Wednesday, January 1, 2020

የዕለተ ሐሙስ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ትናንት ምሽት ሲጠበቅ በነበረው የአርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታ አርሰናል 2-0 አሸንፏል።ሜሱት ኦዚል ድንቅ እንቅስቃሴ ባደረገበት ጨዋታ ፔፔ እና ሶቅራጠስ ለመድፈኞቹ ግቦቹን ያስቆጠሩ ሲሆን አርቴታ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ተቀዳጅቷል።





ናፖሊ እና አያክስ ቤልጄሚያዊውን የቶተንሃም ተከላካይ ያን ቬርቶገን ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የ32 አመቱ ተከላካይ በስፐርስ ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን ከተከፈተው የዝውውር መስኮት ስፐርስ ካለሸጠው ክረምት ላይ ወደ ፈለገበት ክለብ በነጻ መሄድ ይችላል።
(Telegraph)





ሪያል ማድሪድ ከሴኔጋላዊው የ27 አመት አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ወኪሎች ጋር መነጋገሩ ተገልጿል።ሎስብላንኮዎቹ የሊቨርፑሉን ድንቅ የክንፍ አጥቂ በጥብቅ ይሹታል።
(Le10Sport)






ስዊዘርላንዳዊው አማካይ ግራኒት ዣካ ወደ ሀርታ በርሊን በውሰት ከመጓዙ በፊት ከአዲሱ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ጋር በክለቡ ስለሚኖረው ሚና መነጋገር ይፈልጋል።
(Independent)





የቼልሲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ክለቡ ኮዲቫራዊውን የክሪስታል ፓላስ የክንፍ አጥቂ ዊልፍሬድ ዛሃ ለማዘዋወር ፍላጎት እንደሌለው ተናግሯል።
(Star)





የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እንግሊዛዊው አማካይ አዳም ላላና በአመቱ መጨረሻ ውሉ ሲጠናቀቅ ከክለቡ ሊሰናበት እንደሚችል ተናግረዋል።በአንድ ወቅት ብዙዎች ሲያሞግሱት የነበረው ላላና በተለይ ጉዳት የእግር ኳስ ህይወቱ ላይ ጥቁር ጥላ ሆኖበታል።
(Mirror)




ኤቨርተን ሞይስ ኪንን እንደሚፈልገው ነገር ግን ጁቬንትስ ተጨዋቹን በቋሚነት የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው የጣሊያናዊው አጥቂ ወኪል፡ተናግሯል።
(La Repubblica via Star)





ፖርቱጋላዊው የስፖርቲንግ ሊዝበን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ወደ ቶተንሃም ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሶ እንደነበር ተናግሯል።የ25 አመቱ አማካይ በአሁኑ ሰዓት በተለይ በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ይፈለጋል።
(Express)






ማርሴ እና አስቶን ቪላ በአሁኑ ሰዓት በቱርክ የሚገኘውን የቀድሞውን የቼልሲ እና ሊቨርፑል አጥቂ ዳኔል ስተሪጅ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀመረዋል።
(Mail)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...