አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን አማካይ ፖል ፖግባ ለማዘዋወር ከገንዘብ በተጨማሪ ለማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውሩ አካል ሆኖ ጀርመናዊውን አማካይ ቶኒ ክሩስ የመስጠት ዕቅድ አለው።
(Sun)
በሌላ ዜና ደግሞ ጁቬንትስም የቀድሞው ተጨዋቹን ፖል ፖግባን ለማዘዋወር አድናን ራቢዮ ላይ ገንዘብ ጨምሮ ለማንቸስተር ዩናይትድ ጥያቄ አቅርቧል።
(Sun)
አርሰናል የኖርዊች ሲቲውን እንግሊዛዊ ተከላካይ ማክስ አሮንስ ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ሲሆን የከተማ ተቀናቃኙ ቶተንሃምም የ19 አመቱ ተከላካይ ፈላጊ ነው።ስፐርስ ተጨዋቹን የማግኘት ዕድሏ ሰፉ፡ነውም ተብሏል።
(Daily Mail)
አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ 2015 ላይ ሊቨርፑል ብሬንደን ሮጀርስን ካሰናበተ በኋላ ሊሾማቸው ጥያቄ አቅርቦላቸው ባለመስማማት እንዳልተሳካ ተናገሩ።ሊቨርፑል እሳቸውን ካናገረ እና ካልተሳካ በኋላ ነበር የርገን ክሎፕን የሾመው።
(Telegraph)
ማንቸስተር ዩናይትድ ኖርዌያዊውን አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ለማዘዋወር ከፍተኛ ፍላጎት አሳድሮ የነበር ቢሆንም ወደ ቦሩሲያ፡ዶርትመንድ መዘዋወሩ ይታወሳል።በዚህም የተጨዋቹን ወኪል ሚኖ ራዮላ ተቀይመውታል ተብሏል።ራዮላ የፖል ፖግባም ወኪል እንደሆነ ይታወቃል።
(Daily Mail)
ዴንማርካዊው የቶተንሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ወደ ጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።
(Ekstra Bladet, in Danish)
ቦሩሲያ ዶርትመንድ በቼልሲ የሚፈለገውን እንግሊዛዊውን አጥቂ ጄደን ሳንቾ ቢያንስ እስከ አመቱ መጨረሻ በክለቡ የማቆየት እቅድ እንዳለው ታውቋል።በዚህም ቼልሲ ሙሉ ለሙሉ ትኩረቱን ወደ ራ.ቢ ሌብዚኩ ጀርመናዊ አጥቂ ቲሞ ዋርነር አዙሯል።
(Goal.com)
የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሞኒ በአርሰናል እና ቶተንሃም እየተፈለገ ያለውን ፈረንሳዊውን አማካይ ቶማስ ሌማር ማጣት አይፈልጉም።
(Mirror)
ቼልሲ ፣ ክሪስታል ፓላስ እና ብራይተን ሩሲያዊውን የሲኤስኬ ሞስኮ አጥቂ ፌዶር ቻሎቭ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Sky Sports)
No comments:
Post a Comment