Saturday, January 4, 2020

የዕለተ እሁድ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                  አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የሌስተር ሲቲ አማካይ ጄምስ ማዲሰን ለማዘዋወር ለቀበሮዎቹ £45ሚ. እና ጄሴ ሊንጋርድን አቅርቧል።
(Sunday Mirror)






ዌስት ሃም ሴኔጋላዊውን የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።የ28 አመቱ ተከላካይ በማንቸስተር ሲቲም ይፈለጋል።
(Sunday Express)




ማንቸስትር ዩናይትድ ለኢንተር ሚላኑ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ እንደሚፈልጉት እና በምትኩ ደግሞ ፈረንሳዊውን አማካይ ፖል ፖግባ ወደ ሳንሲሮ መሰኘት እንደሚሹ ነግረውታል።
(Sunday Mirror)





ጁቬንትስ ከብራዚላዊው የቼልሲ የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ወኪሎች ግራ መነጋገር መጀመሩን ከወደ ጣሊያን ያሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
(Calciomercato)





አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በሪያል ማድሪድ አብረውት የሰሩትን ኮሎምቢያዊውን የጨዋታ ቀማሪ ሀሜስ ሮድሪጌዝ በውሰት ወደ ጉዲሰን ፓርክ ለማዘዋወር እየሰሩ ነው።
(Sunday Mirror)





ዌስት ሀም በቀጣዩ ሳምንት ከቤኔፊካ ጋር ይወያያል።ውይይቱ የሚያተኩረው ፖርቱጋላዊውን አማካይ ጌዲሰን ፈርናንዴዝ በውሰት ስለመውሰድ ላይ ይሆናል።
(Record, via Star on Sunday)





ቶተንሃም በውሰት ከሪያል ቤቲስ አምጥቶት የነበረውን አርጀንቲናዊውን አማካይ ጂዮቫኒ ሌ ሶልሶ በቋሚነት ለማዘዋወር ለስፔኑ ክለቡ £27ሚ. አቅርቧል።ጆዜ ሞሪንሆ አማካዩን በጥብቅ ይፈልጉታል።
(Sun)





ክሪስታል ፓላስ ቱርካዊውን የኤቨርተን አጥቂ ሴንክ ቶሱን በውሰት ለማዘዋወር ለመርሲሳይዱ ክለብ ጥያቄ አቅርቧል።
(Mail on Sunday)





የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሞኒ በአርሰናል እና ቶተንሃም እየተፈለገ ያለውን ፈረንሳዊውን አማካይ ቶማስ ሌማር ማጣት አይፈልጉም።
(Mirror)





ቼልሲ ፣ ክሪስታል ፓላስ እና ብራይተን ሩሲያዊውን የሲኤስኬ ሞስኮ አጥቂ ፌዶር ቻሎቭ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Sky Sports)



No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...