Thursday, January 2, 2020

የዕለተ ሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

               አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)




ኔይማር እስከ አመቱ መጨረሻ በፓሪሰን ዤርመን ሊቆይ ይችላል።ስሙ ከቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና ጋር በስፋት የተያያዘው ኔይማር ከምባፔ ጋር ደስተኛ ሲሆን ከክለቡ ጋርም ሻምፒዮንስ ሊግን ማሳካት ይሻል።
(L'Equipe)





ቼልሲ ፈረንሳዊውን አጥቂ ሞሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር £40ሚ. አቅርቦ ክለቡ ሊዮን ውድቅ አድርጎበታል።ፍራንክ ላምፓርድ ተጨዋቹ ስታንፎርድ ብሪጅ እንዲከትም አጥብቆ ይሻል።
(FootMercato)






ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ አርሰናልን እንደማይለቅ ተናገረ።በትናንትናው ዕለተ በተከፈተው የዝውውር መስኮት መድፈኞቹን እንደሚለቅ ሲነገር ቢቆይም "100% በአርሰናል እቆያለሁ" ሲል ተናግሯል።ይህም ከአዲሱ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በጎ ዜና ነው ተብሏል።
(Goal)


የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የገና ሰሞን ጨዋታ ዛሬም ሲቀጥል ሊጉን በሰፊ ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው  ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሼፍልድ ዩናይትድን ያስተናግዳል።በዘንድሮው አመት ድንቅ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው አዲሱ አዳጊ ክለብ ሼፍልድ ቀያዮቹን እንደሚፈትን ይጠበቃል።





አስቶን ቪላ ሚቺ ባትሹዋይን ከቼልሲ በውሰት ለመውሰድ እየሰራ ነው።ቤልጄሚያዊው አጥቂ በፍራንክ ላምፓርድ ቡድን ውስጥ በቋሚነት የመሰለፍ ዕድልን እምብዛም ማግኘት አልቻለም።
(FootMercato)





አርሰናል የአጥቂ ስፍራ መስመሩን ለማጠናቀር አይኑን ወደ ስፔን በመጣል የአትሌቲኮ ማድሪዱን አጥቂ ቶማስ ሌማር ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ከሞናኮ ወደ አትኬቲኮ በውድ ዋጋ ከተዘዋወረ አንስቶ አመርቂ እንቅስቃሴ ያላደረገው ሌማር ወደ ሰሜን ለንደኑ ክለብ የመጓዝ ዕድሉ ሰፊ ይመስላል።
(Marca)





አንጋፋው አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ዛሬ በይፋ ኤሲ ሚላንን ተቀላቅሏል።የቀድሞው የአያክስ ፣ ባርሴሎና ፣ኢንተርሚላን ፣ኤሲ ሚላን ፣  ጁቬንትስ እና ማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ አሁን 38ተኛ አመቱ ላይ ነው የሚገኘው።
(Goal)





የባርሴሎናው የቀኝ መስመር ተከላካይ ኔልሰን ሴሜዶ በዝውውር መስኮቱ ብሉግራናዎቹን እንደሚለቅ ይጠበቃል።ፖርቱጋላዊው ኢንተርናሽናል በዘንድሮው አመት በቋሚነት የመሰለፍ ዕድልን በሰርጂ ሮቤርቶ ተነጥቋል።
(Sport)





ፔፕ ጋርዲዮላ በአመቱ መጨረሻ ማንቸስተር ሲቲን ሊለቅ እንደሚችል የቀድሞው የክለቡ አማካይ ሚኬል ብራውን ተናግሯል።በዘንድሮው አመት በኤቲሀድ ደካማ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ፔፕ እስከ 2021 የሚያቆይ ኮንትራት በውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት አለው።
(Goal)





No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...