔይማር ከምባፔ ጋር ደስተኛ ሲሆን ከክለቡ ጋርም ሻምፒዮንስ ሊግን ማሳካት ይሻል።
(L'Equipe)





ቼልሲ ፈረንሳዊውን አጥቂ ሞሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር £40ሚ. አቅርቦ ክለቡ ሊዮን ውድቅ አድርጎበታል።ፍራንክ ላምፓርድ ተጨዋቹ ስታንፎርድ ብሪጅ እንዲከትም አጥብቆ ይሻል።
(FootMercato)






ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ አርሰናልን እንደማይለቅ ተናገረ።በትናንትናው ዕለተ በተከፈተው የዝውውር መስኮት መድፈኞቹን እንደሚለቅ ሲነገር ቢቆይም "100% በአርሰናል እቆያለሁ" ሲል ተናግሯል።ይህም ከአዲሱ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በጎ ዜና ነው ተብሏል።
(Goal)


የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የገና ሰሞን ጨዋታ ዛሬም ሲቀጥል ሊጉን በሰፊ ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው  ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሼፍልድ ዩናይትድን ያስተናግዳል።በዘንድሮው አመት ድንቅ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው አዲሱ አዳጊ ክለብ ሼፍልድ ቀያዮቹን እንደሚፈትን ይጠበቃል።





አስቶን ቪላ ሚቺ ባትሹዋይን ከቼልሲ በውሰት ለመውሰድ እየሰራ ነው።ቤልጄሚያዊው አጥቂ በፍራንክ ላምፓርድ ቡድን ውስጥ በቋሚነት የመሰለፍ ዕድልን እምብዛም ማግኘት አልቻለም።
(FootMercato)





አርሰናል የአጥቂ ስፍራ መስመሩን ለማጠናቀር አይኑን ወደ ስፔን በመጣል የአትሌቲኮ ማድሪዱን አጥቂ ቶማስ ሌማር ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ከሞናኮ ወደ አትኬቲኮ በውድ ዋጋ ከተዘዋወረ አንስቶ አመርቂ እንቅስቃሴ ያላደረገው ሌማር ወደ ሰሜን ለንደኑ ክለብ የመጓዝ ዕድሉ ሰፊ ይመስላል።
(Marca)





አንጋፋው አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ዛሬ በይፋ ኤሲ ሚላንን ተቀላቅሏል።የቀድሞው የአያክስ ፣ ባርሴሎና ፣ኢንተርሚላን ፣ኤሲ ሚላን ፣  ጁቬንትስ እና ማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ አሁን 38ተኛ አመቱ ላይ ነው የሚገኘው።
(Goal)





የባርሴሎናው የቀኝ መስመር ተከላካይ ኔልሰን ሴሜዶ በዝውውር መስኮቱ ብሉግራናዎቹን እንደሚለቅ ይጠበቃል።ፖርቱጋላዊው ኢንተርናሽናል በዘንድሮው አመት በቋሚነት የመሰለፍ ዕድልን በሰርጂ ሮቤርቶ ተነጥቋል።
(Sport)





ፔፕ ጋርዲዮላ በአመቱ መጨረሻ ማንቸስተር ሲቲን ሊለቅ እንደሚችል የቀድሞው የክለቡ አማካይ ሚኬል ብራውን ተናግሯል።በዘንድሮው አመት በኤቲሀድ ደካማ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ፔፕ እስከ 2021 የሚያቆይ ኮንትራት በውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት አለው።
(Goal)





Wednesday, January 1, 2020

የዕለተ ሐሙስ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ትናንት ምሽት ሲጠበቅ በነበረው የአርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታ አርሰናል 2-0 አሸንፏል።ሜሱት ኦዚል ድንቅ እንቅስቃሴ ባደረገበት ጨዋታ ፔፔ እና ሶቅራጠስ ለመድፈኞቹ ግቦቹን ያስቆጠሩ ሲሆን አርቴታ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ተቀዳጅቷል።





ናፖሊ እና አያክስ ቤልጄሚያዊውን የቶተንሃም ተከላካይ ያን ቬርቶገን ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የ32 አመቱ ተከላካይ በስፐርስ ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን ከተከፈተው የዝውውር መስኮት ስፐርስ ካለሸጠው ክረምት ላይ ወደ ፈለገበት ክለብ በነጻ መሄድ ይችላል።
(Telegraph)





ሪያል ማድሪድ ከሴኔጋላዊው የ27 አመት አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ወኪሎች ጋር መነጋገሩ ተገልጿል።ሎስብላንኮዎቹ የሊቨርፑሉን ድንቅ የክንፍ አጥቂ በጥብቅ ይሹታል።
(Le10Sport)






ስዊዘርላንዳዊው አማካይ ግራኒት ዣካ ወደ ሀርታ በርሊን በውሰት ከመጓዙ በፊት ከአዲሱ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ጋር በክለቡ ስለሚኖረው ሚና መነጋገር ይፈልጋል።
(Independent)





የቼልሲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ክለቡ ኮዲቫራዊውን የክሪስታል ፓላስ የክንፍ አጥቂ ዊልፍሬድ ዛሃ ለማዘዋወር ፍላጎት እንደሌለው ተናግሯል።
(Star)





የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እንግሊዛዊው አማካይ አዳም ላላና በአመቱ መጨረሻ ውሉ ሲጠናቀቅ ከክለቡ ሊሰናበት እንደሚችል ተናግረዋል።በአንድ ወቅት ብዙዎች ሲያሞግሱት የነበረው ላላና በተለይ ጉዳት የእግር ኳስ ህይወቱ ላይ ጥቁር ጥላ ሆኖበታል።
(Mirror)




ኤቨርተን ሞይስ ኪንን እንደሚፈልገው ነገር ግን ጁቬንትስ ተጨዋቹን በቋሚነት የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው የጣሊያናዊው አጥቂ ወኪል፡ተናግሯል።
(La Repubblica via Star)





ፖርቱጋላዊው የስፖርቲንግ ሊዝበን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ወደ ቶተንሃም ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሶ እንደነበር ተናግሯል።የ25 አመቱ አማካይ በአሁኑ ሰዓት በተለይ በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ይፈለጋል።
(Express)






ማርሴ እና አስቶን ቪላ በአሁኑ ሰዓት በቱርክ የሚገኘውን የቀድሞውን የቼልሲ እና ሊቨርፑል አጥቂ ዳኔል ስተሪጅ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀመረዋል።
(Mail)

የዕለተ ረቡዕ ምሽት አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች

አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሀና ልጅ)



ሪያል ማድሪድ በአዲሱ አመት ካለው ዕቅድ አንዱ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ማስፈረም ነው።ዋነኛው ውጥኑ ደግሞ ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ሲሆን ከተጨዋቹ ወኪሎች ጋርም መነጋገር ጀምሯል።
(Le10Sport)




የአታላንታው አማካይ ዲያን ኩሉሴቭስኪ ጁቬንትስን ለመቀላቀል በዚህ ሳምንት የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።ስዊድናዊው የ19 አመት አማካይ ከዚህ በፊት ስሙ በስፋት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ ቢሰናበትም በስተመጨረሻ ማረፊያው ቱሪን ይሆናል።ዲያን ያሳለፍነውን አመት በውሰት ፓርማ ነው የነበረው።
(Calciomercato)





ኢንተር ሚላን በቼልሲ የቋሚ ተሰላፊነት ዕድል የተነፈገውን ፈረንሳዊውን አጥቂ ኦሊቪየ ዢሩ በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚያስፈርም ይጠበቃል።በ2020 በሚደረገው የአውሮፓ ዋንጫ ሀገሩን መወከል የሚፈልገው ዢሩ በቂ የመሰለፍ ዕድልን በመሻት ወደ አንቶኒዮ ኮንቴው ክለብ የመሄድ ዕድሉ ሰፊ ነው።
(Calciomercato)





ሁለቱ የስፔን ሐያላን ክለቦች ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ የኤስፓኞሉን አማካይ ማርክ ሮካ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።በዘንድሮው አመት 18 የላሊጋ ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈውን አማካይ ባርሴሎና የማስፈረም ዕድሉ ግን ሰፊ ይመስላል።
(Don Balon)





ቼልሲ ለሲኤስኬ ሞስኮው አጥቂ ፊዮዶር ቻሎቭ £20ሚ. አቅርቧል።ከሩሲያ ክለቦች ጋር ጥሩ ግንኙነት ያለው የሚመስለው ቼልሲ በዘንድሮው አመት በራሺያ ሊግ አምስት ግብ ያስቆጠረውን የ21 አመት አጥቂ ለማስፈረም ጥረቱን አጠናክሯል።
(Express)





ማንቸስተር ዩናይትድ የሊሉን አማካይ ቡባከሪ ሳውማሬ ለማዘዋወር እየሞከረ ነው።ሊል ለተጨዋቹ ዝውውር £50ሚ. የሚፈልግ ሲሆን ቶተንሃም እና ዎልቭስም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(France Football News)





ሊቨርፑል የሲቪያውን ተከላካይ ዲዬጎ ካርሎስ ለማዘዋወር ይፈልጋል።ቀያዮቹ ብራዚላዊውን ተከላካይ የሚፈልጉት በአመቱ መጨረሻ ሲሆን የውል ማፍረሻውን £65ሚ. ለመክፈልም ፈቃደኛ ናቸው።በዘንድሮው አመት 18 ጊዜ በላሊጋው የተሰለፈው ካርሎስ ሪያል ማድሪድም ይፈልገዋል።
(Eldesmarque)





የፓሪሰን ዤርመኑ አማካይ ጁሊያን ድራክሰለር ዛሬ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ክለባቸውን ከሚለቁ ተጨዋቾች መሀከል እንደሚሆን ይጠበቃል።ሊቨርፑል ፣ አርሰናል እና ሲቪያ ደግሞ የክለቡ ዋነኛ ፈላጊዎች ናቸው።
(Sun)






ጆዜ ሞሪንሆ ክለባቸው ቶተንሃም በዝውውር መስኮት እምብዛም እንደማይሳተፍ ፍንጭ ሰጥተዋል።ክርስቲያን ኤሪክሰን ከቶተንሃም በዚህ የዝውውር መስኮት ከሚለቁ ተጨዋቾች ውስጥ እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Goal)

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...